Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Enterance Preparation

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_entrance_preparation_exam — Ethio Enterance Preparation E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_entrance_preparation_exam — Ethio Enterance Preparation
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_entrance_preparation_exam
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia Enterance Preparation

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-01 13:30:52
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳትመው "Gadaa" ጆርናል ብሔራዊ ዕውቅና አጊኝቷል።

Gadaa የተሰኘው ጆርናሉ ፤ ለሦሥት ዓመት የሚቆይ ዕውቅና በትምህርት ሚኒስቴር ተሰጥቶታል።

በሁለት ቋንቋ ማለትም በእንግሊዝኛ እና በአፋን ኦሮሞ የሚታተመው ጆርናሉ፤ በሦሥተኛ ዙር ዕውቅና ከተሰጣቸው 15 የአገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች አንዱ መሆን ችሏል።
3.3K viewsFOREVER, 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 10:24:22
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሞዴል ፈተና ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ ሳምንት ይሰጣል።

ሞዴል ፈተናው ከመጋቢት 27 እስከ 29/2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

ሞዴል ፈተናው ስታንዳርዱን ጠብቆ በቢሮው መዘጋጀቱን የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ገልጸዋል።

ፈተናው ተማሪዎች ራሳቸውን ለዋናው ፈተና ዝግጁ ማድረግ እንዲችሉ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
3.8K viewsFOREVER, 07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 07:34:01
#Advertisement
ማጣቀሻ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ተማሪዎች ያወጡትን ኖት, ጥያቄ እና ሌሎች አጋዥ መፅሀፎችን በ PDF መሸጥ እና መግዛት የሚያስችላቸው ድህረገፅ ተከፈተ።

ለአጠቃቀም በጣም ምቹ የሆነው ማጣቀሻ ሻጮች ኖት አውጥተው ፈተና ሲያልቅ ከመጣል ይልቅ ወደ PDF ለውጠው ማጣቀሻ ላይ Upload በማድረግ ሌሎች ተማሪዎች በገዙ ቁጥር ገቢ የሚያገኙበት ሲሆን ገዢዎች ደግሞ ጊዜ ሳያጠፍ የቀደምት(senior) እና የእኩያ(fellow) ተማሪዎችን ኖቶች እና ሌሎች አጋዥ መርጃዎችን ገዝተው በማንበብ ማንኛውንም ጽንሰ-ሐሳብ በቀላሉ መረዳት እንዲችሉ እና ለፈተና ብቁ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።


https://mataqesha.com
3.8K viewsFOREVER, 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:17:30
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ ዩኒቨርሲቲ አቅም ማሻሻያ የተመደቡ ተማሪዎችን ውጤታማ ለማዲረግ እየሰራ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተለያዩ ሪፎረሞችን አውጥቶ እየሰራ ይገኛል ፡፡ የዚሁ አካል የሆነው የ12ኛክፍልን ሀገር አቀፍ ፈተና ኩረጃን በመከላከል በሚያስችችል በጠበቀ ድሲፕሊን የ2014ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በዩኒቨርቲዎች እንድፈተኑ ተደርጓል ፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎችን በቅድመ ዩኒቨርሲቲ የ4 ወር ያቅም ማሻሻያ እንድወስዱ በተደረገው መሰረት በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አቅም ማሻሻያ ለሚውስዱ ተማሪዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዙሪያው ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ9-12ኛ ክፍል ያሉ መማሪያ መጽሃፍትን በማሰባሰብና በየትምህርት አይነቱ ከ9-12ኛክፍል የሚያገለግሉ መረጃ መጽሀፍትን በመግዛት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡
የ24 ሰዓት የቤተ-መፅሀፍት አገልግሎት መስጠት ከ9-12ኛ ክፍል በየትምህርት አይነቱ አጋዥ መፅሀፍትን በቤተመጽሃፍት በማስቀመጥ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጣለበትን አደራ እየተወጣ ይገኛል ፡፡
ለዚህ ተግባር የተመደቡ የግቢው መምህራን የተፈቀደላቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም በልዩ ሁኔታ ለተምህርት ጥራት የድርሻቸውን እየተወጡ ያገኛሉ ፡፡
2.3K viewsFOREVER, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 14:43:05
ሩሲያዊው ጠፈርተኛ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ልምዱን አካፍሏል፡፡

ለ185 ቀናት በጠፈር ላይ የቆየዉ ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ሰርጌ ሰቨርችኮቭ፤ በህዋ ሳይንስ ያካበተውን ዕውቀትና ልምድ ለኢትዮጵያውያን ምሁራንና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጋርቷል፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ፣ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በተዘጋጀው መድረክ፤ ጠፈርተኛው ልምዱን አጋርቷል።

ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ከጠፈር ላይ የወሰደውን የዳሎል ምሥል ትላን በአዲስ አበባ ተገኝቶ ለኢትዮጵያውያን አስረክቧል።
3.5K viewsFOREVER, 11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 14:43:05
ታዋቂው ሩሲያዊ ጠፈርተኛ ሰርጌይ ኩድ ስቨርችኮቭ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ገለጻ ሊሰጥ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ የሚገኘው ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ሰርጌይ ኩድ ስቨርችኮቭ ከጠፈር ላይ የወሰደውን የዳሎል ምስል ለኢትዮጵያ አስረክቧል።

Sergey Kud-Sverchkov በ2012 ዓ.ም በዓለም አቀፉ የጠፈር ማዕከል 185 ቀናትን ያሳለፈ ጠፈርተኛ ነው፡፡

ጠፈርተኛው ነገ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እና ለተመራማሪዎች ገለጻ እንደሚያደርግ ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ሰርጌይ ኩድ ከ1998 እስከ 2002 ዓ.ም በሩሲያ ብሔራዊ የጠፈር ኤጀንሲ ያገለገለ ጠፈርተኛ መሆኑን ማህደሩ ያሳያል፡፡
3.0K viewsFOREVER, 11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 13:46:25
#FYI

የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት | የትምህርት ዕርከኖች

የትምህርት ዕርከኖቹ ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ አንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ በማለት በአራት ይከፋፈላል።

የአንደኛ ደረጃ ዕርከን ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍልን ያጠቃልላል። መካከለኛ ደረጃ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍልን ያካትታል። ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ይይዛል።

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እስከ 8ኛ ክፍል ሙሉ በሙሉ ትግበራ እንዲሁም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ደግሞ የሙከራ ትግበራ ላይ ይገኛል። ምስል፦ አአትቢ
3.3K viewsFOREVER, 10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 13:15:56
ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ የቲውተር ማህበራዊ ድረ ገጹ በቲውተር ድርጅት የእውቅና ማረጋገጫ/blue badge /አግኝቷል።

የጅግጅጋን ዩኒቨርስቲ ትክክለኛ መረጃዎች ከተረጋገጠው/Verified/ የዩኒቨርስቲው ቲውተር አካውንት

https://twitter.com/jigjigauniveth

እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል ።

https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
1.9K viewsFOREVER, edited  10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 09:00:00
  ካናዳ

ግዜዊ የሚታደስ የሥራ ቪዛ

የሚሰራበት አገር - ካናዳ

የስራው አይነት - የግንባታ _ የቧንቧ ስራዎች የሥጋ ፋብሪካ ስራዎች የ አሳ ፋብሪካ ስራዎች  የብረታ ብረት ስራዎች ሌሎችም ,,,,,
የ ሆቴል ላይ ስራዎች ,,,,,

የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
የስራ ሰዓት - 8 - 10 hr/day
የወር ደሞዝ በሰዓት 23$ እና በ
ፆታ - ሁለቱም
ዕድሜ - 18 እስከ 45
መኖሪያ ቤት - በነፃ
ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 3 ወራት  ነው
የ መሳካት እድሉ 70% በላይ

48 persons (ሰው)  ይፈልጋሉ
 



@Candajob

@Candajob

@Candajob

ወይም ለበለጠ መረጃ

  0909689038
  0909689038
ይደውሉልን

የበለጠ መረጃ ለማግኘት  ቴሌግራም  ግሩፕ ይቀላቀሉ

join  telegram

https://t.me/candajobDV
https://t.me/candajobDV
https://t.me/candajobDV
https://t.me/candajobDV
2.7K viewsFOREVER, 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 21:23:49
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት የኦዲት ግኝት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አሳውቋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2013 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርትን መገምገሙ ይታወቃል።

ቋሚ ኮሚቴው ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተገኘውን የሒሳብ ህጋዊነት ኦዲት ሪፖርት መነሻ በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው የማስተካከያ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ቋሚ ኮሚቴው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ማስተካከያ ለመውሰድ፤ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ግኝቱን ለማረም ከተቋቋመ ግብረ ኃይል ጋር መክሯል።

የፋይናንስ ህግጋትና አሰራሮችን ተከትሎ ከመስራት አኳያ የነበረውን የአሰራር ክፍተት በማረም በቀጣይ ጊዜያት ከኦዲት ግኝት ነጻ ለመሆን ተቀናጅቶ መስራት ተገቢ መሆኑን ማኔጅመንቱ ገምግሟል።

ያለ አግባብ የተከፈሉ ክፍያዎች በፍጥነት ተመላሽ እንዲሆኑ ማኔጅመንቱ ወስኗል።
1.8K viewsFOREVER, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ