Get Mystery Box with random crypto!

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት የዲጂታል ሕይወትን በማቅለል እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ መከወን በሚያ | Ethio telecom

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት የዲጂታል ሕይወትን በማቅለል እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ መከወን በሚያስችለው ቴሌብር ሱፐርአፕ ደንበኞች ከመገበያየት እና ገንዘብ ከማስተላለፍ ባሻገር መረጃን በነጻ በመለዋወጥ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እና ቢዝነሳቸውን የሚያጠናክሩበት ቴሌብር ኢንጌጅ የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ፡፡

አዲሱ ቴሌብር ኢንጌጅ የቢዝነስ እና ግለሰብ ደንበኞች ያለምንም ተጨማሪ የኢንተርኔት ክፍያ ለተናጠል ወይም ለጋራ የጽሁፍ፣ የፎቶ፣ ድምጽ፣ ቪዲዮ እና ፋይሎችን ለማጋራት የሚያስችል ሲሆን ከዚህም ባሻገር ለበዓል ወይም ለተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች የተናጠል ወይም የቡድን መልካም ምኞት መልእክት ከገንዘብ ስጦታ ጋር መላክ የሚያስችላቸውን አዲስ ገጽታ አካቷል፡፡ በተጨማሪም በጭውውቶች ወቅት ገንዘብ ለመጠየቅ፣ ለመላክ እና ለመቀበል፣ ቢል ለማጋራት እንዲሁም ጥቅል ወይም የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ በርካታ የዲጂታል አገልግሎቶችን በአንድ መተግበሪያ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡

ኩባንያችን ለክቡራን ደንበኞቹ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮችን በማስተዋወቅ የቢዝነስ ተሞክሮአቸው እና የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ ተጨማሪ ምቾት እና ቅልጥፍና በመጨመር ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን https://bit.ly/3W3291x ይጠቀሙ፡፡

#telebirrEngage
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia