Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.29K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-08-24 19:12:15
~ የግንባታ ጨረታዎች፣
የግንባታ ዕቃዎችን ወቅታዊ ዋጋ፣ እና
ወቅታዊ መረጃዎችን:Vacancies post ወደ ምናደርግበት channelችን ይቀላቀሉ


https://t.me/conlinkcatalogue

https://t.me/conlinkcatalogue
6.0K viewsENG Sintayehu Melese, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 10:14:17
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ያተኮረ ምርጥ መጽሐፍ ነው በሁሉም መሀንዲሶች እጅ መገኘት ያለበት መጸሐፍ ፡፡
*በEng Endawoke fenta የተዘጋጀ


1. ጃዕፈር መፃህፍት መሸጫ ( ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያዉ አጠገብ ፣ ተወልደ ህንፃ ስር)
ተጨማሪ የመሸጫ መዳረሻዎች ፤
2. መገናኛ ፣ ዲያስፖራ አደባባይ፣ ኤደን መፀሃፍት ወይንም ማራቶን ህንፃ 6ኛ ፎቅ BeGet ኢንጅነሪንግ
3. አራት ኪሎ ዩኒቨርቲ ፊት ለፊት ፣ ዩኒቨርሳል መፀሃፍት
5. ገርጂ-መብራት ሃይል ፣ፍዉንቴን ሕንፃ ጎን 100ሜ ወረድ ብሎ ፣በለጠ መፀሃፍት
6. ገርጂ-ታክሲ ተራ ፊት ለፊት ፣ዕዉቀትን ፍለጋ መፀሃፍት


ከAddis ababa ውጭ መከፋፈል ለምትፈልጉ contact me @+251927708078

*እትዮ ኮንስትራክሽን
4.8K viewsENG Sintayehu Melese, edited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:55:42 በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ ኢንጅነርዎች ሊያውቃቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች...

1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ
የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።
ከታች የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test):
•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test):
•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test:
•Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ አንማር ይሆናል ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ
መማር ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::

2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል
ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን። እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ
በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።

3)የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF
SURVEYING INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ
መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !

4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES
USED IN CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካምድራቸው የአየር፣የንፋስ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸውአንፃርየሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ (Construction codes) አላቸው።
አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ
የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት
ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን
ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ
የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።

5) BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ
ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ
የሆነው የግንባታ አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል
ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ። ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን
ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል

*6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል ማለት ነው።
ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ
እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት
ነው::

7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)
ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን
የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው። (እንዴት መገመት እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን)

8 )የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL)
ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው።ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ
ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው።አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።
አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን አደጋ ለመከላከል።

9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT)
እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣
ለጥንቃቄ የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን ነው

10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ
(COORDINATION) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ
እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ ሊኖረን ይገባል።
ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል።
ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና
ወሳኝ ነገር ነው።
አንድ ጥሩ የሚባል CONSTRUCTION እንጅነር ማወቅ ስለሚገባው ነገሮች ትንሽም ቢሆን እውቀት እንደሰጠናቹ ተስፋ እናረጋለን::


@ethioengineers1
3.9K viewsENG Sintayehu Melese, 06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:37:22
አራብሳ እንዲሁም የካ አባዶ አካባቢ ያሉ የእግረኛ መንገዶች እጅግ ትኩረትን ይሻሉ !!

https://t.me/ethioengineers1
4.3K viewsENG Sintayehu Melese, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 14:29:18
" የታደሰው የቀበሌ ቤታችን ጠቦ ከቤት ወደ ኮሪደር ተለውጧል ። አልጋ እንኳን አያዘረጋንም " ወይዘሮ አሰገደች ዓሊ

ይሄ የቀበሌ ቤት ከሚኒሊክ ሆስፒታል ጀርባ ትንሽ ራቅ ባለ ስፍራ በሚገኝ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቀበሌ 05 የሚገኝ ሸክላ ሰፈር ተብሎ በሚጠራ ቦታ የሚገኝ ነው።

ሰሞኑ በካፒታል ሆቴል ወጪ ቤቱ የታደሰ ሲሆኑ አዛውንቶቹ ቤታችን በመታደሱ ደስተኛ ብንሆንም ቤታችን ወደ ጎን ጠቦ አልጋ ለመዘርጋት እንኳን ያስቸግረናል ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል ።
" ቤታችን ወደ ኮሪደርነት ተቀየረች''
የቀበሌ ሰዎች ቤት ሲያድሱ የአንዱን ቤት አስፍተው የአንዱን አጥበው ለጭቅጭቅ ዳርገውናል ሲሉ ወይዘሮ አሰገደች ዓሊ ተናግረዋል።


https://t.me/ethioengineers1
5.4K viewsENG Sintayehu Melese, 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:14:06
በሕንፃ መናድ 6 ሰዎች ሞቱ

በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 መርካቶ አካባቢ አሮጌ የኪራይ ቤቶች መጋዘን በመናዱ ምክንያት በአካባቢው በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል፡፡

የፖሊስ መግለጫ

እስካሁን ባለው መረጃ 6 ሰው የሞተ ሲሆን ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ላይም ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል::
ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እና ያስከተለውን ጉዳት እያጣራ ይገኛል ሲል የአ/አ ፖሊስ አስታውቋል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
6.6K viewsENG Sintayehu Melese, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 15:36:42
#ባለሀብቱ ወርቁ አይተነው በ1ቢ ዶላር የሲሚንቶ ፋብሪካ ሊገነቡ መሆኑ ተሰምቷል።

የስርጭት መመሪያ እና አሰራር መቀያየር ቢደረግም መፍትሄ ያጣው የሲሚንቶ ጉዳይ ህዝቡን እያማረረ እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን እየጎዳ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል

https://t.me/ethioengineers1
6.3K viewsENG Sintayehu Melese, 12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 14:24:42
standard box size
.
width*length*depth
.
1. 40*50*20cm (mostly for cement mortar)
2. 40*50*18cm (for C-25 concrete)
3. 40*50*16cm (for C-30 concrete)
4. 40*50*14cm (for C-40 concrete but depend on mix design )

Hand mix shall be allowed for class II concrete ,& shall not be allowed for concrete of class C-20 & above or class I concrete
C-7
mechanical mix ratio =1:4:8
Hand mix ratio =1:3.5:8
C-15
mechanical mix ratio =1:3:6
hand mix ratio =1:3:4
C-20
mechanical mix ratio =1:2:4
C-25
mix ratio=1:2:3
C-30
mechanical mix ratio =1:2:3
C-40
mix ratio =1:1.5:3

#Ethioconstruction

@ethioengineers1
6.8K viewsENG Sintayehu Melese, 11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 21:21:43 የconstruction ስራ ማስታወቂያዎችን በቀላሉ የሚያገኙበት የቴሌግራም ቻናል ተቀላቅለዋል?ካልተቀላቀሉ

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ተቀላቅለው በየሰዓቱ ልዩነት የConstruction ስራ ማስታወቂያ መረጃዎችን ያግኙ!!!


https://t.me/conjobseekers
https://t.me/conjobseekers
7.7K viewsENG Sintayehu Melese, edited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 13:13:19 አዳማ ቆርቆሮ 28 ጌጅ ያለው ?

contact me
@Ethiocon143bot
8.7K viewsENG Sintayehu Melese, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ