Get Mystery Box with random crypto!

📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamik_tube — 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖 እ
የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamik_tube — 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖
የሰርጥ አድራሻ: @eslamik_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.31K
የሰርጥ መግለጫ

አሠላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ የቻናሌ ቤተሠቦች👇👇👇
➬እስላማዊ ትምርቶች
➬እስላማዊ ታሪኮችን
➬ሶሒህ የሆኑ ሀዲሶችንም ያገኙበታል!!!
ስለ ቻናሉ ሀሠሳብ
አስተያየት እና cross ለመሠራራት ለምፈልጉ
👉 @Muba_ya👈

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-07-14 21:09:45 ፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡

ክፍል 24

ፀሀፊ fuad seid

ሀያት ከተመረቀች በኋላ ቤተሰቦቿም የሰርጉን ነገር ቀድመዉ
አናግረዉኝ ስለነበር የዝግጅቱ ጥድፊያ ዉስጥ ገባን። አዳራሽ
መከራየት ፣ ለጊዜዉ የምንኖርበት ቤት መከራየት ፣ የቤት እቃ
መገዛዛት ኧረ ስንቱ ተዘርዝሮ ይቻላል? ጣጣዉ ብዙ ነዉ። ደስ
የሚለዉ የቤት ዕቃ መገዛዛቱን ኢስራዕ እና መርየም ከኢማን ጋር
ሆነዉ አገዙን። እኔ ቆንጆ ቤት አግኝቼ ተከራይቻለሁ። የእናቴን
ፀባይ ስለማዉቀዉ ከሀያት ጋር ብቻችንን እንድንኖር ፈለግኩ
እንጂ እናቴ ከሷ ጋር እንድኖር ጠይቃኝ ነበር። ሰዒዶ የአዳራሹን
ነገር ጨርሷል። የአክስቴ ልጆችም በጣም አግዘዉኛል። በተለይ
ኢማን የሷ ሰርግ ነበር የሚመስለዉ። ብቻ ዋና ዋናዉን ጨርሰን
የጥሪ ስራዎችን ምናምን መስራት ጀመርን። የሰርግ ጣጣ ግን
ብዙ ነዉ። ከምር እንደዉም ቢቀር ያስብላል። ቀለል ያለ ድግስ
ቢሆን ይሻል ነበር።
ከብዙ ዉጥረት በኋላ የሰርጉ ቀን ደረሰ። ይገርማል አባዬ ኒካህ
ላይ ተገኝቶ ለሰርጉ ሳይደርስ ሞተ። አንደኛ ሚዜዬ ሰዒድ ነዉ።
ሁለተኛናሶስተኛ ሚዜዎቼ የአጎቴ ልጆች ናቸዉ።
በሚዜዎቼ ታጅቤ ሀያትን በወጉ ከቤቷ ወሰድኳት። ሀዩ ቬሎ
አምሮባታል አይገልፀዉም። አዳራሹ ሰርጋችንን ለማድመቅ
በመጡ እድምተኞች ደምቋል። የሙሽራዉ ቦታ ላይ ከሚዜዎቼ
ጋር ተቀምጬ ሰውን አየሁት! ይበላል፤ይጠጣል። በጣም ደስ
አለኝ። በየአንዳንዷ ጉርሻ ዉስጥ ሀያትን ላይመኝ ማጣቱንና የኔ
መሆኗን አብሮ የሚዉጥ መሰለኝ።
የሰርጉ ቀን ማታ ከሀዩዬ ጋር ሆቴል ነበር ያደርነዉ። ልክ
ክፍላችን እንደገባን ሁለታችንም ትንሽ ደከም ብሎን ስለነበር
ገላችንን ታጠብን። ትንሽ ቀለል አለን። እራት በልተን ከጨረስን
በኋላ ከሀዩ ጋር የፍቅር ጨዋታዉ ተጀመረ። እየተሳሳምን ልብሷን
ቀስ ብዬ አወለቅኩትና በጡት ማስያዣናበፓንት ብቻ አስቀረኋት።
ዉበቷ ሊያቀልጠኝ ምንም አልቀረዉም። በጣም ታምራለች።
ገላዋ ዉብ ነዉ። ዛሬ ለኔ ብቻ የተገለጠ፣ ማንም ያላየዉ ገላ!
ልብሴን በዚህ ፍጥነት ማዉለቅ እንደምችል እስከዚህች ቅፅበት
ድረስ አላዉቅም ነበር። ሀዩ እንደዛሬዋ ቀን የጓጓችለት ቀን ያለ
አይመስለኝም። አልጋዉ ላይ ተጋድመን መሳሳም ጀመርን።
የተቀደሰ መሳሳም! ትዳር ነዉና መልዓክት ሳይቀር በደስታ
ሳይዘምሩ አይቀሩም። ስሜቴ በጣም እየጋለ መጣ። እራሴን
መቆጣጠር ከበደኝ። ሳላስበዉ ሀዩን በጥፊ መታኋት እና የጡት
ማስያዣዋን ከሰዉነቷ ላይ ገንጥዬ አነሳሁት። ሀዩ በጣም
ደንግጣለች ግን ከስሬ ሁና የማደርገዉን ታያለች። ለመነሳት
አልሞከረችም። እዛዉ እንደተንጋለለች በጥፊዬ ህመም
ምክንያት ከአይኗ እንባ እየፈሰሳት የልቤን አደረስኩ።
ሀያትን ምንም ስሜቷን ሳልጠብቅ ነበር የተገናኘኋት። መረጋጋት
ተሳነኝ። ስሜቴ ሲግል በጥፊ የመታኋት ለምን እንደሆነ
አላዉቅም። ግን ከዚህ በፊት ራሄልንም መትቼያት ነበር። አሁን
ትንሽ ግልፅ ሆነልኝ። አልጋ ላይ መረጋጋት አልችልም። ሀዩን
ማየት በጣም አፈርኩ። ተንደርድሬ ወደ በረንዳዉ ወጣሁ።
በረንዳዉ ላይ ያለዉ ዥዋዥዌ ወንበር ላይ ተቀምጬ ተንሰቅስቄ
አለቀስኩ። በምድር ላይ ያለዉን የደስታ ጥግ ማጣጣም
ካለመቻል በላይ ምንም ህመም ሊኖር አይችልም። የሚስትን
ክብር መጠበቅ ካለመቻልናስሜቷን ለማስተናገድ ብቁ ካለመሆን
በላይ ከባድ መርዶ የለም። ጌታዬ ምነዉ ሀዘኔ በዛ?
አልቅሼ ስገባ ሀዩ አልጋዉ ዉስጥ ገብታ ተኝታ ነበር። ፈገግ
ለማለት ሞከረች። እየቀፈፈኝም ቢሆን ከአጠገቧ ሄጄ ተኛሁ።
ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላ ተኛች። ደረቴ ላይ ስትተኛ ብዙም
እንዳልተከፋችብኝ በማሰብ በጣም ደስ አለኝ።
በነጋታዉ ከሆቴል ወደ ተከራየነዉ ቤት ሄድን። ማታ ላይም
ስንደግመዉ ስሜቴ ሲግል እጄ ጥፊ መሰንዘሩንና መድፈር
በሚመስል መልኩ መገናኘቴን መተዉ አልቻልኩም። ሳምንት
ሙሉ አየነዉ ፣ ያዉ ነዉ።
በሳምንቱ የስነ ልቦና ባለሙያ አማከርኩኝ። የህይወት ታሪኬን
ሁሉ ከፈተሸ በኋላ ምናልባት የችግሩ መንስኤ የእናትናአባቴን
ድብድብ ሳይ ማደጌ ሊሆን እንደሚችል ነገረኝ። የአባቴና የእናቴ
ፀብ ለኔም ተረፈ? ታዲያ ለምን ፀባዬ ግንኙነት ስፈፅም ብቻ
ይቀየራል? መልስ አላገኘሁለትም።
ሀያት ትምህርቷን እንደመጨረሷ በተማረችበት ሙያ መስራት
ትፈልጋለች። ዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ ዉጤት ስላላት መምህር
እንድትሆን ሊያስቀራት ፈልጎ የነበረ ቢሆንም እሷ
አልተቀበለችዉም። አሁን አዲስ ሆቴል ከአዲስአበባ ዉጪ
ለመክፈት አቅደናል። ሀጅራ እስክንድር እኔና ሀዩ ተሰባስበን
ከመከርንበት በኋላ ሆቴሉን ራሄል ልንለዉ ወሰንን። ራሄልን
የምናስታዉስበት አንድ ተቋም ይሆነናል ብለን አስበናል። ለሆቴሉ
ግንባታ የኛ ቤተሰብ እና የሀዩ ቤተሰቦች በአክሲዮን መልክ
ከፍተኛዉን መዋጮ አዋጣን። መሬት የከተማዉ መዉጫ ላይ
አገኘን። የህንፃዉም የዲዛይን ስራ ተጀመረ።
ሀያትን በአግባቡ ልገናኛት አለመቻሌ እንደድሮዉ ፈታ ብዬ
እንዳላወራት አደረገኝ። የተገናኘኋት ጠዋት ሀፍረት ሊዉጠኝ
ይደርሳል። ምንም ሳላወራ ቁርሴን በልቼ ወደ ስራ እሄዳለሁ።
ሀያት ግን ስሜቴን ስለተረዳችዉ ፈታ ልታደርገኝ ትሞክራለች።
ጠዋት ወደ ስራ ስሄድ መኪናዬ ከአይኗ ሳይርቅ ወደ ቤት
አትገባም። ልብሴ ሆና ሚስጥሬን ሸሽጋልኛለች።
አንድ ቀን ከሀያት ጋር የሀዩን ወላጆች ለመጠየቅ ወደ ቤታቸዉ
ሄድን። በልተን ፣ጠጥተን ከተጫወትን በኋላ ልንሄድ ስንል
የሀያት አባት ዱኣ ማድረግ ጀመሩ። ሁላችንም አሚን እንላለን።
ከዱአቸዉ በጣም ልቤን የነካዉ ለሀያት ታናሽ እህት መግፊራ
ያደረጉት ፀሎት ነበር። "እንደ አክረም ያለ እንከን አልባ ባል
ስጣት።" ነበር ያሉት። ሀያትን አየኋት እሷም "አሚን" አለች።
ስንት እንከን እንዳለብኝ እያወቀች አሚን ማለቷ ገረመኝ። ሀዩ
ጉድለቴን እስከመች ትቆቋመዉ ይሆን? እየጎዳኋት እንደሆነ
እየተሰማኝ ነዉ። ሀፍረቴ ጣራ እየነካ ሲመጣ ሀያትን እንድንፋታ
ልጠይቃት ወሰንኩ። ከስራ እንደተመለስኩ ጭኖቿ ላይ ተኝቼ
ፀጉሬን እየደባበሰችኝ "ሀዩ እኔ ከዚህ በላይ ባልጎዳሽ እና
ባትሰቃዪ ደስ ይለኛል። ልፍታሽ?" አልኳት።
ሀዩ በአጭሩ ምላሹን ሰጠችኝ። ግንባሬን ሳመችና "ከብዙ
ጥረት በኋላ ነዉ ያገኘሁህ። በግንኙነት ከሌላ ሰዉ ጋር በእርካታ
ከመኖር ከአንተ ጋር ዘላለም እንዲህ መኖሩን እመርጣለሁ። እኔ
እታገሳለሁ። አንተ ግን ደግመህ ይሄን ጥያቄ እንዳትጠይቀኝ!"
አለችኝ።
ከሀዩ ጋር አብረን መኖር ከጀመርን አምስት ወራት ተቆጠሩ።
ሀዩም አምስት ወር ሙሉ በጥፊ እየተመታች ክብሯን ባልጠበቀ
መልኩ ስገናኛት ችላኝ አለች። ያለፉትን አምስት ወራት ለሊቱን
ተነስቼ ጌታዬ መረጋጋትን እንዲሰጠኝ ሳልጠይቀዉ ቀርቼ
አላዉቅም። ሀዩን ከተገናኘሁ በኋላ ወደ በረንዳ ሄጄ መንሰቅሰቁ
የዘወትር ተግባሬ ሆኗል። ገንፎዉ ተሰጥቶህ ማንኪያዉን ስትቀማ
በጣም ያሳዝናል!
ከሀያት ጋር ስተኛ የሚፈጠረዉን ነገር በተመለከተ ለማንም
አልተናገርኩም ነበር። የመጨረሻ አማራጬ ግን ለሰዒድ
ማማከር ነበር። እሱ መፍትሄ አያጣም።
ሰዒድን ለማማከር በወሰንኩ በነጋታዉ ሰዒድ ወደ ቢሮዬ
የማማክርህ ጉዳይ አለኝ ብሎኝ መጣ።
እንደተቀመጠ "ሰዉየዉ እንደዳርኩህ ልትድረኝ ነዉ!" አለኝ።
"ሰዒድዬ በአላህ እኛ የቀመስነዉን ደስታ ልትቀምሰዉ ነዉ?"
አልኩ የተደሰትኩ ለመምሰል እየሞከርኩ። እኔ በሀዩ ደስተኛ
ብሆንም ሀዩን ግን እያስደሰትኩ አይደለም።
"ሊያዉም ልዛመድህ ነዋ!" አለኝ ፈገግ ብሎ እያፈጠጠብኝ
"ማንን? መግፊራን? አላምንም!" አልኩት። መግፊራ የሀያት
እህት ናት።

ይቀጥላል........

ይቀላቀሉን

@eslamik_tube
2.4K views"ųmį¥ę": , 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:02:12 ስለቻናሉ ሀሳብ(አስተያየት) ያላቹሁ @MUBA_YA ላይ አሳውቁኝ

መልካም እንቅልፍ ተመኘሁላቹሁ ውዶቼ
2.7K views"ųmį¥ę": , edited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:58:24 በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።
:
" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው...
2.8K views"ųmį¥ę": , 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:52:34 ‍ አጭር አስተማሪ ታሪክ
ለምጣዱ ሲባል...!

አንዲት ሴትዮ ጓዳቸው ውስጥ እየተንጎዳጎዱ ድንገት አንዲት አይጥ ምጣዳቸው ላይ ትወጣለች ወንድ ልጃቸው እንጨት ያነሳና አይጧን ለመምታት ሊሰነዝር ሲል ሴትዮዋ አስቆሙትና "ልጄ አይጧን ስትመታ እንጀራ ማብሰያችንን ምጣዱን ሰበርከው ማለት ነው ስለዚህ እስኪ ግድ የለም ለምጣዱ ሲባል አይጧን ዝም እንበላት" አሉት ይባላል።

ከዚህ ታሪክ ሁሌም ለምንፈልገው ነገር ስንል ብዙ ነገሮች መታገስ እንዳለብን ፣ ከመወሰናችን በፊት ማስተዋል እንዳለብን እንረዳለን ።
2.6K views"ųmį¥ę": , 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:17:06 ፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 23

ፀሀፊ fuad seid

ግንባሩን ስሜው ወዲያው ወደ ድንኳን ሄድኩ ሠው እየጮሀ ያለቅሣል፡፡ ተይማኖታችን ከማንባት በዘለለእየጮሁ ማልቀስን
ስለሚከለክል ሰዎቹ ዝም እንዲሉ ለመጠየቅ ሞከርኩ ግን
ሊሰሙኝ አልቻሉም። ኋላ ላይ አንድ ሽማግሌ ተቆጥተዉ
ወንዶቹን ስርዓት አስያዙልን። ድንኳን ዉስጥ እንደተቀመጥኩ
አንድ ጎረቤታችን ጠርታ ወደ ሴቶች ድንኳን ይዛኝ ሄደች።
በእስልምና እምነት መሰረት በሰርግም ሆነ በለቅሶ ወንዶች
ከሴቶች ጋር እንዲቀላቀሉ አይፈቀድም። የሴቶች ድንኳን ጋር
ስደርስ ሴትየዋ "ኧረ እናትህን ተይ በላት ፊቷን ቧጣ
ጨረሰችዉ። አላህም አይወደዉ!" አሉኝ። ወደ ሴቶች ድንኳን
ስመለከት እናቴ ደረቷን እየደበደበች ፊቷን እየቧጠጠች
ታለቅሳለች። ከአባዬ ሬሳ አርቀዉ ድንኳን ዉስጥ ያስገቧት
በጣም አስቸግራ መሆኑ ገባኝ። አባቴ በህይወቱ በነበረበት ጊዜ
ስታቆስለዉ ኖራ ዛሬ ታስመስላለች። እናቴ ሆና ክብሯ ባይዘኝ
ባጋጫት ሁላ ደስ ይለኝ ነበር። ወይ የሀይማኖት እዉቀት የላት!
ወይ ስነ ምግባር የላት፣ መልክ ብቻ!
እናቴ መምጣቴን ስታይ ትንሽ ተረጋጋች። እንዲሁ ለኔ ክብር
አላት። እህቶቼን ከቤት ጠርቼ ስርዓት እንዲያስይዟት ነገርኳቸዉ።
.
አባዬ ወዲያዉ ሰባት ሰዓት ላይ ተሰግዶበት ተቀበረ። በእስልምና
እምነት በሬሳ ላይ የሚሰገድ የስግደት አይነት አለ። ሬሳን ቶሎ
መቅበርም ይወደዳል።
በነጋታዉ ሰው ሀዘኑ እየበረደለት ድንኳኑ ዉስጥ መጫወት
ጀመረ። ግማሹ አስፈርሾ ይቅማል። ግማሹ ክብ ሰርቶ
ይጫወታል። ጮክ ብሎ ሚስቅ ሁሉ ነበር። አሪፍ የቤተሰብ
መሰብሰቢያ መድረክ ሆኗል። ለቅሶ መሆኑን ረሱት መሰለኝ።
ማታዉን ቤተሰብ ተሰብስቦ የአባዬን ስራ ማን ያስተዳድር
በሚለዉ ላይ መከረ። መጨረሻ ላይ እኔ ላይ እምነታቸዉን
ጥለዉ ትምህርቴን አቋርጬ የአባቴን ስራ እንድሰራ ወሰኑ።
.
ለቅሶዉ ቀዝቅዞ ፣ ድንኳኑ ፈራርሶ ፣ሰው እንደተበተነ ፤ ሀዩንም
ወደ ባህርዳር ሸኘኋት። ቢያንስ እስኪ ሰቃያችን ትመረቅ። እኔና
ሪቾ እንደሆነ ከትምህርት መስመር ወጥተናል። ትንሽ ቆይቼ
እኔም ወደ ባህርዳር ሄጄ ልብሶቼን ይዤና ዊዝድሮዉ ሞልቼ
ተመለስኩ። የህይወት መስመር መቼ እንደሚቀየር አይታወቅም።
ትናንት ተማሪ የነበርኩት ልጅ ይኸዉ ሰራተኛ ልሆን ነዉ።
.
ስራ በጀመርኩበት የመጀመሪያዉ ቀን ማታ የሪቾን መቃብር ሄጄ
ጎበኘሁ። ወደ ባህርዳር ስበር የፃፍኩትን ግጥም አነበብኩላት።
ሪቾ እንዳለችዉ የእዉነትም ተዉባ እየጠበቀችኝ ይመስለኛል።
እንዲህ ሱፍ ለብሼ የአባቴን መኪና ይዤ ሪቾ ብታየኝ ምን ትል
ነበር? እኔንጃ ብቻ ለየት ያለ ቃል አታጣም። የሆነ ነገር ትለኝ
ነበር።
.
የአባዬን ስራ እያስተዳደርኩ ቀናትም እየሮጡ ወራትም
እየተገነጠሉ ሰባት ወራት አለፉና የሀዩ እና ሀጅራ ምርቃት ደረሰ።
የፈጣሪ ዉሳኔ ነጠለን እንጂ እኔናሪቾም አብረን እንመረቅ ነበር።
በነገራችን ላይ የአባዬን ስራ በጣም ትርፋማ አድርጌዋለሁ።
በቅርቡ እንደዉም ባለን ተቀማጭ ገንዘብ ሌላ ተጨማሪ ስራ
ለማስጀመር እያሰብኩ ነዉ።
.
ቅዳሜዉን ዉዷ ሚስቴን ላስመርቅ ወደ ባህርዳር ሄድኩ።
ሀዩዬ የግቢዉን ትልቁን ዉጤት ነበር ያስመዘገበችዉ። አራት
ነጥብ! በጣም አኮራችኝ። ሀዩ ግን ከመመረቋ በላይ ጓግታለት
የነበረዉ አብረን የምንኖርበት ቀን መድረሱን ነዉ። በሰርግ ከቤቷ
በወጉ የምትወሰድበትን ቀን! የምንጠቃለልበትን እለት!
ሀዩን ሜዳሊያ አጥልቃና ዋንጫ ይዛ ሳያት በጣም ደስ አለኝ።
ሪቾ ከኛ ጋር ባለመሆኗ ግን አዘንኩ።
ሀዩ ፍልቅልቅ እንዳለች ዙሪያዋን የቆሙትን ቤተሰቦቿን እና እኔን
እያየች "የሀያትን ምርቃት ከሌሎች ምርቃቶች ለየት
የሚያደርገዉ በሰርጓ ዋዜማ መካሄዱ ነዉ።" አለች።
.
ይቀጥላል..........

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube
2.4K views"ųmį¥ę": , 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:17:06 ፡፡፡፡መንታ መንገድ::::

ክፍል 22

ፀሀፊ fuad seid

ራሄል የፃፈችልኝን ደብዳቤ ካነበብኩ በኋላ ከለቅሶ ቤት
አልጠፋሁም። ሀጅራ አዲስአበባ ደርሳ የራሄልን ሬሳ ስታይ ራሷን
መቆጣጠር ከበዳት። ለረዥም ሰዓት አነባች። ትናንት ከጎኗ
ትማር የነበረች ልጅ ሳይታሰብ መሞቷ ልቧን ሰበረዉ። ሀጁ ወደ
ኮምቦልቻ እስክትመለስ ድረስ ያለዉን ጊዜ እነሀያት ቤት
አሳለፈች።
ራሄል ዉጪ የነበሩት ዘመዶቿ እንደተሰበሰቡ በሞተች በሶስተኛዉ
ቀን ተቀበረች። ዉስጤ በሀዘን ተሞልቷል። ገዳይዋ እንደሆንኩ
እየተሰማኝ ነዉ። ራሄል ግን እወዳት እንደነበር እንዴት አወቀች?
አዎ ገባኝ ከሀያት በተለየ ጊዜዬን ከሷ ጋር ነበር የማሳልፈዉ።
አይኖቼ፣ ሁሉ ነገሬ ከአንደበቴ ዉጪ እንደምወዳት ይናገር ነበር።
ከፓፒረሱ ክስተት በኋላ ግን የወደፊት ህይወትን ከግምት ዉስጥ
ባስገባ መልኩ ከራሄል እና ከሀያት ምርጫዬ መሆን ያለባት
ሀያት መሆኗን ወሰንኩ። ትኩረቴንም በከፊል ከራሄል ወደ ሀያት
አዞርኩ። ሀያት ምንም አይጎድላትም። ግን ራሄል ልቤ ዉስጥ
ነበረች።
በህይወት እስካለሁ ድረስ እንግዲህ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ
ራሄል መቃብሯን እንድጎበኝ አደራ ብላኛለች።
ግን ሰዉ መንገድ ላይ ሲያየዉ ይሳሳለት የነበረዉ ዉበቷ አፈር
ገባ በቃ? ሰዉ ግን ከንቱ ነዉ። ምንም ዛሬ ቢፈካ ላለመንጠፉ
ዋስትና የለዉም።
ሀያት ሀዘኑ እንደከበደኝ ስለገባት በቻለችዉ አቅም ብቻዬን
አትተወኝም። በርግጥ ሰሞኑን አባዬ ትንሽ ስላመመዉ ስራ እሱን
ተክቼ መግባቴም ለጊዜዉም ቢሆን ሀዘኔን እንድረሳዉ
አድርጎኛል። ስራዉ ከአባዬ ድርጅት ጋር መስራት የሚፈልጉ አዲስ
ደንበኞች ሲመጡ ተቀብሎ ማነጋገር፣ ወደብ ላይ ያሉ እቃዎችን
በተመለከተ ከድርጅቱ ሀላፊዎች ጋር በመመካከር ቶሎ እንዲገቡ
ማድረግ ፣ ከሻጮች ጋር መደራደር ምናምን ነዉ። ብዙ
ዉሳኔዎችን በራሴ መወሰን ስለምፈራ አባዬ ጋር ደዉዬ እሱ
እየነገረኝ እኔ እፈፅማለሁ። ስራዉን ከዚህ በፊት አሳይቶኝ
ስለነበር ብዙም አልከበደኝም። የአባዬ ፀሀፊም ልምድ ስላላት
በደንብ ታግዘኛለች። ሀዩ ከስራ ስመለስ አብራኝ አምሽታ ወደ
ቤት ትሄዳለች።
ከራሄል አባት ጋርም በቅርብ እየተገናኘን እናወራለን።
እስክንድርንም በተደጋጋሚ አገኘዋለሁ። በራሄል ዙሪያ የነበሩ
ሰዎችን ሳወራ እሷን ያወራኋት ያህል ደስ ይለኛል። እንዳለችዉም
ሳጣት ከፍቅሯ እሳት ጋር መጋፈጥ ጀምሬያለሁ። ትናፍቀኛለች።
አንዳንዴ ሀያት ራሄልን እንደነጠቀችኝ እየተሰማኝ ታስጠላኛለች።
እንደዉም ሀዩ ላይ በጣም ቀዝቅዤባት ነበር። ግን የሰዒዶ ምክር
አባነነኝ። "እሷም ራሷን አጥፍታልህ እንዳታርፈዉ!" ነበር ያለኝ።
ቆይ አሁን ስለ ግጥም ከማን ጋር ነዉ የምወያየዉ? ራሄልን
በጣም እወዳት ነበር። ካጠገቤ ስትርቅ ሁሉም ነገር ግልፅ
ሆኖልኛል።
ቀናት ቀልድ አያዉቁም ፣ ወራትም ቀናት ሲጠራቀሙላቸዉ እብስ
ከማለት ወደኋላ አይሉም። ራሄል ከሞተች ሁለት ወራት አለፉ።
ክረምቱ አልቆ አዲስ አመት ተበሰረ። ራሄል የሌለችበት ባዶ
አመት አዲስ አመት ተባለ።
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲም በየቤታቸዉ የተበተኑ ተማሪዎችን ጠራ።
ከሀዩእና እስክንድር ጋር ሆነን ወደባህር ዳር ሄድን። የመጨረሻ
አመታችን ስለሆነ በዚህ አመት እንመረቃለን። በአዉሮፕላን
እየሄድን ሪቾ ትዝ ስትለኝ አጭር ግጥም ፃፍኩ። ወደ መቃብሯ
ስሄድ አነብላታለሁ።
"አንቺ የሌለሽበት ሁሉ ነገር ባዶ፣
ሰፈሩ ጭር አለ ፣በፅልመት ተጋርዶ።
ድምቀት ማለት አንቺ ፣ ስትጠፊ ገባኝ፣
ምንድነዉ ሳቃቸዉ ፣ ሰላም የሚነሳኝ?"
ሀያት በዉጤቷ አሁንም የክፍላችን ሰቃይ ናት። ሪቾ ሞተች እንጂ
ሁለተኛዉ ትልቁ ዉጤት የሷ ነበር። ድሮ እኩል ነበርን። አሁን ግን
በአንድ ትምህርት በልጣኛለች። ግን ሞታለች። ትምህርት
እንደተጀመረ እስክንድርን በጣም ቀረብኩት። ራሄል ከናፈቀችኝ
የማገኘዉ ብቸኛዉ ሰዉ እስክንድር ነዉ። በርግጥ ጊዜዉ ሲገፋ
የራሄል ሀዘንም ቀለል ብሎልኛል። ሀያት ወደ ጣና
እንደለመድነዉ ባጃጅ ተኮናትረን ከሄድን ገና ፓፒረስ ጋር
ከመድረሳችን በፊት በወሬ ትጠምደኛለች። ወሬዉ ትኩረቴን
ወደሷ ካልወሰደዉ ከንፈሬ ላይ ትለጠፋለች። ፓፒረስን ካየሁ
ራሄል ትዝ ትለኛለች። ከራሄል ጋር ያሳለፍነዉን የፓፒረስን ምሽት
ሳስታዉስ ደግሞ ፈገግታ ይርቀኛል። የሀዩም ትኩረቴን ለመስረቅ
መሞከር ሪቾ ትዝ እንዳትለኝ ለማድረግ የታለመ ነዉ። ቀናችንን
ሰላማዊ ለማድረግ!
ትምህርት ተጀምሮ ከወር በላይ እንደተማርን አባዬ በተደጋጋሚ
መታመም ጀመረ። እኔናሀዩ አንዴ ወደ አዲስአበባ መጥተን
ጠይቀነዉ ተመልሰናል። እኛ ስንጠይቀዉ ትንሽ ሰላም ነበር።
ከተመለስን በኋላ ግን ባሰበት።
ጠይቀነዉ በተመለስን በአስራአምስት ቀኑ የአባዬ ጤንነት ጥሩ
የሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን ኢስራዕ ነገረችኝ። በየቀኑ
እንደዋወላለን። በሰዓቱ እኔናሀዩ የመመረቂያ ፅሁፋችንን ምዕራፍ
አንድ ለማጠናቀቅ እየተጣደፍን የነበረ መሆኑ አባዬን ደግሜ
እንዳልጠይቀዉ አደረገኝ።
አንዳንዴ ማታ ከሀዩ ፣ ሀጁ እና እስክንድር ጋር ከተለያየን በኋላ
የግቢያችን ላቭ ስትሪት ላይ ብቻዬን ዎክ አደርጋለሁ። እዚሁ
መንገድ ላይ ሪቾ የፍቅር ግጥም መፃፍ ጀመርኩ ብላ ስታነብልኝ
የነበረዉ ድባብ ትዉስ ይለኛል። እጆቿን ወደ ላይ ሰቅላ
እየተሽከረከረች ስትጨፍር አይኔ ላይ ድቅን ትላለች። ብቻዬን
ስሆን ሀዘኑን መቋቋም ይከብደኛል። ሪቾ በጣም ትናፍቀኛለች።
ፓፒረስ ዉስጥ ራቁታችንን ሆነን ከንፈሬን ስትስመኝ
የማልቆጣጠረዉ ስሜት በጥፊ እንድመታት እንዳደረገኝ
አስታዉስና ይገርመኛል! እስከአሁን መልስ ያጣሁለት ጥያቄ!
አካሌን ማን አዘዘዉ? ልቤ እኮ ሙሉ ለሙሉ ሊተኛት ፈልጎ ነበር።
ሀሙስ ጠዋት ላይ ኢስራዕ ደወለችልኝ። "ወዬ የኔ ሚጢጢ!"
አልኳት።
"አቢ እኮ ወደ አኼራ ሄደ!" አለችኝ እያለቀሰች። አኼራ ማለት
ቀጣዩ አለም ማለት ነዉ። አባቴ ሞተ? እንባዬ ፈሰሰ! ሲያመጣዉ
እንግዲህ አንዴ ነዉ። አባቴን በጣም ነበር የምወደዉ።
ከተረጋጋሁ በኋላ ለሀዩ ደዉዬ ነገርኳት። ሀዩ በጣም አዘነች።
ሀዘኑ በጣም እንዳይጎዳኝ ፈርታለች። እኔ ግን በልኩ ነዉ
ያዘንኩት። አባቴ በመሞቱ ጌታዬን አላማርርም። እድሜዉ
ሄዷል። ከሀዩ ጋር አራት ሰዓት ላይ ቢዝነስ ፍላይት አግኝተን ወደ
አዲስአበባ መጣን። ሰዒድ ከአየርማረፊያ ተቀብሎን የኛ ቤት
ቅያስ ጋር ካደረሰን በኋላ እናቱን ለማምጣት እኛን ወደ ሰፈር
የሚያስገባዉ ቅያስ ጋር አዉርዶን ሄደ። ወደ ቤት እየቀረብን
ስንመጣ አንድ ሰዉዬ ፈገግ ብሎ እዚህ ሰፈር ከሆንን ለቅሶ
ቤቱን እንድናሳየዉ ጠየቀን። እሺ ብለነዉ አብረን መሄድ
እንደጀመርን ሰዉየዉ እየቀለደ ሊያስቀን ሞከረ። ያወቀኝ
አልመሰለኝም። ለቅሶ ለመድረስ የመጣዉ ግን እኛዉ ጋር ነበር።
ልክ ቤት ጋር ስንደርስ በራችን ላይ የተደኮኑትን ድንኳኖች
እያሳየሁ "እዛ ቤት ነዉ!" አልኩት። ወዲያዉ ማጓራት እና
እየጮኸ ማልቀስ ጀመረ። እየጮኸ እኛን ትቶን ወደ ድንኳኑ
እየፈጠነ ሄደ። እዉነት ለመናገር ሳቄን ልለቀዉ ምንም
አልቀረኝም። ሰዉ እንዴት ድንኳን ሲያይ ይቀየራል? ማስመሰል
ምን ያደርጋል? ሀዘኑን ለመግለፅ እንደከብት ማጓራት
አይጠበቅበትም እኮ! አስመሳይ!
ቤት እንደገባሁ ኢስራዕናመርየም አቅፈዉኝ መንሰቅሰቅ ጀመሩ።
ሳያቸዉ አንጀቴን በሉት ከአይኔ እንባዬ ፈሰሰ። ወዲያዉ እነሱን
አረጋግቼ የአባቴ ሬሳ ወዳለበት ክፍል ገባሁ። አባዬ ተከፍኖ
በጣም ደስ የሚል ሽቶ ተቀብቷል። ያን የመሰለ መኪና
እንደማይዝናሱፍ እንዳልቀያየረ ዛሬ በአቡጀዴ ተጠቀለለ።

ይቀጥላል.......

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube
2.4K views"ųmį¥ę": , 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:08:35 ጥያቄ በረሃ ላይ መኪና እያሽከረከራችሁ ነው፣ ደክሞዋችኋል ውሀ ጠምቷችኋል ተርባችኋል....ከዚያም መንገዳችሁ ላይ 3 በሮች መጡ 1ኛው በር ቀዝቃዛ መጠጦች እና ሀይቅ አለ 2ተኛው ምርጥ አልጋ እና ቆንጆ እንቅልፍ አለ 3ተኛው ቆጥራችሁ የማትጨርሱት የገንዘብ ክምችት አለ የመጀመሪያ የምትከፍቱት የትኛውን በር ነው? #መልሳችሁን comment ላይ
2.4K views"ųmį¥ę": , 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:51:24
{أَلَمْ تَرَ كَيْفَ ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا كَلِمَةً طَيِّبَةً كَشَجَرَةٍ طَيِّبَةٍ أَصْلُهَا ثَابِتٌ وَفَرْعُهَا فِي السَّمَاءِ}

አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ (በምድር ውስጥ) የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ (የረዘመች) እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን
[ሱረቱል ኢብራሂም :24]

{وَمَثَلُ كَلِمَةٍ خَبِيثَةٍ كَشَجَرَةٍ خَبِيثَةٍ اجْتُثَّتْ مِن فَوْقِ الْأَرْضِ مَا لَهَا مِن قَرَارٍ}

የመጥፎም ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተጎለሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደኾነች መጥፎ ዛፍ ነው፡፡
[ሱረቱል ኢብራሂም :26]
2.6K viewssⓄz, edited  12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:24:43 ጥያቄ በረሃ ላይ መኪና እያሽከረከራችሁ ነው፣ ደክሞዋችኋል ውሀ ጠምቷችኋል ተርባችኋል....ከዚያም መንገዳችሁ ላይ 3 በሮች መጡ

1ኛው በር ቀዝቃዛ መጠጦች እና ሀይቅ አለ
2ተኛው ምርጥ አልጋ እና ቆንጆ እንቅልፍ አለ
3ተኛው ቆጥራችሁ የማትጨርሱት የገንዘብ ክምችት አለ

የመጀመሪያ የምትከፍቱት የትኛውን በር ነው?

#መልሳችሁን comment ላይ
2.7K views"ųmį¥ę": , 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 09:51:52
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ


#ቁርኣን
2.7K views"ųmį¥ę": , 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ