Get Mystery Box with random crypto!

#አስተማሪ #ታሪክ ነው አንብብት አንዲት ኑሮዋ አሜሪካ የሆነች ወጣት ቤተስብዋን ለመጠየቅ ወደ ሀ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

#አስተማሪ #ታሪክ ነው አንብብት

አንዲት ኑሮዋ አሜሪካ የሆነች ወጣት ቤተስብዋን ለመጠየቅ ወደ ሀገር ቤት ትመጣና በዛው አጋጣሚ መልካም የሆነ ኢማን ያለው ወጣት ለትዳር እንደምትፈልግ #ለአጎቶ #ሹክ ትለዋለች፤አጎትዋም በተነገረው በዲኑ መስረት ጠንካራ ነው የሚለውን ወጣት ሲያስብ ከቆየ በኋላ አንድ በመስጊድ የሚያቀውን ጠንካራ ወጣት ጉዳዩን ሲያስረዳው መርሀባ ይለውና ከልጅቱ ጋር ያስተዋውቃቿል

#ልጅቱም ወጣቱን ካናገረችው በኋላ ልጁ አንደበቱ ርዕቱና መልከ መልካም ስለነበር ወደደችው ከእለታት አንድ ቀን ከቤተስቦቿ ጋር የምሳ ግብዣ አድርጋ ትጠራውና ከምሳ በኋላ ልትሽኘው አብራው ወደ ውጭ ትወጣለች፤ #ልጁ የፂሙ ሱና መሻአሏህ ሰለነበረ ተመለከተችውና፦

#እንዲህም #አለችው።"ሁለመናክን ወድጄዋለው በቅርብ ቀንም ኒካህ እናደርጋለን ግን ይሄን ፂምህ ትንሽ ሽማግሌ አስመስለህ ትለዋለች #ወጣቱም #እሺ #ችግር #የለውም አያሳስብሽ በማለት ፂሙን ሙልጭ አድርጎ ተላጭቶ ይመጣል።

ልጅቶዋ ተመለከተችውና አንተ "ለኔ ትእዛዝ ብለህ የነብዩን (ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም ) ትእዛዝ የምትጥስ ፈፆሞ ባል ልትሆነኝ አትችልም ብላው በቆመበት ጥላው ሄደች አሏህ አክበር!!

እስቲ ስንቶቻችን ነን ለስወች ብለን የአላህና የረሡልን (ስለሏሁ አለይሂ ወሠለም ) ትእዛዝ የምንጥስ፣ቤት ይቁጠረው!!!

አስቡት ይህ ወጣት ወይ ከሷ አልሆነህ
ወይ ከሱናው አልሆነ አላህ ይጠብቀን!!!

"አሏሁመ አሪነል ሀቅ ሀቀን ወርዙቀና ኢቲባአ፣ወአሪነል ባጢላ ባጢለን ወርዙቅና ኢጅቲናበ"አላህ ሆይ!ሀቅን ሀቅ መሆኑን አሳውቀን፤መከተልንም ወፍቀን፤ባጢልም/ሀስትም ሀስት መሆኑን አሳውቀን መከልከልንም ወፍቀን!!! አሚን አሚን ያረብ

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @Ethio_muslim_nashida
 @Ethio_muslim_nashida ╚═══════════╝