2023-03-23 20:50:51
#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት የሒሳብ ህጋዊነት ኦዲት ሪፖርት በርካታ የኦዲት ግኝቶች ተገኝተውበታል።
የህ/ተ/ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ዋና ኦዲተር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የዩኒቨርሲቲውን የኦዲት ግኝቶች
ገምግሟል።
ዩኒቨርሲቲው በኦዲት ግኝቶቹ ላይ የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ተቋሙ ማስመለስ ከነበረበት የገንዘብ ምጣኔ 99.95 በመቶ እንዳላስመለሰና ማስተካከል ከነበረበት 11 ጉልህ የኦዲት ግኝቶች አንድ ብቻ ምላሽ እንዳገኘ ኮሚቴው ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው አመራር የፋይናንስ ህግጋትንና አሰራሮችን ተከትሎ ከመስራት አኳያ ሰፊ ክፍተቶች እንዳሉበትም ተጠቁሟል።
ዩኒቨርሲቲው ባልተሰጠው ስልጣን አዳዲስ ደንቦችና መመሪያዎችን እያዘጋጀ ክፍያ ሲፈጽም የነበረ መሆኑም በግምገማው ወቅት ተመልክቷል።
ለጉልበት ሰራተኞች አራት ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ቢባልም፤ ገንዘብ መውጣቱን እንጂ የት እንደገባ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ኮሚቴው አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ግኝት ማሻሻያውን እስከ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም እንዲያቀርብ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክርስቲያን ታደለ አሳስበዋል።
ተቋሙ በኦዲት ግኝቶቹ ላይ ተገቢውን የእርምት ዕርምጃዎች እየወሰደ በየሦሥት ወሩ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ማቅረብ አለበትም ብለዋል።
ገንዘብ ሚኒስቴር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችን ወስዶ ሪፖርቱን በአስር ቀናት ውስጥ ማሳወቅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር በወንጀለኛ እና በፍትሃብሄር ተጠያቂነት የሚያስከትሉ ጉዳዮች ካሉ መርምሮ ክስ መመስረት እንዳለበት ሰብሳቢው አስረድተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከስልጣኑ ውጪ ባወጣቸው ደንቦች እና መመሪያዎች የሚፈጽማቸውን ክፍያዎች እንዲያቆም
ያሳሰቡት ሰብሳቢው፤ በቀጣይ በመንግስት የፋይናንስ ህግጋት እና መመሪያዎች መሰረት ብቻ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። ያለ አግባብ የተከፈሉ ክፍያዎችም ተመላሽ እንዲሆኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
#HoPR
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
5.9K viewsFOREVER, 17:50