Get Mystery Box with random crypto!

Ethio telecom

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_telecom
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346.45K
የሰርጥ መግለጫ

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-26 18:24:46

22.3K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 13:11:49
ምርትና አገልግሎትዎን ከ44 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ባሉት ቴሌብር ላይ ተደራሽ ለማድረግ እና የድርጅትዎን ሲስተም በቀላሉ ለማስተሳሰር የቅድመ ትግበራ ፍተሻ የሚያደርጉበት የዴቨሎፐርስ ፖርታል ተግባራዊ ማድረጋችንን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው!

የዴቨሎፐርስ ፖርታሉን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን https://developer.ethiotelecom.et ይጠቀሙ!

ቴሌብር-ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
24.6K viewsedited  10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 10:06:52
ሚያዝያን ለመቄዶንያ!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ አረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከል እንለግሳለን!

እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን |
ዩትዩብ | ቲክቶክ |

ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!

#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
25.4K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 20:05:02
የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከላት መጀመሩን በይፋ ማብሰራችንን በማስከተል ምዝገባ በተጀመረባቸው ማዕከላት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ተገኝተው አተገባበሩን ተመልክተዋል።

በዚህም ወቅት ለምዝገባው አስፈላጊ ግብአቶች መሟላታቸው እና የምዝገባ አገልግሎቱ በላቀ ፍጥነት መስጠት መቻሉን በተግባር መመልከት ችለዋል፡፡

አገልግሎቱ በሌሎች ተጨማሪ ማዕከላት የሚስፋፋ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ተገልጋዮች ስለዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ እንዲረዱ የማድረግ ሥራ በስፋት እንደሚከናወን ተነግሯል።

ዜጎች በአቅራቢያቸው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንበትን የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከል ለማወቅ ቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ውስጥ የተካተተውን አዲስ የአቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ ዳታ በማብራት ብቻ በነጻ መጠቀም ይችላሉ።

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #NIDP
13.4K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 20:50:13
ኩባንያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በይፋ አስጀመረ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያን ለማዳረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ኩባንያችን በወር በአማካይ 1 ሚሊዮን ዜጎችን በመመዝገብ ለ32 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ በማድረግ የሀገራዊ ዕቅዱን 36% ለማከናወን የአገልግሎት ማዕከላትን በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን ስራውን ያስጀመረ ሲሆን በሌሎች ከተሞችም አገልግሎቱን ይቀጥላል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ዕውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ የዲጂታል መታወቂያ አንዱ ሲሆን ለአካታች የዲጂታል ማህበራዊና ኢኮኖሚ ግንባታ፣ ለቢዝነስ ትስስር፣ ለኢ-ጋቨርመንት፣ በዳታ ለሚመራ የኢኮኖሚ ሥርአት፣ ለቀልጣፋ አገልግሎት፣ ለተሻለ የዜጎች ህይወት እንዲሁም የሳይበር ማጭበርበርን ለመከላከል ካለው የላቀ ሀገራዊ ሚና በተጨማሪ ለላቀ የደንበኞች ተሞክሮ፣ ለሥራ ፈጠራ፣ ለኢ-ኮሜርስ፣ የፋይናንስ አካታችነት የሚጨምሩ የማይክሮ ብድር አገልግሎቶች ለማቅረብ፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡

ኩባንያችን የዲጂታል መታወቂያ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአገልግሎት ማዕከላት፣ የፍራንቻይዝ ማዕከላት፣ ወኪሎች እንዲሁም የገነባውን ግዙፍ የዳታ ሴንተር፣ ክላውድ ሰርቪስ እና የዲጂታል መሰረተ ልማት አስቻይ ሁኔታ እንደሚፈጥሩለት ታሳቢ ተደርጓል፡፡

ምዝገባ የሚደረግባቸውን ማዕከላት ለመመልከት ቴሌብር ሱፐርአፕን http://onelink.to/fpgu4m ወይም ድረ-ገጻችንን www.ethiotelecom.et ይጎብኙ
ለተጨማሪ https://bit.ly/3QfPuVg
25.7K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 09:52:46
ባሉበት ቦታ ሆነው በርካታ ክፍያዎችን በአንድ መተግበሪያ መፈጸም የሚያስችልዎትን ቴሌብር ሱፐርአፕን http://onelink.to/fpgu4m አውርደው ኑሮዎን ያቅልሉ!

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
27.8K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 19:40:17
በጥሪ መለያ አገልግሎታችን ጥሪ ሲያደርጉ ወይም ሲቀበሉ ለደዋዩ በሚደርስ አጭር ጽሁፍ መልዕክትዎን ይግለጹ!

ለዕለታዊ *623*1*1# ወይም ለሳምንታዊ *623*1*2# በመደወል ይመዝገቡ።
የጥሪ መለያ ይዘትዎን ለመቀየር ከፈለጉ መልዕክቱን አዘጋጅተው ወደ 623 በነፃ መላክ ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ ፡ https://bit.ly/48fkpHT

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
27.5K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 18:23:08
በቴሌብር ኢንጌጅ ቡድን ፈጥረው በነጻ የልብ የልብዎን ያውጉ!

ከግብይት፣ ገንዘብ እና የአየር ሰዓት መላላክ ባሻገር፣ ማህበራዊ ግንኙነትዎን የሚያጠናክሩበት በርካታ አዝናኝ ገጽታዎች ያከተተውን ቴሌብር ሱፐርአፕ አውርደው ዘመናዊውን አለም ይቀላቀሉ!

መተግበሪያውን ለማዘመን ወይም ለመጫን http://onelink.to/fpgu4m ይጠቀሙ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
25.4K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 12:48:08
ቀጣዩ ሚሊየነር እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ!

በ22 ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ4 ሚሊየን ብር እና ሌሎችም ሽልማቶች እድለኛ ለመሆን በቴሌብር ወይም ወደ 605 A ብለው በመላክ በ 10 ብር አሁኑኑ ይቁረጡ!

እድል ከእርስዎ ጋር ትሁን!

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር እና ኢትዮ ቴሌኮም በአጋርነት

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
19.2K views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 09:29:55

23.2K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ