2022-06-21 20:18:45
ታክስ ግን ከየት ነው የሚሰበሰበው?
ሰሞኑን ግንባታ ለመጀመር ካሰበ ኮንትራክተር ወዳጄ ጋር መዋል ጀምሬ በውሎዬ የታዘብኩት የግንባታ እቃዎች ከመወደዱ ይልቅ ያሳሰበኝ የግብይቱ ሁኔታ ነው።
የኮንስትራክሽን ግብአቶች" ከደረሰኝ ውጪ ይገበያዩ " የሚልመመሪያ ወርዶ ይሆን? ያሰኛል።
ከግብይቶቹ መካከል
*** የቁፋሮ ማሽኖች ተከራይቶ ደረሰኝ የለም
*** እንጨት በ15,000 ገዝቶ ደረሰኝ የለም
*** አሸዋ በቢያጆ 23000 ብር ገዝቶ ደረሰኝ መጠየቅ አሸዋውን ያሳጣል
*** ሲሚንቶ በኩንታል 1300ብር ገዝተህ የቫት ደረሰኝ ከጠየቅክ መኖሩን እያየህ የለንም ይሉሀል
*** አናጢ እና የጉልበት ስራ በኮንትራት ተሰጥቷቸው የሰሩ ደረሰኝ አይሰጡም
*** መርካቶ ቆርቆሮ ሚስማር....ደረሰኝ ቢኖርም በቁጥሩና በትክክለኛው ዋጋ ማግኘት ፈተና ነው
*** ድንጋይ 9000 ብር በቢያጆ መጥቶ ተገልብጦ ደረሰኝ መጠየቅ ቀጣይ አቅራቢ ያሳጣል
*** ከአንድ ቦታ ወደ ግንባታው ሳይት በሺዎች ተከፍሎ እቃ ተጭኖ ለተወሰደበት ደረሰኝ ስሙም የለ( ድርጅቶችም መጠቀም የሚችሏቸውን ለእንደዚህ ደረሰኞች ሲጠቀሙበት አላየሁም)
*** የተመረጠ አፈር ገዝተህ ደረሰኝ ከጠየቅክ "አፈር ነህና አፈር ትበላለህ" የሚል አካል ሊገጥምህ ይችላል
ብቻ በጣም አሳሳቢና አሳዛኝ ነው።
እኔ ያዘንኩት በዋጋ ግሽበት እየተሳቀቁ በኪሳራ ለሚሰሩ ኮንትራክተር ወገኖቼ ብቻ ሳይሆን ለሀገሬ እና ለወገኔ ጭምር ነው።
ሀገራችን የምትሰበስበው ግብር ከዓመት ወደ ዓመት እድገት አሳይቷል ቢባልም ከሌሎች እኩያ ሀገሮች ጋር ሲወዳደር ሊሰበሰብ ከሚቻለው ከግማሽ በታች ነው።
በተለይ ብዙ ሀብት በሚንቀሳቀስበት በግንባታው ዘርፍ የታክስ ስርዓት በደንብ አለመተከሉ ፣ ያለውም አለመተግበሩ ፣ ክትትል ማነሱም ጭምር..... ሀገራችን ልታገኘው የምትችለውን እያሳጣት ነው።
ከሻይ ቤት እና መሰል አነስተኛ ቢዝነሶች... ከሰራተኞች የስራ ግብር የሚሰበሰበው የት ያደርሰናል?
ይሄ ከታክስ ውጪ የሚሰበሰበው ሀብት ወዴት ነው የሚሄደው?
በዚህ ከቀጠልን ግን ግንባታ ስራ መቆሙ አይቀሬ ነው።የኮንትራክተሮች ማህበር ግን አለ???? ነፍሱን ይማርልን።
Desalegn Kebede
ለሃሳብ እና ኣስተያየት ይጠቀሙ
@Ethiocon143bot
#እትዮ_ኮንስትራክሽን
2.7K viewsGojobridge, edited 17:18