Get Mystery Box with random crypto!

़ ታላቋ ሴት ़ ुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुु . ከዕለታት በአን | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

़ ታላቋ ሴት ़
ुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुुु
.
ከዕለታት በአንዱ ቀን ነብያችን ﷺ ታላላቅ ከሚባሉት የአንሷርና የሙሃጂር ሰሃቦች ጋር መስጂድ ውስጥ ተቀማምጠው ሳለ አንዲት ሴት ድንገት በሩ ላይ ብቅ አለች ፡፡ በቀጥታም ነብያችን ﷺ ወደተቀመጡበት አምርታ ከፊት ለፊታቸው ቆመችና ሃያዕ በተጫነው ድባብ ‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እኔ ዝሙት ፈፅሜያለሁ አንፁኝ ›› አለቻቸው ፡፡
ይህን እንደሰሙ ነብያችን ﷺ ፊታቸው ደም የሚያዘንብ እስኪመስል ቀላ ፡፡ ከዛ ፊታቸውን ወደ ቀኝ አዞሩ ምንም ያልሰሙ መስለውም ዝም አሉ ፡፡ ሴትየዋ ከንግግሯ ትመለስ ዘንድም ከጀሉ ፡፡
ነገር ግን ይቺ ኢማን በደም ስሯ የሰረፀ ታላቅ እንስት ...‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ማዒዝ ኢብን ማሊክን እንደመለሱት ሊመልሱኝ ይፈልጋሉን ( ? ) በአላህ ይሁንብኝ እኔ ከዚና አርግዤያለሁ ››... አለቻቸው ፡፡ ነብያችን ﷺ ይህንን አስደንጋጭ ዜና ሲሰሙ ..‹‹ እስክትወልጂው ድረስ ሂጂ ››.. ብለው ሸኟት ፡፡ እርሷም ውሳኔዋን ተቀብላ ወደመጣችበት ተመለሰች ፡ እስክትወልደውም በትዕግስት ፣ በፀፀትና በሀዘን ጠበቀች ፡፡ እንደወለደችውም በቀናቶች እድሜ ያለውን ልጇን ታቅፋ ወደ ነብያችን ﷺ በመምጣት ..‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አንፁኝ ››.. አለቻቸው ፡፡
የዚህኔ የእዝነቱ ነብይ ﷺ ወደ ህፃኑ በሀዘንና ትካዜ ከተመለከቱ በኀላ ይቺ ሴት ላይ ቅጣቱን ተፈፃሚ ካደረግን ይህንን ህፃን ማን ያጠባዋል ' ማንስ ይንከባከበዋል ብለው አሰቡና ..‹‹ ተመልሰሽ ....... አጥቢውና ጡት ሲጥል ነይ ››.. ብለው ሸኟት ፡፡ ልክ እንደ ቀደመው ጊዜ አሁንም ወደመጣችበት ተመለሰች ፡፡ ከዚያም ልጇ ጡት እስኪጥል አጠባችው ፡፡ ይህንን ካደረገች በኀላም በቀጠሮዋ መሰረት ልጇን ዳቦ አስይዛ ነብያችን ﷺ ዘንድ መጣች ፡፡ ከዚያም ..‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይኸው ( ልጄ ) ጡት ጥሏል አንፁኝ ››.. አለቻቸው ፡፡
የዚህኔም ሆደ ባሻ የሆኑት ነብያችንም ﷺ ልጇን ተቀበሏትና ..‹‹ ይህንን ልጅ የሚያሳድግ በጀነት ከኔ ጋር ይሆናል ››.. አሉ ፡፡ ይህንን ሲናገሩ ከአንሷሮች መሃል አንዱ እኔ አሳድገዋለሁ አለ ፡፡

በመቀጠልም እስከ ደረቷ ተቀብራ በድንጋይ እንድትቀጠቀጥ ተደረገ ፡፡ ከሞተች በኀላም የፍጥረተ ዐለሙ ምርጥ ነብያችን ﷺ ሰገዱባት ፡፡
የዚህኔ ታላቁ ሰሃባ ዑመር ( ረዲየ ' ሏሁ ዐንሁ ) ..‹‹ አንቱ የአላህ ነብይ ሆይ ዚና ሰርታ ይሰግዱባታልን ( ? ) ››.. አላቸው ፡፡
እሳቸውም ﷺ ..‹‹ በእርግጥ ( ይቺ ሴት ) ሰባ ለሚሆኑ የመዲና ሰዎች ቢከፋፈል የሚበቃን ተውባ ቶብታለች ››.. በማለት መለሱለት ፡፡

@ethio_Muslim_Nashida