2023-04-07 21:48:26
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !
ነገ ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ድረስ መንገዶች ይዘጋሉ።
" ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል ነገ ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከባምቢስ በመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና ላይ የኢፍጣር ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ፕሮግሙ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፕሮግራሙ በሚካሄድበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-
- ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
- ከልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
- ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከሜትሪዎሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ሠዓት ድረስ ዝግ ይሆናሉ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልእክት አስተላልፏል።
4.7K views18:48