Get Mystery Box with random crypto!

በየቀኑ ባነበውም በየቀኑ ይገርመኛል . ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዘንድ አንድ ከ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

በየቀኑ ባነበውም በየቀኑ ይገርመኛል
.
ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዘንድ አንድ
ከገጠርየመጣ ኑሮው ያልሰመረለት (ድሃ) ግለሰብ ሰሃን
ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል፡፡ነቢዩም ሰ.ዐ.ወ
ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት
ጀመሩ..የመጀሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ..ሁለተኛውንም
ጎርሰው ፈገግ አሉ..ግለሰቡም እጅጉን ተደሰተ..የነቢዩ
ጓዶች (ሰሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ስጦታ
ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን
እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ..የአላህ መልእክተኛ
ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና
ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ.. ስጦታ አቅራቢው
እጅግ በጣም ተደሰቶ..ስጦታውንም ስለወደዱለት
አመስግኖ ሄደ..አንድ የነቢይ
ሰ.ዐ.ወ ጓድ (ሰሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው
‹‹የአላህ መልእከተኛ ሆይ..ምነው ሳያካፍሉን?››
እሳቸውም ሰ.ዐ.ወ
ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሱቱን አይታችኋል
አይደል?!..
ወይኑን ስቀምሰው በጣም ይመር ነበር..ባካፍላችሁ
አንዳችሁ
ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር
እንዳታሳዩት ብየ ስለሰጋሁ ነው ብለው መለሱላቸው።
ሀቢቢ የኔ ነቢይ እናቴም አባቴም ህይወቴም ፊዳ ይሁንሎት።

አስተማሪ ይሆን ዘንድ ሼር ይደረግ

@ethio_muslim_nashida
@ethio_muslim_nashida