Get Mystery Box with random crypto!

ሊግ ካፓኒው ለዛሬ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግራለሁ ባለው መሰረት የሚወሰኑ ውሳኔወችን አየጠበ | ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

ሊግ ካፓኒው ለዛሬ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግራለሁ ባለው መሰረት የሚወሰኑ ውሳኔወችን አየጠበቅን ነው ሚዛናዊ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን


ከዛ በፊት
#ሸር ይደረግ
ከጨዋታው በፊትም በጨዋታው በኋላም ብዙ ትኩረትን የሳቡ የ30ኛው ሳምንት የኢ. ፕሪሜርሊግ ለሻምፕዮንና ላለመውረድ የነበሩ ክስተቶች፦
1. አዲስ አበባ ከተማ ከጊዮርጊስ የነበሩ ክስተቶች ስናይ
አዲስ አበባ ከተማ
-በቁጥር በረከት ያሉ ቋሚ ተጫዋቾች ተጠባባቂ ወንበር ላይ መቀመጣቸውና አሰልጣኙ ሲጠየቅ ያሳፈቸው መሆኑ
-አሰልጣኝ ጳውሎስ ከጨዋታው በፊት የፋሲልና ድሬደዋ ጨዋታን በተመለከተ ቅድመ ክስ ማስያዙ
-ጨዋታው ላይ ከአዲስ አበባ ተጫዋቾች እስከ ዳኛው ውሳኔ የነበሩ ትይንቶች
-አሰልጣኙ ቡድኑን የመሩበት ከወትሮው የተለየ የተነሳሽነት ማነስ
- ተጫዋች ሮቤል ያለቀሰበትና በጨዋታው ተጠባባቂ ስለሆነበት ምክንያት ከአሰልጣኙ ጋር ስለተነጋገሩበትና ሌሎች

2. ሀዋሳና አዳማን በተመለከተ በአመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳማዎች 3 ጎሎችን በ9 ደቂቃ ማስቆጠራቸው በኋላም ሀዋሳ በተከታታይ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠሩበትና ጨዋታው የተጠናቀቀበት መንገድ

3. ወደ ድሬደዋና ፋሲል ጨዋታ ስንመጣ፦
ጨዋታው እስከ 76ኛው ደቂቃ ምንም እንኳን ፋሲል 2 ለ0 ቢመራም ጥሩ የመሸናነፍ ፍላጎት የነበረበት ሲሆን ጊዮርጊስ 2 ለ0 መምራቱን ተከትሎ ከዋንጫው ፉክክር ውጭ የሆኑት ፋሲሎች የመጫወት ፍላጎት ማጣትን አጋጣሚ ድሬዎች በመጠቀም በ13 ደቂቃ ውስጥ 3 ለ 2 በማሸነፍ በሰላማዊ መንገድ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ነገር ግን ድሬደዋ ከነማ ሶስተኛውን ጎል ሲያስቆጥር የጊዮርጊስንና የአዲስ አበባ ከተማን ጨዋታ በአይነ ቁራኛ ሲከታተል የነበሩ ጥቂት የፋሲልን መለያ የለበሱ ተመልካቾች መጨፈራቸው ትኩረትን የሳበ ነበር። እዚህ ላይ ስለ Emotional እናንሳ አንዳንድ ፀሀፍት ስሜታዊነት መዳረሻው ራስን እስከ ማጥፋት ይርሳል ይላሉ ያውም በደል ተጨምሮበት ለዚህ ነው ደጋፊዎች ጨዋታው ላይ የተሰራውን ደባ በመረዳት ስሜታቸው ያዘዛቸውን ያደረጉ፤ ይህን ለመወንጀል ቦታው ላይ መሆን አይጠበቅም። ነገር ግን እነ መርጦ አልቃሽ ውስን የስፓርት ጋዜጠኛ በአለም ላይ ተደርጎ የማያውቅ በማስመሰል ፍፁም ሚዛኑን በሳተ መልኩ የክለባችን መልካም ገፅታ በማበላሸትና የወከለውን ማህበረብ እሴት፣ መገለጫና ማንነትን ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ከፍተዋል።
ከዚህ በተጨማራ አወዳዳሪው አካል አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ መጠበቅና መዘገብ ሲገባው ሆን ተብሎ ውሳኔ ሰጭዎችን ጫና ውስጥ ለመክተት ዘመቻ አጠናክረው ቀጥለዋል።

#በመጨረሻም ፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ አወዳዳሪው አካል በህጉ መሰረት ውሳኔ እንዲሰጥ የማድረግ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡና ከውሳኔ በኋላ የፁሁፍም ሆነ የድምፅ ማስረጃዎችን በመያዝ የሚዲያ ህግ በሚፈቅደው መሰረት እነዚህን ተቋማትና መርጦ አልቃሽ ግለሰቦችን ለህግ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን።

#ለደጋፊዎችና ስፓርት ወዳድ ማህበረሰብ በሙሉ በተለይ አዲስ አበባ አካባቢ ያላችሁ አስፈላጊውን ማስረጃ መሰብሰባችን እንዳንዘነጋ፤
ሁሉም ደጋፊዎች ከስሜት ወጥተን በተረጋጋ መንገድ ነገሮችን እንድንከታተል።

#እኛ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የሁሉም ክለብ ደጋፊዎች ተፎካካሪዎቻችን እንጅ ጠላቶቻችን አይደሉም።
#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ!!!


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official