Get Mystery Box with random crypto!

ኩባንያችን አዲስና አካታች የዲጂታል ስነምህዳር ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ምርትና አገልግሎታቸው | Ethio telecom

ኩባንያችን አዲስና አካታች የዲጂታል ስነምህዳር ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ምርትና አገልግሎታቸውን በአጭር ጊዜ Time To Market (TTM) ተደራሽ ለማድረግ የሚፈልጉ አጋር ድርጅቶች ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር ሲስተሞቻቸውን በፍጥነት ለማስተሳሰር (to integrate) የሲስተም ሙከራ የሚያከናውኑበት የዴቨሎፐርስ ፖርታል አዘጋጅቶ በይፋ አስጀመረ፡፡

የዴቨሎፐርስ ፖርታሉ በዋነኛነት የአጋር ድርጅቶች ሲስተም ወደ ዋናው ቴሌብር ሲስተም ከመተሳሰሩ በፊት በተለየ የሙከራ ቦታ ላይ (sandbox environment) የኢንተግሬሽን ሙከራ ለማከናወን ያስችላል፡፡ አገልግሎቱ ከሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት፣ የሲስተም መፈተሻ እና የትግበራ ቦታ በተጨማሪ ለዴቨሎፐሮች ዶክመንቴሽኖች፣ መመሪያዎች፣ የቪዲዮ ቱቶሪያሎች፣ የኮድ ናሙናዎች፣ የኤፒአይ ማጣቀሻዎች እና ሌሎች አጋዥ መርጃ መሳሪያዎች ያካተተ ነው፡፡

ፖርታሉ ዴቨሎፐሮች ከኩባንያችን ሲስተሞች ጋር በፍጥነት እንዲላመዱ እና ክህሎት በመጋራት ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች እንዲያፈልቁ ከማስቻሉ በተጨማሪ የኦንላይን ማህበረሰብ በመፍጠር የስነምህዳሩን ተደራሽነት ይጨምራል ብለን እናምናለን፡፡

የዴቨሎፐርስ ፖርታሉን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን https://developer.ethiotelecom.et ይጠቀሙ!

#telebirrEngage #telebirr #Ethiotelecom #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Huawei #GSMA #ITU