Get Mystery Box with random crypto!

መዲና ውስጥ አንዲት ሴት ትሞትና ጀናዛዋ መታጠብ ይጀምራል በድንገት የአጣቢዋ ሴት እጅ ከጀናዛው | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

መዲና ውስጥ አንዲት ሴት ትሞትና ጀናዛዋ መታጠብ ይጀምራል በድንገት የአጣቢዋ ሴት እጅ ከጀናዛው ብልት ጋር ተጣብቆ አልላቀቅም አለ መዲና ውስጥ ያሉ ኡለማዎች የአጣቢዋ እጅ ይቆረጥ ወይስ የጀናዛው ብልት በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገቡ በዚህ ጊዜ ነበር ለእንግድነት ለመጡት ኢማሙ ማሊክ ይህ ጥያቄ የቀረበው እሳቸውም ወደ አጣቢዋ በመዞር《 እያጠብሽ ሳለ በመሀል የተናገርሽው ነገር አለ?》ሲሉ ጥያቄን አቀረቡላት እሷም《 አዎ እያጠብኩ ብልቷ አካባቢ ስደርስ ይሄ ዝሙተኛ ብልት ብዬ ተሳደብኩ እጄም ተጣብቆ ቀረ》 በማለት መለሰች እሳቸውም በሉ በዚህ ጀናዛ ላይ አላግባብ ቀጥፋለችና ሰማንያ ጅራፍ ትገረፍ ሲሉ አዘዙ እየተገረፈች ሰማንያኛው ላይ ግርፊያ ላይ ሲደርሱ ተጣብቆ የነበረው እጇ ለቀቀ
《 ኢማሙ ማሊክ በህይወት እያሉ ማንም ፈትዋ እንዳይሰጥ》 ተብሎ መዲና ውስጥ ታወጀ ።

《የሰው ልጅ ሆይ!ምላስህን ጠብቅ እባብ ነውና እንዳይነድፍህ ።》
ኢማሙ ሻፊኢ

⇒ይህን ታሪክ ስትፈልጉ የነበራቹ ይሄው አቀረብነው
ሼር ያድርጉ ላላነበበው

@ethio_muslim_nashida