Get Mystery Box with random crypto!

ሸገር ደርቢ ከቅዳሜ ጀምሮ ሲደረጉ የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕ | ቡናችን👆

ሸገር ደርቢ

ከቅዳሜ ጀምሮ ሲደረጉ የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት በተደረጉ ጨዋታዎች ለገጣፎ ለገዳዲ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አስቀድመው ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ዛሬ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች በዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት የተለዩ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም መቻል እና ለጋጣፎ ለገዳዲ በግማሽ ፍፃሜው ተገናኝተዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ከበርካታ ጊዜ በኃላ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ የሚያደርጉ ሲሆን ጨዋታው ነገ 10:00 በአበበ በቂላ ስታዲየም ይደረጋል።

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc