Get Mystery Box with random crypto!

ኸሚስ ሙባረክ #ሒከም እኔስ ቀናሁበት አዲስ ምርጥ የህብረት ነሺዳ ሙሉ ግጥሙን ለጠየ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

ኸሚስ ሙባረክ
#ሒከም

እኔስ ቀናሁበት አዲስ ምርጥ የህብረት ነሺዳ

ሙሉ ግጥሙን ለጠየቃችሁ ጀባ ብያለው በዱአ አትርሱኝ


***

እንጉርጉሮ ( ሙሃባዉ )
:::::::::::::::::::::::

መሀባውን ይዞ የለም የሚቸገር
መሃባው ክብረት ነው በሁለቱም አገር
ግን መቻል አቃተኝ የናፍቆቱን ነገር
በቀለም አይሰፍር ወይ ባፍ አይነገር
ሆኖልኝ ገር በገር እስካልዘየርኩሁ
።።።

የደግነት ምንጩ የዝነት መናገሻው
የከረሙ መንበር የወህዩ መፍሰሺያው
ወዳጅሁ ነኝ ያንቱ ሌላን የማልሻው
ሸውቅሁ ያሳሰረኝ ያረገኝ እንዳሻው
ማብረጃ ማርከሻው አንቱ ኖት ልይሁ
።።።።።

የደመቀው መልኩ ከንጋት ጠሃይ
ማተም የተመታው ከተከሻው ላይ
አልመጣም አይመጣም ጀማሉን መሳይ
ባይኖሩበት አይደል ባይሆኑ እሱ ላይ
በመሬት የቀናው ላይኛው ሰማይ
...።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ
።።።።።።።።

ያለሙ ረህመቱ ----------
ቢጠና ናፍቆቱ
በተራመዱበት
ቀናሁ በመሬቱ
።።።።

ባቀፈው ያን ጀማል ------------
ባቀፈው ያን ውበት
በመዲናው መሬት
እኔስ ቀናሁበት

።።።

ሐቢቢ ያለሙ ረህመት አይነታው --------
ለሰማይ ለምድርም ከብዷል ውለታው
ጦር ሳይመዝ በዝነቱ ብቻ በርጋታው
ጠላቱን በሃያል ፍቅሩ የረታው
።።።።

ነግ ዛሬም እንደትላንቱ -------------
ቀለሜ አያውቅ ያላንቱ
ሙራዱ ሆነሁ ምኞቱ
ለሌላው አይዞርም ፊቱ
።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ
።።።።።።።።

።።።

አስቀናኝ በትሩም------------
ቀልቤን አላዘዘው
ቀመሩል አንቢያእ
የተመረኮዘው
።።።።

ናፍቆቴ ማያርፈው -------------
ቅናቴ ማይሰንፈው
በቀለሜም ቀናሁ
ስሙን በሚፅፈው
።።

ማይገኝ ቅንጣትም እንከን ከሃሉ -----
ከገፁ ከስብእናውም ከቃሉ
ናፈቁኝ ሲል እኛን ማደር መዋሉ
እርቆም በፍቅሩ ገዛኝ ጀማሉ
።።።።

ሲያልቀው ጌታው ከሪሙ -------------
ቢያስጠጋው ስሙን ከስሙ
ቀድ ተወሰለ ቢኩሙ
አደም ዓለይሂ ሰላሙ
።።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ


(እንጉርጉሮ )

ያመዝሃረል ጀማል ጀማሊ ሃይባው
ሳላየው በኸበር ሆዴን አባባው
ወቅትሁን ታድየ ባልጣድ ካምባው
ባይቀናኝ መቆጠር ከባልደረባው
ያን ጀማል ባቀፈው ቀናው ባስሃባው

።።።
ወስዳ ምታበራው ጀንበር ተግንባሩ
የደግነት ምንጩ የረህማው ሰፈሩ
አሏህ ያዘዘውን ሰርተው የሚያሰሩ
እንደማይመሽ ንጋት ቀን ሌት የሚበሩ
መሬት የሚራመድ ቁርአን ነበሩ
።።።።።
ወለው በመናሜ ባየው ያንን ጀማል
መች ሩህ ጀሰዴ እንዲህ ይታመማል
እስካምር እስክሽር እንዳዩት አይቼ
ምን ቅናት ቢወርስኝ ቢሻራውን ሽቼ
ለምን ቀና አትበሉኝ ልቅና እንጂ ፀንቼ
።።።።

ያ ሙስጦፈል ወራ ያ ከንዘል ፉቀራ
ስከርረው ልኑር ያንቱን ስም ስቀራ
ሰው ሆኜ በመምጣት መንገሴ መክበዴ
ቀጥ ያለው መስመሬ ተቃንቶ ውልግዴ
ባንቱ አይደል ሙራዴ የሰላልኝ ባንዴ

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ

አሏህ እሱው ፈጥሮት አብልጦ ሲወደው -----
እኔው ከኔም በላይ እንዴት አልውደደው

ጀማሉን ያን የኛን ፈንታ -----------
የቀለም ፊደል ገበታ
እንዲህ ነው ብሎ ሊፈታ ------------
አልቻለም ቋንቋው ተረታ
።።።
አላየሁ ጀማል ውበቱን -------------
አልሰማሁ ማር አንደበቱን
አትፍረዱብኝ ባልፀናም
ባዩት በሰሙት ብቀናም
።።።።

ጀማሊ ሰላሙ አለይኩም ጀማሊ
ጀማሊ ሰላም አለይኩም ጀማሊ

ጀማሊ ቢያገረሽ አይደል ናፍቆቱ
ይህ ልቤ ባዩት በነኩት መቅናቱ

ተቃርቦኝ መውደዱ
ቢርቅ ነው ጀሰዱ
ናፍቆ መንሰቀሰቁን
ያቃተኝ መልመዱ
።።።
ጀማሉ ማይደብሰው
ባዘል ነው ሲያነግሰው
ምንኛ ታድሏል
ያየ ትልቁን ሰው
።።።።

ሲለዩት ኑር ሙሐመዱ
ቢያለቅስ ጠንቶ መውደዱ
ቀናሁኝ በቴምር ግንዱ
ወርደው ባቀፉት ጀዋዱ
።።።

ናፍቆቱ ውስጥ አይል ደጂ
አያማርጥ ትልቅ ከልጂ
ወዳጁን ካየ ነውንጂ
ሳያይ መች ያርፋል ወዳጂ

ድቤ

እኔ ቀናተኛው
ቅናቴ ማይቆመው

ስፍራው ላይ ተጥዶ
እጅ እግሩን በሳመው

ቀናሁ ትከሻሁ ላይ
በተጠመጠመው

ቀናሁ በሶሃባው
ቀናሁ በድያ እጣው

ድፋ ቢባል ደሙን
ጠጥቶት በመጣው

እንዴቱን አልቀናም
አብረው በከረሙት

ሲያማቸው መጥተው
በጁ በታከሙት

በዚያች አይንም ቀናሁ
ባየችው ሲስቁ

ዛትሁ ባረፈበት
ቀናሁ በቡራቁ

ባላይ ነው ያን ጀማል
ከሱ አድርሶኝ ወቅቴ

እንዲህ ነጋ ጠባ
በቅናት መሞቴ

ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ ||