Get Mystery Box with random crypto!

Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_muslim_nashida — Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_muslim_nashida — Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_muslim_nashida
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.43K
የሰርጥ መግለጫ

ሀሳብ አስተያየት ☞ @To_The_One

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2022-05-05 15:52:03 ़ ታላቋ ሴት ़
ुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुु
.
ከዕለታት በአንዱ ቀን ነብያችን ﷺ ታላላቅ ከሚባሉት የአንሷርና የሙሃጂር ሰሃቦች ጋር መስጂድ ውስጥ ተቀማምጠው ሳለ አንዲት ሴት ድንገት በሩ ላይ ብቅ አለች ፡፡ በቀጥታም ነብያችን ﷺ ወደተቀመጡበት አምርታ ከፊት ለፊታቸው ቆመችና ሃያዕ በተጫነው ድባብ ‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እኔ ዝሙት ፈፅሜያለሁ አንፁኝ ›› አለቻቸው ፡፡
ይህን እንደሰሙ ነብያችን ﷺ ፊታቸው ደም የሚያዘንብ እስኪመስል ቀላ ፡፡ ከዛ ፊታቸውን ወደ ቀኝ አዞሩ ምንም ያልሰሙ መስለውም ዝም አሉ ፡፡ ሴትየዋ ከንግግሯ ትመለስ ዘንድም ከጀሉ ፡፡
ነገር ግን ይቺ ኢማን በደም ስሯ የሰረፀ ታላቅ እንስት ...‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ማዒዝ ኢብን ማሊክን እንደመለሱት ሊመልሱኝ ይፈልጋሉን ( ? ) በአላህ ይሁንብኝ እኔ ከዚና አርግዤያለሁ ››... አለቻቸው ፡፡ ነብያችን ﷺ ይህንን አስደንጋጭ ዜና ሲሰሙ ..‹‹ እስክትወልጂው ድረስ ሂጂ ››.. ብለው ሸኟት ፡፡ እርሷም ውሳኔዋን ተቀብላ ወደመጣችበት ተመለሰች ፡ እስክትወልደውም በትዕግስት ፣ በፀፀትና በሀዘን ጠበቀች ፡፡ እንደወለደችውም በቀናቶች እድሜ ያለውን ልጇን ታቅፋ ወደ ነብያችን ﷺ በመምጣት ..‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አንፁኝ ››.. አለቻቸው ፡፡
የዚህኔ የእዝነቱ ነብይ ﷺ ወደ ህፃኑ በሀዘንና ትካዜ ከተመለከቱ በኀላ ይቺ ሴት ላይ ቅጣቱን ተፈፃሚ ካደረግን ይህንን ህፃን ማን ያጠባዋል ' ማንስ ይንከባከበዋል ብለው አሰቡና ..‹‹ ተመልሰሽ ....... አጥቢውና ጡት ሲጥል ነይ ››.. ብለው ሸኟት ፡፡ ልክ እንደ ቀደመው ጊዜ አሁንም ወደመጣችበት ተመለሰች ፡፡ ከዚያም ልጇ ጡት እስኪጥል አጠባችው ፡፡ ይህንን ካደረገች በኀላም በቀጠሮዋ መሰረት ልጇን ዳቦ አስይዛ ነብያችን ﷺ ዘንድ መጣች ፡፡ ከዚያም ..‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይኸው ( ልጄ ) ጡት ጥሏል አንፁኝ ››.. አለቻቸው ፡፡
የዚህኔም ሆደ ባሻ የሆኑት ነብያችንም ﷺ ልጇን ተቀበሏትና ..‹‹ ይህንን ልጅ የሚያሳድግ በጀነት ከኔ ጋር ይሆናል ››.. አሉ ፡፡ ይህንን ሲናገሩ ከአንሷሮች መሃል አንዱ እኔ አሳድገዋለሁ አለ ፡፡

በመቀጠልም እስከ ደረቷ ተቀብራ በድንጋይ እንድትቀጠቀጥ ተደረገ ፡፡ ከሞተች በኀላም የፍጥረተ ዐለሙ ምርጥ ነብያችን ﷺ ሰገዱባት ፡፡
የዚህኔ ታላቁ ሰሃባ ዑመር ( ረዲየ ' ሏሁ ዐንሁ ) ..‹‹ አንቱ የአላህ ነብይ ሆይ ዚና ሰርታ ይሰግዱባታልን ( ? ) ››.. አላቸው ፡፡
እሳቸውም ﷺ ..‹‹ በእርግጥ ( ይቺ ሴት ) ሰባ ለሚሆኑ የመዲና ሰዎች ቢከፋፈል የሚበቃን ተውባ ቶብታለች ››.. በማለት መለሱለት ፡፡

@ethio_Muslim_Nashida
10.8K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍu, 12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 15:15:22 Watch "አዲስ ነሺዳ አብዱሰላም አበራ እና ፉኣድ መልካ ||" on YouTube


9.0K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍu, 12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 14:29:25 ።።። #ያልተጠበቀው_የሌባው_ፍፃሜ ።።።
-
-
በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ለፈጣሪው ፀሎት ለማድረስ ራቅ ወዳለ ስፍራ ይሄዳል ፣
በዚህም ወቅት ወደ ፀሎት ቦታ የሚሄዱት ተሳፋሪዎች በጉዞ መሀል ምሳ ለመብላት ወደ አንድ ካፌ ይወርዳሉ ።
ወጣቱም ከነሱ ጋር አብሮ በመውረድ ምግብ አዞ መመገብ ይጀምራል ።
ተመግቦም ከጨረሰ በኃላ ሂሳብ ለመክፈል ወደ ኪሱ ሲገባ ዋሌቱን ያጣዋል
ለ ሆቴሉ ማናጀርም ዋሌቱ እና ብሩ በሌባ መሰረቁን ያስረዳዋል ፣
ከዛም ከተማ ላለው ጓደኛው ደዉሎ የሆነውን ይነግረዋል ።
ጓደኛውም ገንዘብ ይልክለትና አመስግኖ ሂሳቡን ከፍሎ ሲወጣ ባሱ ስለቆየበት ጥሎት ይሄዳል ።
ከዛም በጣም አዝኖ ወደ ጓደኛው ዘመድ ቤት ያቀናል፣
እነሱም ጋር ለ 2 ቀን አድሮ ወደ ፀሎት ቦታው እንዲሸኙት ይጠይቃቸዋል ፣
እነሱም ያሳፍሩታል! ፀሎት ቦታውም ጋር ለ 2 ቀን አድሮ ወደ ቤቱ ወዳጁ ያሳፍረዋል ፣


ወደ ቤቱም ሲገባ እያለቀሱ ከቤቱ የሚወጡ ሰዎችን ይመለከታል ።
ከዛም ፈጠን ብሎ ወደ ቤት ሲገባ ሰዎቹ እንዳለ በፍርሀት እና ድንጋጤ ይጮሀሉ።
እሱም ማን እንደሞተ እያለቀሰ ይጠይቃቸዋል ፣ ከጎረቤቱም አንዱ ጠጋ ይልና << አንተን ያሳፈርንህ ባስ መንገድ ላይ ተገልብጦ ማንም የተረፈ ሰው የለም> > ይለዋል ፣
ወጣቱም ስላጋጠመው ችግር በሰከነ መልኩ ያስረዳቸዋል ።
በአደጋውም ከባድነት የሰዎች መልክ ባለመለየቱ ያንተን ዋሌት በኪሱ ይዞ ስናይ አንተ መስለከን ከቀበርነው ዛሬ 4ኛ ቀናችን ነው ይለዋል
ለካ በወጣቱ ቦታ የተሳፈረው የወጣቱነደ ዋሌት የሰረቀው ሰው ነበር

<<በምድር ላይ የሚያጋጥመን ነገር ቢከብደንም አላህ ሁሉንም ነገር የሚያደርገው ለኸየር ነው >>

#አብዱሰላም

Share & Support Us .
10.2K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍᴏ, 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 18:54:37
እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አልፈጥር በኣል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ያሳለፍነውን 30 ቀናት የረመዳን ፆምችንን እና ኢባዳ አላህ ይቀበለን

በድጋሚ ኢድ ሙባረክ
#share

•••••••••••••••••••••••••••••••
@ethio_muslim_nashida
@ethio_muslim_nashida
11.7K views卄卂乃丨乃ㄩ卂 ✮ًٍٜ۪۪͜͡༒ًٍٰٰٰٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃, edited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 15:47:23 በየቀኑ ባነበውም በየቀኑ ይገርመኛል
.
ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዘንድ አንድ
ከገጠርየመጣ ኑሮው ያልሰመረለት (ድሃ) ግለሰብ ሰሃን
ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል፡፡ነቢዩም ሰ.ዐ.ወ
ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት
ጀመሩ..የመጀሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ..ሁለተኛውንም
ጎርሰው ፈገግ አሉ..ግለሰቡም እጅጉን ተደሰተ..የነቢዩ
ጓዶች (ሰሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ስጦታ
ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን
እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ..የአላህ መልእክተኛ
ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና
ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ.. ስጦታ አቅራቢው
እጅግ በጣም ተደሰቶ..ስጦታውንም ስለወደዱለት
አመስግኖ ሄደ..አንድ የነቢይ
ሰ.ዐ.ወ ጓድ (ሰሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው
‹‹የአላህ መልእከተኛ ሆይ..ምነው ሳያካፍሉን?››
እሳቸውም ሰ.ዐ.ወ
ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሱቱን አይታችኋል
አይደል?!..
ወይኑን ስቀምሰው በጣም ይመር ነበር..ባካፍላችሁ
አንዳችሁ
ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር
እንዳታሳዩት ብየ ስለሰጋሁ ነው ብለው መለሱላቸው።
ሀቢቢ የኔ ነቢይ እናቴም አባቴም ህይወቴም ፊዳ ይሁንሎት።

አስተማሪ ይሆን ዘንድ ሼር ይደረግ

@ethio_muslim_nashida
@ethio_muslim_nashida
10.4K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍᴏ, 12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 11:53:03 ​​#አንዲት_ገራሚ_ቂሷ

#ነብዩ በሂወት በነበሩበት ወቅት
አንድ ለማኝ ወደ ቤታቸው ይመጣል…
#ከዛም አንድ ልብስ
ስጡኝ በማለት ሲጠይቃቸው
አዛኙ ነብይ አኢሻን አንሺና
አንዱን ስጪው ይሏታል…
#አኢሻም አንድ ልብስ ታነሳና
እንካ ስትለው ይህን አልፈልግም
ይላታል እሷም ቀይራ ሌላ
ልብስ እንካ አለችው እሱም
ይህንንም አልቀበልም ይላታል
አሁንም ሶስተኛ ሌላ ልብስ
እንካ ስትለው ይህንም
አልፈልግም ይላታል…

#በመጨረሻም አኢሻ እና የቱን ነው የምትፈልገው ስትለው
እሱም ነብዩ ትናንትና
ለብሰውት የነበረውን ቀሚስ
(ጀላብያ) ነው የምፈልገው ሲላት…

#አኢሻም እሱንማ ነብዩ
በጣም ስለሚወዱት አልሰጥህም
ስትለው ነብዩ ሰሟትና ስጪው
ሲሏት አንስታ ስትሰጠው
ተቀብሎ ሄደና…

#ገቢያ ቦታ ይዞት ወጣና
ከፍ ባለ ድምፅ ማን ነው የነብዩ
ሙሀመድን ልብስ መግዛት
የሚፈልግ በማለት መጣራት
ጀመረ…

#በግዜውም አንድ አይኑ የጠፍ
ሰው ነበር ይህም ሰውዬ የነብዩ
ሙሀመድ ልብስ ገቢያ
መውጣቱን ሲሰማ ባሪያ
ነበረውና ባሪያውን እንዲህ
አለው……
#የነብዩ ሙሀመድ ልብስ
ገቢያ ወጥቷልና እሱ
በሚጠራበት ዋጋ ቢያስወድደውም እንኳን ገዝተህ
ካመጣህልኝ ነፃ አወጣሀሉ ይለዋል…
#ባሪያውም በፍጥነት ገቢያ
ቦታ ሂዶ ልብሱን በጣም በውድ
ዋጋ ገዝቶት ተመልሶ
ለአሳዳሪው ይሰጠዋል
የሸጠውም ሰውዬ ከበረ…

#ልብሱን አምቶ ለአሳዳሪው
ሲሰጠው ቃል ስለገባለት ባሪያውን ነፃ አወጣው…
#ሰውዬውም የነብዩን ልብስ በእጁ ያዘና እንዲህ ሲል ዱኣ
አደረገ "ያ አሏህ የነብዩሏህ
የእቁብን አይን በነብዩሏህ ዩሱፍ
ልብስ አማካኝነት
እንዳበራህላች ሁሉ የኔንም
በነብዩ ሙሀመድ ልብስ
ይሁንብህ አብራልኝ ብሎ
ፊቱን ሲያብስበት አይኑ
በራለት ከዛ…
#የነብዩ ሙሀመድን ልብስ ይዞ
ሰውዬው ወደ ነብያችን ሄደና
ሀድያ ብሎ ያንን ልብስ
ሲሰጣቸው ነብዩን ከየት
አገኘህው ሲሉ ጠየቁት…
#እሱም ይቺ ልብሳቹህማ
ድሃ የነበረን ሰው አክብራ ባሪያን
ሁር አስብላ (ነፃ አስወጥታ)
አይኑ የጠፍን አይኑን አብርታ
ይሄው ተመልሳ መጣችላቹህ
አላቸው…
#ከዛም ነብዩ ወደ አኢሻ
ዞሩና አየሽ አይደል በመስጠትሽ
አማካኝነት ይህ ሁሉ ሰው
ተጠቀመ አሏት።

ሀቢቡና ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም
@ethio_muslim_nashida
12.5K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍᴏ, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 19:40:06 መዲና ውስጥ አንዲት ሴት ትሞትና ጀናዛዋ መታጠብ ይጀምራል በድንገት የአጣቢዋ ሴት እጅ ከጀናዛው ብልት ጋር ተጣብቆ አልላቀቅም አለ መዲና ውስጥ ያሉ ኡለማዎች የአጣቢዋ እጅ ይቆረጥ ወይስ የጀናዛው ብልት በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገቡ በዚህ ጊዜ ነበር ለእንግድነት ለመጡት ኢማሙ ማሊክ ይህ ጥያቄ የቀረበው እሳቸውም ወደ አጣቢዋ በመዞር《 እያጠብሽ ሳለ በመሀል የተናገርሽው ነገር አለ?》ሲሉ ጥያቄን አቀረቡላት እሷም《 አዎ እያጠብኩ ብልቷ አካባቢ ስደርስ ይሄ ዝሙተኛ ብልት ብዬ ተሳደብኩ እጄም ተጣብቆ ቀረ》 በማለት መለሰች እሳቸውም በሉ በዚህ ጀናዛ ላይ አላግባብ ቀጥፋለችና ሰማንያ ጅራፍ ትገረፍ ሲሉ አዘዙ እየተገረፈች ሰማንያኛው ላይ ግርፊያ ላይ ሲደርሱ ተጣብቆ የነበረው እጇ ለቀቀ
《 ኢማሙ ማሊክ በህይወት እያሉ ማንም ፈትዋ እንዳይሰጥ》 ተብሎ መዲና ውስጥ ታወጀ ።

《የሰው ልጅ ሆይ!ምላስህን ጠብቅ እባብ ነውና እንዳይነድፍህ ።》
ኢማሙ ሻፊኢ

⇒ይህን ታሪክ ስትፈልጉ የነበራቹ ይሄው አቀረብነው
ሼር ያድርጉ ላላነበበው

@ethio_muslim_nashida
10.7K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍᴏ, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 16:09:24
አንዋር መስጅድ
# የጎንደርጭፍጨፋ
# ሙስሊሞችጥቃት
# GondarMassacre
# MuslimsUnderAttack
# GondarCityofHorror
#ሼር ለወዳጅ ዘመድ ያዳርሱ

https://t.me/ethio_muslim_nashida
11.8K views卄卂乃丨乃ㄩ卂 ✮ًٍٜ۪۪͜͡༒ًٍٰٰٰٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃, edited  13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 12:21:23
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
10.8K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍᴏ, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 12:21:15
10.4K viewsᴀʙᴅᴜsᴇʟᴀᴍ ᴍᴏ, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ