Get Mystery Box with random crypto!

ቀጣይ አመት በደንብ በኩል ማሻሻያዎች ይኖሩ ይሆን? በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ኘሪምየር | ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

ቀጣይ አመት በደንብ በኩል ማሻሻያዎች ይኖሩ ይሆን?

በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ የተለያዩ ችግሮች መስተዋላቸው ይስተዋላል።ከቅርብ ሳምንታት ብንጀምር እንኳን የሜዳ አመዳደብ ላይ የተነሳ ቅሬታን ማስታወስ እንችላለን።

ታዲያ አወዳዳሪው አካል በዘንድሮው የውድድር ዘመን የታዩ ድክመቶች በቀጣይ እንዳይደገሙ መፍትሄ ይሆናል ብሎ ያሰበው የውድድር ደንቡን ማሻሻል ነው። በዚህም መሠረት ይሄን የክረምት ወቅት ብሎም እስከ መስከረም ድረስ በነዚህ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አዳዲስ የተሻሻሉ ደንቦች በቀጣይ አመት በውድድሩ ላይ እንደሚተገበሩ ይጠበቃል።

የሰሞኑ ጉዳይ በአወዳዳሪው አካል እንዴት እየታቀኘ ነው?

ሌላው የሰሞኑን ጉዳይ በተመለከተ አወዳዳሪው አካል ከእለቱ ጀምሮ በጉዳዩ ላይ ውይይቶችን ጀምሮ የነበረ ሲሆን ጉዳዩን ለመመርመር በነገው እለት የ3ቱ ጨዎታዎች ኮሚሽነሮች፣ ዋና ዳኞች፣4ተኛ ዳኞች እና ድሬደዋን፣ቅ/ጊዮርጊስን እና አዳማን በመላቀቅ ጠቅመዋል ተብለው የተጠረጠሩት የፋሲል ከነማ፣የአዲስ አበባ ከነማ እና የሀዋሳ ከነማ አሰልጣኞች እና የቡድን መሪዎች ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል። አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት የተጠሩትን አካላት አወዳዳሪው አካል በተጠናል የሚያነጋግራቸው ሲሆን ዛሬ ብዙም አጥጋቢ መረጃ ካልተገኘ ተጨማሪ ምርመራዎችን እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል።
ከምርመራዎች በኋላም ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ አካላት ላይ ቆራጥ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውንም ለማወቅ ችለናል።

ዳኝነትን በተመለከተስ?

ሌላው ዘንድሮ የታየው ክፍተት የዳኝነቱ ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል፤ ይህንንም ለማሻል ያግዝ ዘንድ በአወዳዳሪው አካል ከተያዙ እቅዶች መካከል በክረምቱ ከዲኤስቲቪ ጋር በመተባበር ከውጭ ሀገራት በሚመጡ ባለሙያዎች የተለያዩ የብቃት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን ለሊጉ ዳኞች መስጠት ነው። ይህም ተግባራዊ ሊሆን ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን በቅርቡ ይጀመራል።  በተጨማሪም ደግሞ በቴክኖሎጂ ለመታገዝ የቫር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ከውጭ ድርጅት ጋር አወዳዳሪው አካል በንግግር ላይ መሆኑን መግለፃችን አይዘነጋም። አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ይሄንንም ከ2015 ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ንግግሮች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

የፎርማት ጉዳይ

ሊጉ ዘንድሮ እና አምና በተካሄደበት ፎርማት ነው መካሄዱን የሚቀጥለው።

ዘንድሮ ሊጋችን ከብሮድካስቲንግ ምን ያህል ገንዘብ ወደ ካዝናው አስገባ?

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ በዘንድሮው የውድድር አመት ከዲኤስቲቪ የቴሌቪዥን መብት ሽያጭ 4.25 ሚሊዮን ዶላር( ወደ 222 ሚሊዮን 54 ሺህ 467 ብር የሚጠጋ) ገንዘብ ወደ ካዝናው ማስገባቱን ለማወቅ ተችሏል።
Utopia


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene


#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official