Get Mystery Box with random crypto!

።።። #ያልተጠበቀው_የሌባው_ፍፃሜ ።።። - - በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ለፈጣሪው ፀሎት ለማድረ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

።።። #ያልተጠበቀው_የሌባው_ፍፃሜ ።።።
-
-
በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ለፈጣሪው ፀሎት ለማድረስ ራቅ ወዳለ ስፍራ ይሄዳል ፣
በዚህም ወቅት ወደ ፀሎት ቦታ የሚሄዱት ተሳፋሪዎች በጉዞ መሀል ምሳ ለመብላት ወደ አንድ ካፌ ይወርዳሉ ።
ወጣቱም ከነሱ ጋር አብሮ በመውረድ ምግብ አዞ መመገብ ይጀምራል ።
ተመግቦም ከጨረሰ በኃላ ሂሳብ ለመክፈል ወደ ኪሱ ሲገባ ዋሌቱን ያጣዋል
ለ ሆቴሉ ማናጀርም ዋሌቱ እና ብሩ በሌባ መሰረቁን ያስረዳዋል ፣
ከዛም ከተማ ላለው ጓደኛው ደዉሎ የሆነውን ይነግረዋል ።
ጓደኛውም ገንዘብ ይልክለትና አመስግኖ ሂሳቡን ከፍሎ ሲወጣ ባሱ ስለቆየበት ጥሎት ይሄዳል ።
ከዛም በጣም አዝኖ ወደ ጓደኛው ዘመድ ቤት ያቀናል፣
እነሱም ጋር ለ 2 ቀን አድሮ ወደ ፀሎት ቦታው እንዲሸኙት ይጠይቃቸዋል ፣
እነሱም ያሳፍሩታል! ፀሎት ቦታውም ጋር ለ 2 ቀን አድሮ ወደ ቤቱ ወዳጁ ያሳፍረዋል ፣


ወደ ቤቱም ሲገባ እያለቀሱ ከቤቱ የሚወጡ ሰዎችን ይመለከታል ።
ከዛም ፈጠን ብሎ ወደ ቤት ሲገባ ሰዎቹ እንዳለ በፍርሀት እና ድንጋጤ ይጮሀሉ።
እሱም ማን እንደሞተ እያለቀሰ ይጠይቃቸዋል ፣ ከጎረቤቱም አንዱ ጠጋ ይልና << አንተን ያሳፈርንህ ባስ መንገድ ላይ ተገልብጦ ማንም የተረፈ ሰው የለም> > ይለዋል ፣
ወጣቱም ስላጋጠመው ችግር በሰከነ መልኩ ያስረዳቸዋል ።
በአደጋውም ከባድነት የሰዎች መልክ ባለመለየቱ ያንተን ዋሌት በኪሱ ይዞ ስናይ አንተ መስለከን ከቀበርነው ዛሬ 4ኛ ቀናችን ነው ይለዋል
ለካ በወጣቱ ቦታ የተሳፈረው የወጣቱነደ ዋሌት የሰረቀው ሰው ነበር

<<በምድር ላይ የሚያጋጥመን ነገር ቢከብደንም አላህ ሁሉንም ነገር የሚያደርገው ለኸየር ነው >>

#አብዱሰላም

Share & Support Us .