Get Mystery Box with random crypto!

​​#አንዲት_ገራሚ_ቂሷ #ነብዩ በሂወት በነበሩበት ወቅት አንድ ለማኝ ወደ ቤታቸው ይመጣል… | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

​​#አንዲት_ገራሚ_ቂሷ

#ነብዩ በሂወት በነበሩበት ወቅት
አንድ ለማኝ ወደ ቤታቸው ይመጣል…
#ከዛም አንድ ልብስ
ስጡኝ በማለት ሲጠይቃቸው
አዛኙ ነብይ አኢሻን አንሺና
አንዱን ስጪው ይሏታል…
#አኢሻም አንድ ልብስ ታነሳና
እንካ ስትለው ይህን አልፈልግም
ይላታል እሷም ቀይራ ሌላ
ልብስ እንካ አለችው እሱም
ይህንንም አልቀበልም ይላታል
አሁንም ሶስተኛ ሌላ ልብስ
እንካ ስትለው ይህንም
አልፈልግም ይላታል…

#በመጨረሻም አኢሻ እና የቱን ነው የምትፈልገው ስትለው
እሱም ነብዩ ትናንትና
ለብሰውት የነበረውን ቀሚስ
(ጀላብያ) ነው የምፈልገው ሲላት…

#አኢሻም እሱንማ ነብዩ
በጣም ስለሚወዱት አልሰጥህም
ስትለው ነብዩ ሰሟትና ስጪው
ሲሏት አንስታ ስትሰጠው
ተቀብሎ ሄደና…

#ገቢያ ቦታ ይዞት ወጣና
ከፍ ባለ ድምፅ ማን ነው የነብዩ
ሙሀመድን ልብስ መግዛት
የሚፈልግ በማለት መጣራት
ጀመረ…

#በግዜውም አንድ አይኑ የጠፍ
ሰው ነበር ይህም ሰውዬ የነብዩ
ሙሀመድ ልብስ ገቢያ
መውጣቱን ሲሰማ ባሪያ
ነበረውና ባሪያውን እንዲህ
አለው……
#የነብዩ ሙሀመድ ልብስ
ገቢያ ወጥቷልና እሱ
በሚጠራበት ዋጋ ቢያስወድደውም እንኳን ገዝተህ
ካመጣህልኝ ነፃ አወጣሀሉ ይለዋል…
#ባሪያውም በፍጥነት ገቢያ
ቦታ ሂዶ ልብሱን በጣም በውድ
ዋጋ ገዝቶት ተመልሶ
ለአሳዳሪው ይሰጠዋል
የሸጠውም ሰውዬ ከበረ…

#ልብሱን አምቶ ለአሳዳሪው
ሲሰጠው ቃል ስለገባለት ባሪያውን ነፃ አወጣው…
#ሰውዬውም የነብዩን ልብስ በእጁ ያዘና እንዲህ ሲል ዱኣ
አደረገ "ያ አሏህ የነብዩሏህ
የእቁብን አይን በነብዩሏህ ዩሱፍ
ልብስ አማካኝነት
እንዳበራህላች ሁሉ የኔንም
በነብዩ ሙሀመድ ልብስ
ይሁንብህ አብራልኝ ብሎ
ፊቱን ሲያብስበት አይኑ
በራለት ከዛ…
#የነብዩ ሙሀመድን ልብስ ይዞ
ሰውዬው ወደ ነብያችን ሄደና
ሀድያ ብሎ ያንን ልብስ
ሲሰጣቸው ነብዩን ከየት
አገኘህው ሲሉ ጠየቁት…
#እሱም ይቺ ልብሳቹህማ
ድሃ የነበረን ሰው አክብራ ባሪያን
ሁር አስብላ (ነፃ አስወጥታ)
አይኑ የጠፍን አይኑን አብርታ
ይሄው ተመልሳ መጣችላቹህ
አላቸው…
#ከዛም ነብዩ ወደ አኢሻ
ዞሩና አየሽ አይደል በመስጠትሽ
አማካኝነት ይህ ሁሉ ሰው
ተጠቀመ አሏት።

ሀቢቡና ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም
@ethio_muslim_nashida