Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.29K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2022-05-18 18:54:23 ለማንኛውም አዲስ አበባን ጨምሮ የኢትዮጵያ ከተሞች መለያቸው የሀገረሰብእ (Indigenous) ቅኝት የሚስተዋልባቸው ቅይጥ (Mixed) ጠባይ ያላቸው ናቸው።

እንደ ሞዛይክ ቅይጥ መልካቸውን በማጥፋት አንድን ከተማ "አንድ ዓይነት" ቀለም ለመቀባት መወሰን ፍጹም ስህተት ነው። ይህንን የመሰለ አስተሳሰብ እና አሠራር ምንጩ ግን ምን ይሆን ?

ሀ) አለማወቅ ?
ለ) አጀንዳ መስጠት ?

#ፕሮፐርቲ ታክስ:::::>ህንፃህን የመረጥከውን ቀለም መቀባት አትችልም(ግራጫ ቀባ)::::::>ቀጣዩን የንብረት መብት እጣፋንታ(ገምቱ)

ይጠቀሙ

@Ethiocon143bot

Good night
#ሲሚንቶ
1.6K viewsENG Sintayehu Melese, edited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 15:00:38 ስለግራጫ ቀለም ውሳኔ

ጌታሁን ሄራሞ እንደፃፈው

አዲስ አበባ "ግራጫ ትሁን" ተብሏል። ግራጫ፣ ነጭና ብርማ "ቀለሞች" ከኪነ ሕንፃ ታሪክ አኳያ ሞደርኒዝም ከናኘበት ከዛሬ 60 ዓመታት በፊት በብዙ ሀገራት ተሞክረው ቀለሞቹ በሰው ልጆች ሥነ ልቦናና አካል ላይ ከሚያስከትሉ ተፅዕኖ አንፃር በብቸኝነት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተደረጉ ናቸው። ሲጀመር እነዚህ በዘልማድ በቀለምነት ይፈረጁ እንጂ ቀለም-አልባ ዝሪያዎች(Achromatic) ናቸው።

ከሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖ አንፃር በተለይም ግራጫ ቀለም ሰፊ ቦታ ከተሰጠው ራስን የማጥፋት(Suicide commitment) ውሳኔን የሚያበረታታ "ቀለም" መሆኑ በብዙ ጥናቶች የተረጋገጠ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ግራጫ "ቀለም" ሲያይል ድባቴን(Depression) ፈጥሮ ሰዎች ከራሳቸው ወጣ ብለው እንዳይንሸራሸሩ የሚያደርገውን "Introvert" ሰብዕናን ማበረታቱ ነው። በተለይም በሌሎች የግልና ማህበረሰባዊ ችግሮች ለተወጠሩ ሰዎች(ለምሣሌ ኑሮ ውድነት፣ጦርነት) "Extrovert" እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው አካባቢ ነው መፈጠር ያለበት። ይህም መሠረታዊ የሁባሬን መርሆችን(Harmony principles) የተከተለ የቀለማት አጠቃቃም(Chromatic environment) ይተገበር ዘንድ ግድ ይላል። በተለያዩ ቀውሶች ለተከበበ ማህበረሰብ ድባቴን የሚፈጥሩ "ቀለሞችን" እንካችሁ ማለት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍን እንደመጥራት ይቆጠራል።

በነገራችን ላይ የአንድ ከተማ ቀለም ከመወሰኑ በፊት በከተማው ማስተር ፕላን ውስጥ ዕቅዱ መካተት አለበት። የአዲስአበባ ከተማ ማስተር ፕላን ደግሞ ቀለምን በተመለከተ የሚለው አንዳች የለውም። በማስተር ፕላኑ የሌለውን መርህ ለመተግበር መሞከር በራሱ አጠያያቂ ነው። አንዳንድ የአሜሪካ፣ የካናዳ፣የአውሮፓና የእስያ ከተሞች በማስተር ፕላናቸው ውስጥ "City Color Planning" ዲፓርትመንት አላቸው። በዲፓርትመንቱ ውስጥ የከለር አማካሪዎችና ኢንቫይሮመንታል ሳይኮሎጂስቶች፣ የከተማ ፕላነርስና አርክቴክቶች፣ ሠዓሊዎች፣ ግራፊክ ዲዛይነሮችና የታሪክ ባለሙያዎች ተካትተው በይነዲስፒሊናዊ በሆነ መልኩ የቀለም ፕላንግ ንድፍ ያወጣሉ። አንድ ሕንፃ ከመገንባቱ በፊት ልክ እንደ ግንባታ ፈቃዱ የቀለሙም ፈቃድ በቅድሚያ ዲዛይን ውስጥ ተካትቶ ይጠናና ውሳኔው ይሰጣል። ስለዚህም የትኛውም የከተማ ቀለም ከመወሰኑ በፊት ፕላንጉ በማስተር ፕላኑ መታቀፍ አለበት። ይህ ባልሆነበት የከተማን ቀለም መወሰን እንደ ሕገወጥ ግንባታ መቆጠር አለበት። አቅሙ ካለ ከሁሉም አስቀድሞ ማስተር ፕላኑ ውስጥ የከለር ፕላንግ መካተት አለበት። ይህ በኮሚቴ የሚወሰን ርዕሰ ጉዳይ አይደለም።

አንዳንዶቻችሁ በዚህ ሥራ ተሳታፊ ሆኜ የበኩሌን እንዳበረክት ስትጠይቁኝ ነበር። እስከአሁን ባለው መረጃ በግልፅ ከሚመለከታቸው የከተማ ኃላፊዎች በሥራው እንድሳተፍ የተደረገ ጥሪ የለም፣ በእርግጥ አንድ ወጣት አርክቴክት(በኮሚቴው ሳይኖር አይቀርም) በግል ጠይቆኛል። በእኔ አረዳድ ጥያቄው መቅረብ ያለበት ግን በግለሰቦች ሳይሆን ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች መሆን አለበት ባይ ነኝ። ብዙውን ጊዜ ደግሞ ውሳኔዎች በችኮለ ስለሚሰጡ እንደ እኛ ዓይነት ባለሙያዎች በውሳኔ አሰጣጡ ልናዘገይ ስለምንችል እንደ እንቅፋት ሳንቆጠር አንቀርም። መኪና ማርሽና ነዳጅ መስጫ ብቻ አይደለም ያለው። ፍሬን የሚባል መቆጣጠሪያም አለው። በአብዛኛው በፖለቲከኞች ዘንድ ፕሮፌሽናልስ እንደ "ፍሬን" ብቻ ነው የሚታዩት! ፍሬኑ ተገፍቶ በማርሽና በነዳጅ መስጫ ብቻ ምን እንደሚደርስና የት እንምንደርስ አብረን የምናያው ይሆናል::
ለሃሳብ እና ኣስተያየት ይጠቀሙ

@Ethiocon143bot

https://t.me/ethioengineers1
2.2K viewsENG Sintayehu Melese, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 15:00:38
#ይመዝገቡ #ይሰልጥኑ

የሲቪል ኢንጂነሪንግ፣አርክቴክቸር፣ ኮተምና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሶፍትዌርዎችን የትም ሆነው መማር ይችላሉ ከ ሰርተፊኬት ጋር፡
Megenagna
Marathon Building , 6th Floor, Office No 614


0911890392/ 0944186744

Join @BeGetEngineering
1.7K viewsENG Sintayehu Melese, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 15:00:38
~ የግንባታ ጨረታዎች፣
የግንባታ ዕቃዎችን ወቅታዊ ዋጋ፣

የባለሙያዎችን አድራሻ እና
ወቅታዊ መረጃዎችን post
ወደ ምናደርግበት channelችን ቀላቀሉ


https://t.me/conlinkcatalogue

https://t.me/conlinkcatalogue
332 viewsENG Sintayehu Melese, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 09:50:51 2/2

ግራጫ ቀለም ሲወሰን ሁሉም ሕንፃዎች ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ ቀለም ይኖራቸዋል ማለት እንዳልሆነ የሚናገሩት ኃላፊው፣ እስከ 30 የሚደርሱ በኮድ የሚለያዩ የግራጫ ቀለም ዓይነቶች እንዳሉና የሕንፃ ባለቤቶች ከእነዚህ ውስጥ መምረጥ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከግራጫ ቀለም ዓይነቶች ውስጥ የማይካተት ቀለም የተቀቡ ሕንፃዎች በሙሉ፣ ቀለማቸውን በግራጫ ቀለም አማራጮች እንደሚቀይሩ አስረድተዋል፡፡

ኃላፊው እንደሚናገሩት በከተማ ውስጥ ያሉት ሕንፃዎች ቀለም የተዘበራረቀ፣ እርስ በርስ የሚጋጭና ጎን ለጎን ባሉ ሕንፃዎች መካከል እንኳን ተቀራራቢነት የሌለው ነው፡፡ ከእዚህ በላይ ‹‹ለዓይን ዕይታና ለጤና ጉዳት ያላቸው›› መስታወቶችንና አልሙኒየሞችን የሚገጥሙ ባለ ሕንፃዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ አሠራር መቅረትና ወጥ በሆነ ስታንዳርድ መመራት እንዳለበት የሚገልጹት ስጦታው (ኢንጂነር)፣ አሁን ያለው አሠራር የከተማዋን የአፍሪካ መዲናነትንም ሆነ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ከተማነት የማይመጥን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሕንፃዎቻቸው የቀለም ስታንዳርድ ያበጁ ከተሞች እንዳሉ ጠቅሰው፣ የከተማ አስተዳደሩም ይህንን ልምድ በአዲስ አበባ ለመተግበር ማሰቡን አስረድተዋል፡፡

በፌዴራል ደረጃ የወጣው የሕንፃ አዋጅም ሆነ የከተማዋ የሕንፃ መመርያ የቀለም ስታንዳርድን ስለማያስቀምጡ፣ የከተማ አስተዳደሩ በ2010 ዓ.ም. የወጣውን የሕንፃ መመርያ ቁጥር 2/2010 በማሻሻል ረቂቁን ለከተማዋ ዓቃቤ ሕግ መላኩን ገልጸዋል፡፡ የሕንፃና የቀለም ስታንዳርድ መመርያው ላይ የተካተቱ አዲስ ሐሳቦች መሆናቸውን የተናገሩት ስጦታው (ኢንጂነር)፣ በየአንቀጾቹ ሌሎች ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ረቂቅ መመርያው ከፀደቀ በኋላ ቢሮው የሕንፃዎችን ቀለም መቆጣጠር ኃላፊነት እንደሚኖርበት፣ አዲስ ሕንፃ ገንቢዎችም ካሉት የግራጫ ቀለም አማራጮች ውስጥ የመረጡት ቀለም በቢሮው ፈቃድ ሳያገኝ መቀባት እንደማይችሉ አብራርተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለሕንፃዎች የወሰነውን የቀለም ስታንዳርድ በተመለከተ ካለፈው ሳምንት አንስቶ ትልልቅ ሕንፃዎች ካሏቸው ባለሀብቶች ጋር ውይይት ማድረግ የጀመረ ሲሆን፣ እስካሁን በቂርቆስና በልደታ ክፍላተ ከተሞች ውይይት ተደርጓል፡፡ እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ በተደረጉት ውይይቶች የሕንፃ ባለቤቶች ውሳኔውን በመደገፍ ለመተግበር ተስማምተዋል፡፡ በየአካባቢው ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ማኅበራት ጋርም ምክክር መጀመሩን፣ የሕንፃዎቹንና የጣርያዎቹን ቀለም ወደ የሚፈለገው ስታንዳርድ ለማምጣት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ ይህ ውይይት በሁሉም ክፍላተ ከተሞችና ወረዳዎች እንደሚቀጥልም አክለዋል፡፡

የከተማዋን ሕንፃዎች ቀለም ወደ ግራጫ ለመቀየር ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ያስረዱት ኃላፊው፣ እስካሁን ድረስ የሕንፃዎችን ቀለም ለመቀየር የተቀመጠ የጊዜ ገደብ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ እናደርጋለን፣ እስከ መቼ ድረስ ሊጨርሱ ይችላሉ የሚለውን አስበንና ጊዜ ሰጥተናቸው እንወስናለን፤›› ብለዋል፡፡

በመጪው ሁለትና ሦስት ወራት ግን በአንድ የተመረጠ አካባቢ የሚገኙ ሕንፃዎችን ቀለም ሙሉ ለሙሉ ወደ ግራጫ በመቀየር ሞዴል አካባቢ የማሳየት ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡ ሞዴል አካባቢው ሌሎች ክፍላተ ከተሞች ጭምር ያምራል አያምርም የሚለውን መጥተው ልምድ የሚወስዱበት፣ ይሳካል አይሳካም የሚለውንም የሚመለከቱበት እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

ይሁንና በከተማው ውስጥ የሚገኙ ስማቸው መለያ (ብራንድ) የሆኑ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ሕንፃቸውን በግራጫ ቀለም ለመቀየር እንደማይገደዱ ስጦታው (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡ የተለየ ቀለም ያለው መስታወት ወይም አልሙኒየም የተገጠመላቸው ሕንፃዎችን በተመለከተ፣ ‹‹እንዴት እናርመው የሚለውን ተወያይተን መፍትሔ እንፈልጋለን፤›› ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለከተማዋ ሕንፃዎች የቀለም ስታንዳርድ ተግባራዊ የማድረግን ሐሳብ ከሳምንታት በፊት በተደረገው የከተማ አስተዳደሩ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ አንስተው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለከተማ ካቢኔ አባላት መመርያ ካስተላለፉባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ስለሆነው የሕንፃዎች ቀለም ጉዳይ ሲናገሩ፣ የከተማዋ ሕንፃዎች ቀለም ወጥነት የሚጎድለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዓብይ (ዶ/ር)፣ ‹‹እያንዳንዱ ሕንፃ በተፈቀደለት የቀለም ዓይነት ነው እንጂ የሚቀባው፣ የእኔ ስለሆነ ቀለም ስላማረኝ ብሎ ሁላችንም የምናየውን ቀለም እንደፈለገ መቀባት አይችልም፤›› ካሉ በኋላ፣ የካቢኔ አባላት ሊመለከቱት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ተናግረው ነበ
ር፡፡

Reporter
2.5K viewsENG Sintayehu Melese, 06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 09:50:51
የአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን ተወሰነ
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማው ‹‹የተዘበራረቀ›› የሕንፃዎች ቀለም ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ለማውጣት ባደረገው ጥናት፣ ሁሉም ሕንፃዎች ቀለማቸው ግራጫ (ግሬይ) እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔውን አስመልክቶ የሕንፃ ባለቤት ከሆኑ የከተማዋ ባለሀብቶች ጋር ውይይት የጀመረ ሲሆን፣ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ባለ ጊዜ ውስጥ የውሳኔው ማሳያ የሚሆን ሞዴል አካባቢ ለማዘጋጀት አቅዷል፡፡

በከተማው ለሚገኙ ሕንፃዎች ቀለማቸው ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት ላለፈው አንድ ወር ጥናት ሲደረግ መቆየቱን ለሪፖርተር የተናገሩት የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አካለ (ኢንጂነር)፣ በጥናቱ አብዛኞቹ ሕንፃዎች ቀለማቸው ምን ዓይነት እንደሆነ የመለየት ሥራ እንደተከናወነ ገልጸዋል፡፡ እንደ እሳቸው ገለጻ፣ የከተማዋ ሕንፃዎች ተቆጥረው ቀለማቸው የተለየበት ጥናት አብዛኞቹ ሕንፃዎች ግራጫ ቀለም ያላቸው መሆኑን አመላክቷል፡፡ ቂርቆስ ክፍለ ከተማን ለማሳያነት የጠቀሱት ኃላፊው፣ በቂርቆስ ከ100 ሕንፃዎች ውስጥ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ ነው ብለዋል፡፡ ከእዚህ ውጪ ያሉት ቀለሞች አነስተኛ ቁጥር ያላቸውና የተለያዩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

‹‹መሬት ላይ የሌለ አዲስ ቀለም ብናስቀምጥ የተሠሩት ሁሉም ሕንፃዎች እንደ ገና [ቀለም] ሊቀይሩ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዋነኛው የትኛው ቀለም ነው የሚለውን ወስደን ቀሪዎቹ ሕንፃዎችና ወደፊትም የሚሠሩት በተመሳሳይ ግራጫ እንዲሆኑ ወስነናል፤›› ሲሉ ለከተማዋ ሕንፃዎች ግራጫ የተመረጠበትን ምክንያት አስረድተዋል፡፡

1/2
2.3K viewsENG Sintayehu Melese, 06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:45:36 #የኮንስትራክሽን ግብአቶች እንደ ሲሚንቶ እና ብረት ያሉት ዋጋቸው ከፍ እንዳለ ነው።
#መንግስትም ዝምታን መርጧል።
#እስቲ በችግሩ ዋና መንስኤና መፍትሄው ላይ ሀሳብ አስተያየት ስጡበት።

ለሃሳብ እና ኣስተያየት ይጠቀሙ

@Ethiocon143bot
3.1K viewsENG Sintayehu Melese, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:45:36
#ይመዝገቡ #ይሰልጥኑ

የሲቪል ኢንጂነሪንግ፣አርክቴክቸር፣ ኮተምና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሶፍትዌርዎችን የትም ሆነው መማር ይችላሉ ከ ሰርተፊኬት ጋር፡
Megenagna
Marathon Building , 6th Floor, Office No 614


0911890392/ 0944186744

Join @BeGetEngineering
2.8K viewsENG Sintayehu Melese, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 15:29:10
~ የግንባታ ጨረታዎች፣
የግንባታ ዕቃዎችን ወቅታዊ ዋጋ፣

የባለሙያዎችን አድራሻ እና
ወቅታዊ መረጃዎችን post
ወደ ምናደርግበት channelችን ቀላቀሉ


https://t.me/conlinkcatalogue

https://t.me/conlinkcatalogue
4.7K viewsENG Sintayehu Melese, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 18:21:52 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ ባሳለፍነው ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 6/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በተደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ….

በተለያዩ ተፈጥሯዊም ሆኑ ሰው ሰራሽ በሆኑ አደጋዎች ወይም ግጭቶች መነሻነት የሚደርሱ መጠነ-ሰፊ ኪሳራዎችን ተከትሎ ከሥራ ተቋራጮች በኩል የሚነሱ መልከ ብዙ ጥያቄዎች በምን መልኩ ይስተናገዳሉ?፤ "ቁስለኛው አልያም ራሱን በራሱ ያቆሰለው" የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ከድምር ስብራቱ በምን መልኩ ያገግማል?፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተለዋዋጭ የሆነው የግንባታ ግብዓቶች የዋጋ ንረት የዘርፉን የእድገት ጉዞ የኋሊት ያንደረድረው ይሆን? ወ.ዘ.ተ እየተባባልን፤ ከዕለቱ እንግዶቻችን አቶ መላኩ ታደሰ እና አቶ ጀማል አሊ ጋር እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር ተጨዋውተናል።

#ውድ_አድማጮች...
የዚህኑ ፕሮግራም ጥቅል ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡልን ዘንድ እየጋበዝን፤ በይደር ባቆየነው ተከታይ የውይይት ክፍል ዳግም እስግንገናኝ... አስተያየት፣ ጥቆማ እና ተያያዥ ጥያቄዎች ሲኖሯችሁ... በውሃልክ የቴሌግራም ገፃችሁ እንዲሁም በእጅ ስልክ ቁጥራችን 0941431700 ላይ መልዕክቶቻችሁን ብታደርሱን በአክብሮት እናስተናግዳለን።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ_መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
#ውሃልክ_ሚዲያ_እና_ኮሚዩኒኬሽን።
1.4K viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ