Get Mystery Box with random crypto!

#ቀጣዮን_የውድድር_ዘመን_ከተስፈኛ_ልጆቻችን_ጋራ #እኛ ደጋፊዎች ያለፈውን ዓመት በዬሄዱበት | ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

#ቀጣዮን_የውድድር_ዘመን_ከተስፈኛ_ልጆቻችን_ጋራ

#እኛ ደጋፊዎች ያለፈውን ዓመት በዬሄዱበት ሄደን ደጀን: ወኔ: ተጨማሪ አቅምን የፈጠርን በውድድሩ ዓመት መጨረሻም ጀግኖች ልጆቻችንን በማመስገን : በደማቅ አቀባበል በማንገስ እንደቋጨን (እንደደመደምን)ሁሉ ለቀጣዮ ዓመት ደግሞ በክለባችን ላይ በአንክሮ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጦት ሊሰራ ስለሚገባ የሁሉም ደጋፊ ቀዳሚ አጀንዳ: ፍላጎት የሆነውን የስራ ዘርፍ ለክለባችን የበላይ ቦርድ አባላት: ለክለቡ ፕሬዘዳንት: ብሎም የ2015 የቡድኑ ኮቺንግ ስታፍ በሙሉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

#በቀጣዮ ዓመት ለስኬት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከሚደረጉ ዝግጅቶች ዋነኛው በዝውውሩ መድረክ ክለቡ ንቁ ተሳታፊ መሆኑ የታወቀና እርግጥ ቢሆንም ይህ የዝውውር እንቅስቃሴ በቢጫ ተሴራ ላይ ያሉ ብሎም አሁን ለሚጨመሩ የተስፉ ቡድኑ ግብአት የከተማችን ፍሬዎች : ከድጋፍ ጀምሮ ልባቸው ውስጥ ከልጅነት እስከ እውቀት ፋሲልን አትመው ላደጉት : እስትንፋሰ ፋሲላዊ : የክለባችን ታማኝ ተረካቢ: እንቁ ልጆቻችንን #የሚገፉ #የሚጫን ሊሆን እንደማይገባ የዝውውሩ ሂደት እኛ ደጋፊዎች በአፅዕኖት መናገር እንወዳለን።

#ከዛም በላይ አቅማቸው የተሻሉ መሆናቸው እየታመነ ከተቀያሪ ወንበር ሳይነሱ ዓመቱን የሚጨርሱበት መንገድ በስንት አስቸጋሪ የከተማ ዕድሜ ዕርከን ውድድር እስከ አሰልቺ የፕሮጀክት ስልጠና እዚህ የደረሱ ልጆቻችን ከአቋም ዝቅ እያደረገ: በስነልቦናም እያዘቀጠ : በቁጥርም እያመነመነ : አቅም ችሎታቸው ላይ ተፅዕኖን እየፈጠረ መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ለቀጣይ የውድድር ዘመን አቅማቸውን የሚያሳዩበትን በቂ የመጫወት ጊዜ እንዲያገኙ እንሻለን እፈልጋለን።
#በክልላችን :በከተማችን ጎንደር ተጫዋቾች በቅለው በብሔራዊ ቡድን እና በፕሮፌሽናል ደረጃ የማይታዮበትም ምክንያት ክለቦቻችን ለታዳጊ የሚሰጡት አነስተኛ ትኩረት መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ከሌሎች ክልል ቡድኖች አንፃር በፋይናንስ የተሻልን ሆነን ሳለ በታዳጊ ማብቃት ደረጃ ደካማ የሆንበት ምክንያት በጥናት ተደግፎ መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ መሆኑንም ለመጠቆም እንወዳለን።

#ከተማችን ጎንደር ብዙ የመሰረተ ልማት ግድፈቶችን ከዕይታዋ ገለል አድርጋ ከጎዶሎው መቀነቷ ፈታ የምትቸረው የአብራኳ ክፋይ ክለባችን ምንም በሀገራችን እግር ኳስ ፎርማት ድክመት አትራፊ ሆኖ የገንዘብ ትርፍ ባይመጣም የከተማዋን ፍሬዎች: የህዝቡን አካል ታዳጊዎች በተሻለ በማብቃት ህዝቧን ሊክስ ይገባል ወደ ህዝቧም ክለቡ ሀፍቱን ሊያፈስ ይገባል የሚል አፅዕኖታዊ ጥያቄ አለን። እንጂ ከታዳጊ ያነሰ አቅምን ይዘው ከነሱ በላይ እየተከፈላቸው ቡድናችን ወደ ዝቅታ የሚመሩ ልጆችን ዕልባት እንስጥ ...ለቡና መጠጫ እንኳ የማይተርፍ ሳንቲም የሚያገኙ ታዳጊ ልጆቻችን ተጠቃሚ እና ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን መንገድ መፈለግ እንደ ቀዳሚ ስራ ትኩረት ቢደረግበት በሚል የኛ ደጋፊዎችን ዕሳቤ ለመጠቆም እንወዳለን።

ሁሌም እኛ ደጋፊዎች ትላንትም ነበርን ዛሬም አለን ሁሌም የጀርባ ደጀናቹህ እና አቅማቹህ እየሆን ለዘላለም አለን።

#የክለቡ ቀዳሚ ባለቤቶች እኛ ደጋፊዎች እስከሆንም ድረስ ድምፃችን ይሰማ። #በውስን ግለሰብ ፍላጎት ብቻ ክለባችን መመራት ሊያቆም ይገባል በሁሉም ውሳኔ የኛ ደጋፊዎች ፍላጎት ቦታ ሊያገኝ ይገባል።

#ዝንተ ዓለም ፋሲል ከነማ

#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official