Get Mystery Box with random crypto!

Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_muslim_nashida — Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_muslim_nashida — Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_muslim_nashida
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.43K
የሰርጥ መግለጫ

ሀሳብ አስተያየት ☞ @To_The_One

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 26

2022-07-02 17:30:29
መዲና | MEDINA | የጉዞ ማስታወሻ | አዲስ ነሺዳ | ሙአዝ ሐቢብ

@ethio_muslim_nashida
Comment @abudi_junior
23.6K views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 17:18:42
21.0K views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 18:08:58 ❥::::::::::::::::ሀያዕ::::::::::::::❥

#repost...
☞ሀያዕ ከኢማን ነው!! ሀያዕ ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም ሀያዕ ነው!!

#እህቴ__ሆይ!

☞ሰላት የጋብቻ ዋነኛ መስፈርትሽ ይሁን!!
ለፈጠረው አምላክ ያልተናነሰ፣ ለነብሱ ያላዘነና ትእዛዝን ያላከበረ ሰው ላንቺ የሚያስብና የሚራራ አይሆንም!!

አላህን ከወደድሽ ወዳጆቹን ትወጃለሽ ለትእዛዛቱ እጅ የማይሰጡ ፋሲቆችን ትጠያለሽ፣ ትርቂያለሽም!! ሰው እንደውሎው ነው!!

::::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::

@ethio_muslim_nashida
@ethio_muslim_nashida
19.0K views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 21:43:41 #አስተማሪ #ታሪክ ነው አንብብት

አንዲት ኑሮዋ አሜሪካ የሆነች ወጣት ቤተስብዋን ለመጠየቅ ወደ ሀገር ቤት ትመጣና በዛው አጋጣሚ መልካም የሆነ ኢማን ያለው ወጣት ለትዳር እንደምትፈልግ #ለአጎቶ #ሹክ ትለዋለች፤አጎትዋም በተነገረው በዲኑ መስረት ጠንካራ ነው የሚለውን ወጣት ሲያስብ ከቆየ በኋላ አንድ በመስጊድ የሚያቀውን ጠንካራ ወጣት ጉዳዩን ሲያስረዳው መርሀባ ይለውና ከልጅቱ ጋር ያስተዋውቃቿል

#ልጅቱም ወጣቱን ካናገረችው በኋላ ልጁ አንደበቱ ርዕቱና መልከ መልካም ስለነበር ወደደችው ከእለታት አንድ ቀን ከቤተስቦቿ ጋር የምሳ ግብዣ አድርጋ ትጠራውና ከምሳ በኋላ ልትሽኘው አብራው ወደ ውጭ ትወጣለች፤ #ልጁ የፂሙ ሱና መሻአሏህ ሰለነበረ ተመለከተችውና፦

#እንዲህም #አለችው።"ሁለመናክን ወድጄዋለው በቅርብ ቀንም ኒካህ እናደርጋለን ግን ይሄን ፂምህ ትንሽ ሽማግሌ አስመስለህ ትለዋለች #ወጣቱም #እሺ #ችግር #የለውም አያሳስብሽ በማለት ፂሙን ሙልጭ አድርጎ ተላጭቶ ይመጣል።

ልጅቶዋ ተመለከተችውና አንተ "ለኔ ትእዛዝ ብለህ የነብዩን (ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም ) ትእዛዝ የምትጥስ ፈፆሞ ባል ልትሆነኝ አትችልም ብላው በቆመበት ጥላው ሄደች አሏህ አክበር!!

እስቲ ስንቶቻችን ነን ለስወች ብለን የአላህና የረሡልን (ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም ) ትእዛዝ የምንጥስ፣ቤት ይቁጠረው!!!

አስቡት ይህ ወጣት ወይ ከሷ አልሆነህ
ወይ ከሱናው አልሆነ አላህ ይጠብቀን!!!

"አሏሁመ አሪነል ሀቅ ሀቀን ወርዙቀና ኢቲባአ፣ወአሪነል ባጢላ ባጢለን ወርዙቅና ኢጅቲናበ"አላህ ሆይ!ሀቅን ሀቅ መሆኑን አሳውቀን፤መከተልንም ወፍቀን፤ባጢልም/ሀስትም ሀስት መሆኑን አሳውቀን መከልከልንም ወፍቀን!!! አሚን አሚን ያረብ

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @Ethio_muslim_nashida
 @Ethio_muslim_nashida ╚═══════════╝
17.9K views卄卂乃丨乃ㄩ卂 ✮ًٍٜ۪۪͜͡༒ًٍٰٰٰٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃, edited  18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 22:50:24 ኸሚስ ሙባረክ
#ሒከም

እኔስ ቀናሁበት አዲስ ምርጥ የህብረት ነሺዳ

ሙሉ ግጥሙን ለጠየቃችሁ ጀባ ብያለው በዱአ አትርሱኝ


***

እንጉርጉሮ ( ሙሃባዉ )
:::::::::::::::::::::::

መሀባውን ይዞ የለም የሚቸገር
መሃባው ክብረት ነው በሁለቱም አገር
ግን መቻል አቃተኝ የናፍቆቱን ነገር
በቀለም አይሰፍር ወይ ባፍ አይነገር
ሆኖልኝ ገር በገር እስካልዘየርኩሁ
።።።

የደግነት ምንጩ የዝነት መናገሻው
የከረሙ መንበር የወህዩ መፍሰሺያው
ወዳጅሁ ነኝ ያንቱ ሌላን የማልሻው
ሸውቅሁ ያሳሰረኝ ያረገኝ እንዳሻው
ማብረጃ ማርከሻው አንቱ ኖት ልይሁ
።።።።።

የደመቀው መልኩ ከንጋት ጠሃይ
ማተም የተመታው ከተከሻው ላይ
አልመጣም አይመጣም ጀማሉን መሳይ
ባይኖሩበት አይደል ባይሆኑ እሱ ላይ
በመሬት የቀናው ላይኛው ሰማይ
...።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ
።።።።።።።።

ያለሙ ረህመቱ ----------
ቢጠና ናፍቆቱ
በተራመዱበት
ቀናሁ በመሬቱ
።።።።

ባቀፈው ያን ጀማል ------------
ባቀፈው ያን ውበት
በመዲናው መሬት
እኔስ ቀናሁበት

።።።

ሐቢቢ ያለሙ ረህመት አይነታው --------
ለሰማይ ለምድርም ከብዷል ውለታው
ጦር ሳይመዝ በዝነቱ ብቻ በርጋታው
ጠላቱን በሃያል ፍቅሩ የረታው
።።።።

ነግ ዛሬም እንደትላንቱ -------------
ቀለሜ አያውቅ ያላንቱ
ሙራዱ ሆነሁ ምኞቱ
ለሌላው አይዞርም ፊቱ
።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ
።።።።።።።።

።።።

አስቀናኝ በትሩም------------
ቀልቤን አላዘዘው
ቀመሩል አንቢያእ
የተመረኮዘው
።።።።

ናፍቆቴ ማያርፈው -------------
ቅናቴ ማይሰንፈው
በቀለሜም ቀናሁ
ስሙን በሚፅፈው
።።

ማይገኝ ቅንጣትም እንከን ከሃሉ -----
ከገፁ ከስብእናውም ከቃሉ
ናፈቁኝ ሲል እኛን ማደር መዋሉ
እርቆም በፍቅሩ ገዛኝ ጀማሉ
።።።።

ሲያልቀው ጌታው ከሪሙ -------------
ቢያስጠጋው ስሙን ከስሙ
ቀድ ተወሰለ ቢኩሙ
አደም ዓለይሂ ሰላሙ
።።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ


(እንጉርጉሮ )

ያመዝሃረል ጀማል ጀማሊ ሃይባው
ሳላየው በኸበር ሆዴን አባባው
ወቅትሁን ታድየ ባልጣድ ካምባው
ባይቀናኝ መቆጠር ከባልደረባው
ያን ጀማል ባቀፈው ቀናው ባስሃባው

።።።
ወስዳ ምታበራው ጀንበር ተግንባሩ
የደግነት ምንጩ የረህማው ሰፈሩ
አሏህ ያዘዘውን ሰርተው የሚያሰሩ
እንደማይመሽ ንጋት ቀን ሌት የሚበሩ
መሬት የሚራመድ ቁርአን ነበሩ
።።።።።
ወለው በመናሜ ባየው ያንን ጀማል
መች ሩህ ጀሰዴ እንዲህ ይታመማል
እስካምር እስክሽር እንዳዩት አይቼ
ምን ቅናት ቢወርስኝ ቢሻራውን ሽቼ
ለምን ቀና አትበሉኝ ልቅና እንጂ ፀንቼ
።።።።

ያ ሙስጦፈል ወራ ያ ከንዘል ፉቀራ
ስከርረው ልኑር ያንቱን ስም ስቀራ
ሰው ሆኜ በመምጣት መንገሴ መክበዴ
ቀጥ ያለው መስመሬ ተቃንቶ ውልግዴ
ባንቱ አይደል ሙራዴ የሰላልኝ ባንዴ

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ

አሏህ እሱው ፈጥሮት አብልጦ ሲወደው -----
እኔው ከኔም በላይ እንዴት አልውደደው

ጀማሉን ያን የኛን ፈንታ -----------
የቀለም ፊደል ገበታ
እንዲህ ነው ብሎ ሊፈታ ------------
አልቻለም ቋንቋው ተረታ
።።።
አላየሁ ጀማል ውበቱን -------------
አልሰማሁ ማር አንደበቱን
አትፍረዱብኝ ባልፀናም
ባዩት በሰሙት ብቀናም
።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ

ተቃርቦኝ መውደዱ
ቢርቅ ነው ጀሰዱ
ናፍቆ መንሰቀሰቁን
ያቃተኝ መልመዱ
።።።
ጀማሉ ማይደብሰው
ባዘል ነው ሲያነግሰው
ምንኛ ታድሏል
ያየ ትልቁን ሰው
።።።።

ሲለዩት ኑር ሙሐመዱ
ቢያለቅስ ጠንቶ መውደዱ
ቀናሁኝ በቴምር ግንዱ
ወርደው ባቀፉት ጀዋዱ
።።።

ናፍቆቱ ውስጥ አይል ደጂ
አያማርጥ ትልቅ ከልጂ
ወዳጁን ካየ ነውንጂ
ሳያይ መች ያርፋል ወዳጂ

ድቤ

እኔ ቀናተኛው
ቅናቴ ማይቆመው

ስፍራው ላይ ተጥዶ
እጅ እግሩን በሳመው

ቀናሁ ትከሻሁ ላይ
በተጠመጠመው

ቀናሁ በሶሃባው
ቀናሁ በድያ እጣው

ድፋ ቢባል ደሙን
ጠጥቶት በመጣው

እንዴቱን አልቀናም
አብረው በከረሙት

ሲያማቸው መጥተው
በጁ በታከሙት

በዚያች አይንም ቀናሁ
ባየችው ሲስቁ

ዛትሁ ባረፈበት
ቀናሁ በቡራቁ

ባላይ ነው ያን ጀማል
ከሱ አድርሶኝ ወቅቴ

እንዲህ ነጋ ጠባ
በቅናት መሞቴ

ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ ||
449 views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:58:53 HIKEM 1 እኔስ ቀናሁበት አዲስ የህብረት ነሺዳ #ሒከም
723 views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:06:07 #የመዲናዉ_ሹሙ#ኢሳም አል- ሙነወርእና#አቡበከር መካ@Al Faruk Multimedia Production
@Ethio_muslim_nashida
1.0K views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 21:29:00
#ሐያተል_ዐለም አዲስ ኦሮምኛ መንዙማ በ ሙኣዝ ሀቢብ በቅርብ ቀን ይጠብቁ

ቻናላችንን ለማግኘት @Ethio_muslim_nashida
572 views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 21:26:04 በየቀኑ ባነበውም በየቀኑ ይገርመኛል
.
ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዘንድ አንድ
ከገጠርየመጣ ኑሮው ያልሰመረለት (ድሃ) ግለሰብ ሰሃን
ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል፡፡ነቢዩም ሰ.ዐ.ወ
ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት
ጀመሩ..የመጀሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ..ሁለተኛውንም
ጎርሰው ፈገግ አሉ..ግለሰቡም እጅጉን ተደሰተ..የነቢዩ
ጓዶች (ሰሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ስጦታ
ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን
እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ..የአላህ መልእክተኛ
ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና
ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ.. ስጦታ አቅራቢው
እጅግ በጣም ተደሰቶ..ስጦታውንም ስለወደዱለት
አመስግኖ ሄደ..አንድ የነቢይ
ሰ.ዐ.ወ ጓድ (ሰሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው
‹‹የአላህ መልእከተኛ ሆይ..ምነው ሳያካፍሉን?››
እሳቸውም ሰ.ዐ.ወ
ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሱቱን አይታችኋል
አይደል?!..
ወይኑን ስቀምሰው በጣም ይመር ነበር..ባካፍላችሁ
አንዳችሁ
ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር
እንዳታሳዩት ብየ ስለሰጋሁ ነው ብለው መለሱላቸው።
ሀቢቢ የኔ ነቢይ እናቴም አባቴም ህይወቴም ፊዳ ይሁንሎት።

አስተማሪ ይሆን ዘንድ ሼር ይደረግ

@ethio_muslim_nashida
@ethio_muslim_nashida
618 views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 21:25:52
የማለዳ ማስታወሻ -3

ለፕሮፋይል የሚሆኑ ፎቶዎች ለማግኘት
@HidayaGFX
554 views𝗔𝗯𝘂𝗱𝗶𝗢𝗻𝗲, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ