Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.29K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2022-05-25 17:59:38 Ethio Construction pinned a photo
14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 17:59:22
~ የግንባታ ጨረታዎች፣
የግንባታ ዕቃዎችን ወቅታዊ ዋጋ፣

የባለሙያዎችን አድራሻ እና
ወቅታዊ መረጃዎችን post
ወደ ምናደርግበት sister channelችን ቀላቀሉ


https://t.me/conlinkcatalogue

https://t.me/conlinkcatalogue
1.6K viewsENG Sintayehu Melese, 14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 20:17:59 #ሲሚንቶ
* *
ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው

የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከስርዓቱ እንዲወጡ በማድረግ በየክልሉ ያሉ የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተክተው እንዲሠሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በገበያው ላይ በቂ የሲሚንቶ ምርት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በገበያ ላይ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በአማካይ እስከ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሆነ እና መንግሥት ሲያደርግ የነበረው የቁጥጥር ሥራ መነሳቱም እየታየ ላለው ችግር አባባሽ ሆኖ እንደተገኘ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

አዲስ ማለዳ
#የኛ ሀሳብ
* ****
#ህዝቡ የሲሚንቶ ገበያ ይረጋጋል ብሎ እየተጠባበቀ ነው።ጉዳዩን በቀላሉ ባታዩት ጥሩ ነው።
#ቸርቻሪስ ወጣ እንበል ዋናወቹ ጅምላ አከፋፋዮችስ(ዋናዎች ችግር ፈጣሪዎች ማለት ነው) ባሉበት ይቀጥላሉ?

#እትዮ_ኮንስትራክሽን
1.5K viewsENG Sintayehu Melese, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 20:53:23
#ይመዝገቡ #ይሰልጥኑ

የሲቪል ኢንጂነሪንግ፣አርክቴክቸር፣ ኮተምና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሶፍትዌርዎችን የትም ሆነው መማር ይችላሉ ከ ሰርተፊኬት ጋር፡
Megenagna
Marathon Building , 6th Floor, Office No 614


0911890392/ 0944186744

Join @BeGetEngineering
2.7K viewsBelay #1, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 18:35:57
~ የግንባታ ጨረታዎች፣
የግንባታ ዕቃዎችን ወቅታዊ ዋጋ፣

የባለሙያዎችን አድራሻ እና
ወቅታዊ መረጃዎችን post
ወደ ምናደርግበት sister channelችን ቀላቀሉ


https://t.me/conlinkcatalogue

https://t.me/conlinkcatalogue
1.6K viewsENG Sintayehu Melese, 15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:23:53 ለሚመለከተው ክፍል ጥቆማ

ዛሬ ለማድረስ የፈለግኩት ጉዳይ ከሳርቤት (ፑሽኪን አደባባይ)ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው መንገድ ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለምዶ ከጎፋማዞሪያ ወደ መብራትኃይል እንዲሁም ከጎፋማዞሪያ ወደ ጨርቆስ እየተሰራ ያለው መንገድም በከፊል እየተጠናቀቀ ይገኛል ነገርግን የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም በቀጣይ የመንገዱን እድሜ የሚያሳጥር አካባቢውንም ወደፊት በጎርፍ እንዲጥለቀለቅ የሚያደርግ ስራ እየተከናወነ ነው ይህም የመንገዱን ስራ የሚቆጣጠር ሃላፊ የሌለ በሚመስል መልክ አዲስ የተሰሩ የፍሳሽ መስመሮች (ፖሴቲዎች)ከአፍ እስከ ገደፋቸው ድረስ (ሙሉበሙሉ) በኮረትና በድንጋይ እንደተሞላ ክዳን እየተገጠመላቸው ነው ። በአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ የወረዳ አመራሮች ሳያዩ ቀርተው ነው ብዬ ለማመን ይቸግረኛል ባለቤቱ ማነው ባንተ በኩል መድረስ ከቻለ ክረምት ከመግባቱ በፊት እንዲስተካከል ቢደረግ ። እንደለመደብን ጨረስን ብለን በማግስቱ ወደ ቁፋሮ እንዳንገባ በህዝብና በመንግሥት ገንዘብ መቀለድም እንዳይሆን ብዬ ነው ።

#እትዮ_ኮንስትራክሽን
1.4K viewsENG Sintayehu Melese, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 10:37:33
#ይመዝገቡ #ይሰልጥኑ

የሲቪል ኢንጂነሪንግ፣አርክቴክቸር፣ ኮተምና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሶፍትዌርዎችን የትም ሆነው መማር ይችላሉ ከ ሰርተፊኬት ጋር፡
Megenagna
Marathon Building , 6th Floor, Office No 614


0911890392/ 0944186744

Join @BeGetEngineering
2.2K viewsENG Sintayehu Melese, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 10:37:33
~ የግንባታ ጨረታዎች፣
የግንባታ ዕቃዎችን ወቅታዊ ዋጋ፣

የባለሙያዎችን አድራሻ እና
ወቅታዊ መረጃዎችን post
ወደ ምናደርግበት sister channelችን ቀላቀሉ


https://t.me/conlinkcatalogue

https://t.me/conlinkcatalogue
2.0K viewsENG Sintayehu Melese, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 10:37:33 የሙያ ነጻነት ለአርክቴክት ግራጫ ቀለም
***

ግራጫ አካባቢ ነው፡፡ “It is a gray area” ፈረንጆች ነገሩ አልገባ ሲላቸው ወይም ሲያወዛግባቸው የሚጠቀሙት ሃረግ ነው፡፡ ቀለሙና አባባሉ መገጣጠሙ ገርሞኛል፡፡

በኪነ ህንጻ ጥበብ (Architecture) ዋነኛ የህንፃ ቀለማት ዲዛይንና መረጣ የአርክቴክቱ ዋነኛ ኃላፊነት ነው፡፡ የቀለማት ስራ ህንጻውን ከማስዋብ ባሻገር በሰው ላይ ተፈጥሮአዊ ስሜትና ስን ልቦና የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከባድ በመሆኑ በጥንቃቄ የሚታቀድ እና የሚፈጸም ስራ ነው፡፡ የቀለምን ንድፈ ሃሳብ ለማብራራት አስቸጋሪ ቢሆንም ሰዎች በተራዘመ ጉዞ የለዩትን ትርጓሜ ይዞ ማየቱ ስለምንነቱ ለመረዳት ያግዛል፡፡
ቀለማት ድምጽ አልባ የመግባቢያ መሳሪያ ተደርገው ስለሚወሰዱ የብዙሃኑን ቀልብ ይስባል፡፡ ለቀለማት ያለን ምርጫና ዝንባሌም ከሰው ሰው የሚለያይ መሆኑ ደግሞ ሌላው የቀለማት ባህሪ ነው፡፡

በአዲስ አበባ በቂ የሆነ የህዝብ ግንኙነት ስራ አለመሰራቱ ካልሆነ በስተቀር የህንጻ ቀለማት ዓይነት፣ የሚመረጡበት ዘዴና በተጓዳኝ እንደ ህንጻው አጠቃቀም ሊኖረው ስለሚገባው የቀለም ገጽታ ዝቅተኛ መስፈርቶች በቴክኒክ መመሪያ ውስጥ ተመልከተው አሉ፡፡ ባልሳሳት አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ደረጃውን ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መግዛት ይቻላል፡፡

በአንድ አንድ ሀገራት መንደሮች በልዩ ሁኔታ ወጥ የሆነ ቀለም እንዲቀቡ የሚያስገድድ ተፈጥሮአዊ ታሪካዊና መሰል ሁኔታዎች አሉ፡፡ የብዙ ሀገራትን ልምድ እንዳየሁት ከሆነ ከዝቅተኛው መስፈርት በላይ በደምሳሳው የከተማን ቀለም ወጥ አድርጎ መወሰን ግን የተለመደ አይደለም፡፡ ይሁን ቢባል እንኳን ብዙ የሚያነጋግሩ የሙያና ሞራላዊ ጉዳዮች አሉት፡፡

የሆነው ሆኖ ሰሞኑን አዲስ አበባ መስተዳድር የከተማዋን ቀለም ግራጫ እንዲሆን ወሰነ አሉ፡፡ እንግዲህ ውሳኔው የሚያስገኙትን ጥቅሞች እንዳያሳጣን እና ደግሞ ጉዳትም እንዳያስከትል በእውቀት ላይ የተመሰረተ አስተያየት ለመሰንዘር ያስገድደናል፡፡

በአጠቃላይ ባደረኩት ጥናት በሳይንሱ የሚታወቁት ቀለማትን ሀገራት ከራሳቸው ባህላዊና ስነልቦናዊ ሁኔታ በመነሳት የሚሰጡት ትርጓሜ ቢኖርም በአብዛኛው ማለት በሚቻል በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀለማት የሚከተለውን እንደየአግባብነቱ ትርጓሜ እንዲይዙ ስምምነት አለ፡፡
• ቀይ :- ጥልቅ ስሜት፣ ፍቅር፣ ቁጣ
• ብርቱካናማ :- ጉልበት፣ ደስታ፣ ህይወት
• ቢጫ :- ደስታ፣ ተስፋ፣ ማታለል
• አረንጓዴ :- አዲስ ጅምሮ፣ የተትረፈረፈ፣ ተፈጥሮ
• ሰማያዊ :- ረጋ ያለ፣ ሀላፊነት፣ ሀዘን
• ሐምራዊ :- ፈጠራ፣ ንጉሳዊ፣ ሀብት
• ጥቁር :- ምስጢር፣ ውበት፣ ክፋት
• ግራጫ :- ተለዋዋጭ ስሜት፣ ወግ አጥባቂ፣ መደበኛነት
• ነጭ :- ጥሩነት፣ ንጽህና፣ በጎነት
• ቡናማ:- ተፈጥሮ፣ ጤናማነት፣ ጥገኛነት
• ታን ወይም ቤይጅ:- ወግ አጥባቂ፣ ቅድስና፣ ደደብ
• ክሬም ወይም የዝሆን ጥርስ:- የተረጋጋ፣ የሚያምር፣ ንፅህና

ግራጫ ቀለም በዝርዝር
የግራጫ ቀለም አዎንታዊ ጎኖችን ስንመለከት፤ ግራጫ ገለልተኛ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ቀዝቃዛ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ስሜት ቀስቃሽ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ጥበብ ነው፡፡ ግራጫ ተራነት ነው፡፡ ግራጫ ዘመናዊነት ነው፡፡
የግራጫ ቀለምን አሉታዊ ጎኖች ስናይ ደግሞ፤ ግራጫ ተስፋ አስቆራጭ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ወግ አጥባቂነት ነው፡፡ ግራጫ ሃዘን ነው፡፡ ግራጫ ሰውን ከሰው የመነጠል ስሜትም ነው፡፡ ግራጫ መራራቅም ነው፡፡ ግራጫ ያልተለመዱ ኢ-ስነምግባር ድርጊትንም ይወክላል፡፡ ግራጫ አሻሚነት ነው፡፡

እንግዲህ ከእነዚህ እሳቤዎች በመነሳት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የከተማዋ ቀለም አሉታዊውን ጎኖች እንዲወክልለት አስቦ እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡

በእኔ እይታ ግራጫ የህዝብ ቀለም እንዲሆን የታሰበው ምናልባት አዲስ አበባ የሀገሪቱ ርዕሰ መዲና በመሆኗ እና በአሁኑ የሀገራችን ፖለቲካ ውጥንቅጥ ገለልተኛነቷን ለማመላከት ወይስ የፖለቲካ ቅራኔ መጫሪያነቷን ለማብረድ እንድትቀዘቅዝ፤ ወይስ አዲስ አበባ በታላቅነቷ አነቃቂ ስሜት ቀስቃሽ እንድትሆን ተፈልጎ፤ ወይስ አዲስ አበባ የጥበብ ማዕከልነቷን እውቅና ለመስጠት፤ ወይስ ለዘመናዊነቷ ምላሽ ይሆን ዘንድ ታስቦ የተቸረ የቀለም ሽልማት? ይህ ከሆነ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ይህ ነው ብሎ ከተማውን ግራጫ በግራጫ ለመቀባት መወሰን ደግሞ ስህተት ይመስለኛል፡፡ ሌሎች ቀለሞች ከላይ በአጭሩ እንዳስቀመጥኩት ከግራጫ ቀለም ባልተናነሰ የሚነግሩን አለና፡፡

ለማንኛውም በመርህ ደረጃ ህዝባዊ ቀለም ለመምረጥ የተኬደበትን ርቀት እያደነኩና እያከበርኩ ተግባራዊ ይደረግ ቢባል ሊፈጸም የማይችል ቢተገበር እንኳን ሙያዊነትና ስነምግባር የጎደለው መሆኑን ተረድቶ አስተዳደሩ ውሳኔውን እንዲያጤነው እጠቁማለሁ፡፡ ከግራጫ ቀለም ባልተናነሰ ጥቅም ያላቸውን ቀለማት ዋጋ ማሳጣትና የአርክቴክቱን የሙያ ነጻነት የሚጋፋ አደገኛ ውሳኔ እንዳይሆን ከልብ በሆነ ትህትና ጭምር ነው፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ ክትትል እና ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያቤት ከውሳኔው ጀርባ ያለው በቀጥታ የሚመለከተው መ/ቤት እንደመሆኑ መጠን በህንጻ አዋጁ ላይ የተመለከቱትን ዝቅተኛ መስፈርቶች መሟላታችውን ማረጋገጥ እና ማስጠበቅ ሚናውን እንዲወጣ እና የቀለም መረጣው ጉዳይ ደግሞ የአርክቴክቱ ኃላፊነት መሆኑን ተረድቶ ወደ ዋናውደ ስራ ቢገባ የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ የኢትዮጰያ አርኪቴክቶች ማህበርም እንደዚህ ያሉ ግድፈቶችን ለማቀናት መንግስትንና ህዝብን ማገዝ ነውና አንዱ አላማችሁ ጉዳዩን ፈትሻችሁ የደረሳችሁበትን ለትምህርታችን እንዲሆን አሳውቁን፡፡

ሰላም ሁኑ
ኢንጅነር ኃይለመስቀል ተፈራ
1.7K viewsENG Sintayehu Melese, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 09:52:03 እስኪ ትንሽ ስለቀለሙ የገንዘብ ወጭ!

ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ለ1,000,000 ህንፃዎች ቀለም እንቀይር ብልን
በአማካይ የቀለም ቅብ በካሬ ለአንድ ህንፃ 150m2 ቢሆን በጣም በትንሹ ማለቴ ነው።
ቀለም አሁን ባለው የአ.አ ዋጋ ለካሬ 120ብር ቢሆን
1,000,000x150x120 = 18,000,000,000 ብር ያስወጣል።
በዚህ የቀለም ስራ ተጠቃሚ ማህበረሰብ የለም። ግለሰቦች ይበለፅጉበታል።
ቀለም ቀቢ + የቀለም አምራች + ደላላ
አይይ የዚች ሃገር ነገር።

18 ቢሊዮን ብር አዲስ የቤት ግንባታ ወይም ለስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ቢፈጠርላቸው ወይም የኑኖ ውድነቱን ቢያረጋጉበት አይሻልም።

ቀለም ለድሃ ሆድ አይሞላም።

#እትዮ_ኮንስትራክሽን
1.8K viewsENG Sintayehu Melese, 06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ