Get Mystery Box with random crypto!

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድ ወንድሞች በዚ ጊዜ እንደ አጠቃላይ ሙስሊ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ ወንድሞች በዚ ጊዜ እንደ አጠቃላይ ሙስሊሙ ላይ ፈተና በበዛበት መስጂዳችን ላይም ጠንካራ ትግል በሚጠበቅበት ሰዓት ብዙዎቻችን ከሱብህ ጀመዓ ተዘናግተን እየተስተዋልን ነው።

አረ አላህን እንፍራ !!!!

የጀመዓው አይን ተደርገን የምንቆጠረው ሳንቀር መስጂዱን ጭር አድርገነዋልኮ።

ነፍስያችንን ማሸነፍ ሳንችል በየትኛው አቅማችን ነው ውስጣዊና ውጫዊ የዲን ጠላቶችን ልናሸንፍ የምንፍጨረጨረው? ወሬ ብቻኮ ስራ ከሌለው የትም አያደርስም።

ተሀጁድ ላይ ፊት ፊት ሆነን ስናሽቃብጥ የነበርነው ሱብህ ላይ ከኋላ እንኳን መታየት ካልቻልን ሌላው ሰው ከኛ ምንድነው የሚማረው? ያ አህባቢ በእንዲህ አይነት ድክመት ሸይጣን ሽባ ካደረገን ምንም አይነት ዳገት መወጣጣት አንችልም።

ነቃ እንበል ልንቀጥልበት የሚገባው የሱብህ ጀመዓ ብቻ ሳይሆን የለይል ሰላትንም ጭምር ነው ባረከላሁ ፊኩም።

ማታ በፌስቡክና በመሳሰሉት ጊዜ ማጥፊያ ነገሮች ማርፈድን ተቆጥበን በአላርምም ታግዘን ሱብህ መስጂዳችንን ማስዋብ ይኖርብናል።

እንደሚታወቀው ቁርአንም ላይ በግልፅ እንደተወሳው ትክክለኛው የመስጂድ ግንባታ ውስጡን በዒባዳ ማስዋብ እንጂ ውጫዊ ጣሪያና ግድግዳን መገንባት አይደለም።

ከሁሉም በፊት አላህ ይታዘበናል ከሱ በታች ደግሞ ሰውም ያቀለናል። የሱብህ ሙሐደራ በሳምንት አንድ ቀንም ቢሆን መቀጠል ይኖርበታል። ደርሶችንም ቶሎ እንጀምራቸው። አላህ እኔንም እናንተንም ያበርታን !

فاللهم يا مقلب القلوب ثبت قلوبنا على دينك ربنا لا تزغ قلوبنا بعد إذ هديتنا وهب لنا من لدنك رحمة إنك أنت الوهاب
@ethio_Muslim_Nashida
@ethio_Muslim_Nashida