Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Enterance Preparation

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_entrance_preparation_exam — Ethio Enterance Preparation E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_entrance_preparation_exam — Ethio Enterance Preparation
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_entrance_preparation_exam
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia Enterance Preparation

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-27 16:02:11
#EAES

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለባቸው ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እንደማይፈተንም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

፨ፈተናው እንደ ቀድሞ ተፈታኞች በዩንቨርሲቲዎች ይሰጣል

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
   https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
368 viewsFOREVER, edited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 15:53:39
የእርዳታ ጥሪ

ወጣት መለቶ ምትኩ ይበላለ እድሜው 21 ሲሆን
የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ አመት ተማሪ ሲሆን ይህ ወጣት በባህሪው መልካም እና በትህምርቱ ከአንደኛ ደረጃ አሁን እስካለበት ድረስ ተሸላሚ እና የደረጃ ተማሪ ነበረ ባደረበት የጭንቅላት ህመም ትምህርቱን ማቋረጥ ግድ ሆኖበታል በመጀመሪያ ህመሙ ሲጀምረው በመርሳት እንቅልፍ ከሚገባው በላይ በመተኛት ሲሆን ይህ ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ዲፕሬሽን ተብሎ ህክምና ሲከታተል ህመሙ በከፍተኛ ደረጃ እየፀና በመምጣቱ የተለያዬ ህክምና እየተደረገ የቲቪ
ማናጃይት በሽታ ነው በማለት መድሃኒት ሲወስድ በጭራሽ እየባሰበት አግሮቹ መንቀሳቀስ አልቻሉም እራሱን መቆጣጠር አልቻለም ከተለያየ ምርመራ ቦኃላ የጭንቅላት ኢጢ መሆኑ ተረጋግጦ ጭንቅላቱ ውስጥ ያለው ፈሳሽ በትክክል እንዳይዘዋወር ስለ ዘጋዉ መንቀሳቀስ እና እራሱን መቆጣጠር አልቻለም እና ኢትዮዺያ በለዉ ኮሪያ ሆስፒታል ፈሳሹን ለጊዜው በሌላ በኩል መፍትሄ እንዲያገኝ ሁለት ጊዜ ሰርጀሪ ተሰርቶ ነበር ነገር ግን እሄ መፍትሄ ዘላቂ ስላልሆነ በአስቸኳይ ወደ ዉጭ ሄዶ ህክምና እንዲያደርግ የጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቦርድ ወስኖዋል ቤተሰቦቹ ይህንን የህክምና ወጪ መሸፈን ስላልቻሉ እባካችሁ ተባብረን የዚህን ጨቅላ ወጣት ህይወት እንታደግ ለዚህ ህክምና ወጪ የተጠየቁት 1.6 ሚሊየን ነው
እትዮዽያ ላላችሁ ቀጥታ በወላጆቹ አካውንት ማስገባት ትችላላችሁ

1000271873607 የሺ እሸቱ (CBE)
1000021377329 ምትኩ በቀለ (CBE)

#share
476 viewsFOREVER, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 14:07:36 #ExitExam

ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ?

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦

" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።

ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።

አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።

ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ Sociologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።

ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "

የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?

" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።

ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል።

https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
1.3K viewsFOREVER, edited  11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 19:30:35
DUOLINGO ENGLISH TEST /DET/

ቅዳሜ ማታ 12:00 በ Zoom  ይቀላቀሉን!

ለብዙ #Scholarship ዕድሎች አስፈላጊ የሆነውን የ #Duolingo English Test ስልጠና እነሆ በ Online በነፃ ልንሰጥዎ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

!!!ይቀላቀሉን!!!

በስልጠናው:
     ስለ Scholarship በጥቂቱ
   ስለ DET ማወቅ የሚገባዎትን በሙሉ
  ለጥያቄዎ መልስ
 
ለአንድ እድለኛ ሰልጣኝ DET ክፍያ በነፃ

ስልጠናውን ለመሳተፍ ከታች ያለውን Link በመጫን አጭር ፎርም ሞልተው ይመዝገቡ።

https://forms.gle/jMYs3nvLUttPi3pP6

ከስልጠናው በተጨማሪ ፈተናውን ለመውሰድ ካሰቡ ለአጭር ጊዜ በሚቆይ ቅናሽ በ 2599 ብር ብቻ አናስፈትኖታለን።

Test Center ካስፈለግዎም  እናመቻችሎታለን

0903827304
Telegram: @DETethiopia ያገኙናል።
4.0K viewsFOREVER, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 14:29:49 የRemedial ሞጁል ነው ፥ ከየትም ቢገኝ አትጠይቁ መንግስት ያወጣው ነው ተመሳሳይ ነው ።

#Chemistry_Module

https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
4.8K viewsFOREVER, edited  11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 14:14:33 የRemedial ሞጁል ነው ፥ ከየትም ቢገኝ አትጠይቁ መንግስት ያወጣው ነው ተመሳሳይ ነው ።

#Physics_Module
Share share

https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
4.6K viewsFOREVER, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 09:49:55
#KEU

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ሞዴል ፈተና ሰጥቷል፡፡

ሞዴል ፈተናው ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ ተገቢውን ዕውቀትና ክህሎት መያዛቸውን ለመገምገምና ክፍተቶችን በቀጣይም ለመሙላት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በቀጣይ ሁለተኛ ሞዴል የመውጫ ፈተና ለተማሪዎች በግንቦት ወር አካባቢ በኢንተርኔት አማካይነት እንደሚሰጥ የዩኒቨርሲቲው የአግባብነትና ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡
3.4K viewsFOREVER, 06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 07:09:07 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

በኮሌጆች የአካዳሚክ ኮሚሽኖች ተፈትሾና በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ታይቶ የቀረበለትን መረጃ ከተመለከተ በኋላ፤ የየኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ለአምስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው፦

1. ዶ/ር ነፃነት ወርቅነህ (በህፃናት ህክምና እና ህፃናት ጤና)

2. ዶ/ር ጌታቸው አበሹ (በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ)

3. ዶ/ር ጉዲና ተረፈ (በኢነርጂ እና አካባቢ ጤና)

4. ዶ/ር ታመነ አዱኛ (በውሃ ሀብት ምህንድስና)

5. ዶ/ር ቃልኪዳን ሀሰን (በስነ ምግብ እና ህብረተሰብ ጤና)

የምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በተቋማዊ ጉዳዮች ያበረከቱትን አስተዋጽኦ መሰረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
731 viewsFOREVER, 04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 07:08:20
710 viewsFOREVER, 04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 07:08:20
704 viewsFOREVER, 04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ