Get Mystery Box with random crypto!

ቡናችን👆

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_coffee_sc — ቡናችን👆
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_coffee_sc — ቡናችን👆
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_coffee_sc
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.79K
የሰርጥ መግለጫ

🍵ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 62

2022-09-23 07:26:45
የጨዋታ ቀን

ሸገር ደርቢ
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታ

ዛሬ 13/01/2015
ኢትዮጲያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
10:00
አበበ ቢቂላ ስታድየም (አአ)

የጨዋታው ውጤት ግምታችሁን ከታች አድርሱን!

አይቀርም ሁላችንም ቡናውያን ካምቦሎጆ በቦታችን እንገናኝ!

ድል ለ ኢትዮጲያ ቡና

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
3.4K views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 21:20:54
ለጠቅላላ_ዕውቀት
Via Eyobed belayneh

የኢትዮጵያ_ቡና ከ20 አመት በታች ቡድን እና #የጊዮርጊስ ከ20 አመት በታች ቡድን ያለፉትን ሁለት አመታት አራት ጨዋታዎችን አከናውነው ኢትዮጵያ ቡና ሶስት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ሲችል በአንድ ብቻ ነው የተሸነፈው።

ያለፉትን ሁለት አመታት በአንድ ምድብ በነበርንበት ሁሉ በደረጃ ከኛ በታች ሆነው ነው የጨረሱት።

ስለ ታዳጊዎች ይወራ ካልንም ይሄ ነው እውነታው! በርቱልን ጀግኖች

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
3.7K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 19:20:12
ዝግጁ

የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ

ሸገር ደርቢ
ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስ

ነገ አርብ መስከረም 13/2015
10:00
አበበ በቂላ ስታዲየም

መቅረት አይታሰብም

ድል ለ ኢትዮጲያ ቡና

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
3.8K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 18:00:57
የአፍሪካ ከ 23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ አንደኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ

ጨዋታው ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ 0-0 ዲሪ ኮንጎ

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
3.7K viewsedited  15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 10:02:12
ሸገር ደርቢ

ከቅዳሜ ጀምሮ ሲደረጉ የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት በተደረጉ ጨዋታዎች ለገጣፎ ለገዳዲ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አስቀድመው ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ዛሬ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች በዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት የተለዩ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም መቻል እና ለጋጣፎ ለገዳዲ በግማሽ ፍፃሜው ተገናኝተዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ከበርካታ ጊዜ በኃላ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ የሚያደርጉ ሲሆን ጨዋታው ነገ 10:00 በአበበ በቂላ ስታዲየም ይደረጋል።

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
4.0K views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 20:50:28
ከራስ አልፎ ለባንዲራ
ውድ ልጆች የሚያፈራ

1, ብሩክ በየነ
2, መሀመድ ኑር
3, መስፍን ታፈሰ
4, ጫላ ተሺታ
5, አብዱልከሪም ወርቁ
6, ሃይለሚካኤል አደፍርስ

ኢትዮጵያ ቡና

የኢትዮጲያ ከ 23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ በ 10:00 አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከዲሞክራቲክ ኮንጎ አቻው ጋር በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ውድድር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

መግቢያ በነፃ

ጨዋታውን መታደም የምንችል በሙሉ በመግባት ልጆቻችንን እናበረታታ!

ድል ለ ዋልያው

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
4.0K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 19:13:08
የጨዋታ ጥቆማ

16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ክለባችን የኢትዮጵያ ቡና የፊታችን አርብ መስከረም 13/2015 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ነገ በዕጣ ከሚለየው ቡድን ጋር ለዋንጫ ለማለፍ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
3.9K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 17:29:08
OFFICIAL

ዘነበ ከድር ለኢትዮጲያ ቡና ፊርማውን አኑሯል!

ያለፉትን አመታት በደቡብ ፖሊስና በሀዋሳ ከነማ ጥሩ የውድድር ጊዜን ያሳለፈው የግራ ተመላላሹ ዘነበ ከድር በኢትዮጲያ ቡና የሚያቆየውን የሁለት አመት ስምምነት ተፈራርሟል!

እየተካሄደ በሚገኘው የሲቲ ካፕ ውድድር ላይም ድንቅ ብቃቱን እያሳየን ይገኛል!

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
4.1K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 20:23:16
የሻኪሶ ስጦታ!
(Abdu Hussen )

ልጁ ሲበዛ ፈጣን ነው። ፍጥነቱ ለ ዋናው ሊግ እንደውም የሚበዛ ይመስለኛል ሊጋችንን እንደምናውቀው የ ጎልማሶች ሶምሶማ አሯሯጥ በብዛት የ ሚታይበት መሆኑ እሙን ነው ።

ልጁ ከ ክልል ክለቦች ሻምፕዮና ለ ዋናው ሊግ ኢትዮጵያ ቡና መፈረሙ ለ አንዳንዶች አጀብ ቢያስብልም ለኛ አዲስ አደለም ። ስሙን ከማያቁት ቡድን መምጣቱ ተከትሎ ሊሳለቁበን ሞክረዋል።

እኛ ደሞ እስቲ Sadio mane ከተገኘበት ቲንሿ እና ገጠራማዋ Bambali መንደር ጎራ ብላቹ ተመልከቱ እንላለን ።

ትንሿ ችግኝ ኮትኩቶ ውሀ አጠጥቶ ሚያሳድጋት ካገኘች ትልቅ ዛፍ ትሆናለች!

ከ ኳስ ጋር እጅግ ምቾት የሚሰማውን ፈጣኑ ጎበዝ ጎል አስቆጣሪውን ችግኛችን ኮትኩቶ ውሀ አጠጥቶ ትልቅ ዛፍ የሚያደርገው ሰው ያስፈልገዋል!

እሱን ለ ኮች ተመስገን ዳና አደራ እያልን ልጃችንን በርታ ጠንክረህ ስራ ትልቅ ትሆናለህ እንለዋለን ።

19 Anteneh tefera!

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
4.4K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 14:23:58
አንተነህ ተፈራ በትላንትናው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታ ላይ!

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
4.2K viewsedited  11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ