Get Mystery Box with random crypto!

📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamik_tube — 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖 እ
የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamik_tube — 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖
የሰርጥ አድራሻ: @eslamik_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.31K
የሰርጥ መግለጫ

አሠላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ የቻናሌ ቤተሠቦች👇👇👇
➬እስላማዊ ትምርቶች
➬እስላማዊ ታሪኮችን
➬ሶሒህ የሆኑ ሀዲሶችንም ያገኙበታል!!!
ስለ ቻናሉ ሀሠሳብ
አስተያየት እና cross ለመሠራራት ለምፈልጉ
👉 @Muba_ya👈

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-07-12 21:31:20 ፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 21

ፀሀፊ fuad seid

አኩ ሪቾኮ ራሷን አጠፋች! አለችኝ፡፡ እጄ ስልኬን መሸከም ከበደዉ፡፡ ስልኬ እንደዚህ ይከብድ ነበር እንዴ? ራሄልየተገናኘንበት ምሽት ላይየነገረችኝ ነገር ስንብት መሆኑ ገባኝ ፡፡ ሀዩ አልጋየ ላይ መሆኔን አረጋግጣ የነገረቺኝ ጉዳት እንዳይደርስብኝ በመስጋት ነበር፡፡ እንደነገረችኝ የተኛሁበት ቤት መታ እስክታነሳኝ ድረስ አልነቃሁም፡፡ አሁን ለቅሶ ስደርስ አላፍርም? በኔ ምክንያት ሙታ ሂጄ ባለቅስማላገጥ አይመስልም ሪቾዬ ጠልቻት እኮ አይደለም። ግን ሁኔታዎች
አንድ ላይ እንዳንሆን አደረጉ። ሀይማኖታችን ተለያየ። ምን
ላድርግ? ምን ያህል ታፈቅረኝ እንደነበር እኮ በደንብ ነበር
የምረዳዉ። መላ አካሌን የማዘዝ ስልጣን የነበረዉ ዉበት እኮ
ነበራት። ግን የፈጣሪ ዉሳኔ የሀዩ አደረገኝ። እነዛ ለዛ ያላቸዉ
ግጥሞቿስ? ወይኔ ሪቾዬ! አሁን ማለቃቀሱ ምን ይጠቅማል?
ምንም!!
.
በሀያት አስገዳጅነት የራሄልን ለቅሶ ለመድረስ ሄድን። እስክንድር
ቀድሞን ሄዶ ስለነበር ስንደርስ ተቀበለን። በጣም እየተለቀሰ
ነበር። ሀጅራ ለቅሶ ልትደርስ ከኮምቦልቻ እየመጣች ነዉ። ሪቾ
በመርየም ሰርግ ቀን ራሷን ያላጠፋችዉ ደስታዬን ላለማደብዘዝ
ብላ መሆኑ ገባኝ። እሷ እየተሰቃየች ለኔ ድርብ ደስታ
ትጨነቃለች። ለቅሶ ቤት ገብተን ትንሽ እንደተቀመጥን የራሄል
አባት ወደ ሀያት መጥተዉ የሆነ ነገር አወሯት። ሀዩ ወደኔ
ጠቆመቻቸዉ። አባቷ ወደኔ መጡና "ና እስኪ አንዴ!" ብለዉ
ይዘዉኝ ወደ ዋናዉ ቤት ገቡ። ወደ ራሄል መኝታ ቤት ስንገባ
ራሄል ተገንዛ አልጋዉ ላይ ተጋድማለች። አልተከፈነችም። ከላይ
አንሶላ ለብሳለች። አባትየዉ በሩን ከዘጉት በኋላ አንሶላዉን
ከፊቷ ላይ አነሱት። ራሄል ሞታለች። ሳያት እንባዬ ከአይኔ
ያለማቋረጥ ፈሰሰ። ልቤ በጣም ተነክቷል። አባትየዉ የሆነ
የመድሀኒት ብልቃጥ እየጠቆሙኝ "በዚህ ነዉ ራሷን
ያጠፋችዉ።" አሉኝ። የሰዉ ልጅ ጤዛ ነዉ። አሁን ታይቶ በቅፅበት
ዉስጥ የሚጠፋ። ግን ምንም አይነት ፈተና ቢጋረጥ ነብስ
ማጥፋት በፍፁም እንደመፍትሄ ሊታይ አይገባም። ምክንያቱም
ከዚህ ከተኬደ በኋላ እዛ ሰማይ ቤት የሚጠብቀንን ስቃይ
ካለንበት ችግር ጋር አወዳድረን አላየነዉምና!
.
ትንሽ የአልጋዉ ራስጌ ጋር ተቀምጬ ካነባሁ በኋላ አባትየዉ
አንድ ወረቀት ከኮታቸዉ የዉስጥ ኪስ ዉስጥ አዉጥተዉ ሰጡኝ።
እዛዉ ከፍቼ አነበብኩት። የራሄል ፅሁፍ ነዉ።
"እንደምወድህ ከማዉቀዉ በላይ እንደምትወደኝም አዉቅ ነበር።
አንተን የኔ እንዳትሆን ያገደህ ሀይማኖታችን መለያየቱ ብቻ ነዉ።
ልክ ስታጣኝ እዉነታዉን መጋፈጥ ትጀምራለህ። ሁሌም ደስተኛ
ሆነህ እንድትኖር እመኝልሀለሁ። ግን ናፍቆትህን አልችለዉምና
ሞት እስኪያገናኘን ካላስቸገርኩህ ቢያንስ በአመት አንድ ቀን
መቃብሬ አጠገብ እየመጣህ እንድታጫዉተኝ አደራ እልሀለሁ።
ተዉቤ እጠብቅሀለሁ። አፈቅርሀለሁ።" ይላል።
.
ራሄል የፃፈችዉ ደብዳቤ ዉስጥ አንድም ሀሰት አልነበረም። ግን
ማነዉ ከሴቶች ጋር ጓደኝነት መስርት ያለኝ? ሴትናወንድ መካከል
ተፈጥሯዊ መፈላለግ መኖሩ እንዴት ጠፋኝ? ብሽቅ ነኝ።
ራሄልን እወዳት ነበር። ግን የወደፊት ህይወትን፣ ትዳርን ሳስብ
ሀይማኖታችን መለያየቱ ትዝ አለኝ። እየወደድኳት አታዛልቀኝም
በሚለዉ ሀያትን መረጥኩ። እንጂ እኮ ራሄል አጠገቤ ስትቆም
በራሱ መላ ሰዉነቴን ነበር የምትቆጣጠረዉ። እወዳት ነበር።
የራሄልን ደብዳቤ ጥብቅ አድርጌ ያዝኩት። በህይወት እያለሁ
ላልጥለዉ ለራሴ ቃል ገባሁ።
.
ይቀጥላል.......

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube
3.1K views"ųmį¥ę": , 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:31:20 ፡፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 20

ፀሀፊ fuad seid

ከሀያት ጋር የተጋባንበት እና ባለሚስት የሆንኩበት ቀን አለፈ።
የሴሚስተሩም እረፍት አልቆ ወደ ባህርዳር ተመለስን። በኔና
በሀዩ መካከል ብዙ ነገሮች ተቀየሩ። ከድሮዉ በተለየ ብቻችንን
እናሳልፋለን። እንደልቤ አቅፋታለሁ። እስማታለሁ። ታዲያ ሰዉ
በሌለበት ነዉ። ማንም እና ምንም ሀዩን መንካት አይከለክለኝም።
ምክንያቱም ሚስቴ ነች!!
.
ቅዳሜ ከሰዓት ብዙ ጊዜ ጣና ነዉ የምናሳልፈዉ። ለመጀመሪያ
ጊዜ ከንፈሯን የሳምኳትም ጣና ዳር ተቀምጠን ነዉ። ከንፈር የሆነ
ለየት ያለ ጣዕም አለዉ። ለኔ የሀዩ ከንፈር የምድር ምርጡ
ጣዕም ባለቤት ነዉ። ምክንያቱም ከሀዩ ዉጪ ሌላ ሴት እንዲህ
በወጉ ስሞኝ አያዉቅም። ያለዉድድር ከንፈሯ አሸንፏል። በርግጥ
ሪቾ አንዴ ከንፈሬን ስማኝ ነበር ግን ላስታዉሰዉ አልፈልግም።
ካስታወስኩት ብዙ ነገሮች አብረዉ ይታወሱኛል።
.
የሴሚስተሩ ማለቂያ ሲደርስ አባቴ ደዉሎ መርየም ልታገባ
መሆኑን አበሰረኝ። ታናሽ እህቴ ፈለጌን ስለተከተለች ደስ አለኝ።
የምታገባዉም ልጅ በስነ ምግባሩ መልካም የሚባል አይነት ነዉ።
ኒካሁ በሌለሁበት ተደርጎ ሰርጉን ክረምት ስመለስ ለማድረግ
ነዉ ያቀዱት። ህይወቴ በደስታ ተሞላች።
.
የሪቾ ፍቅረኛ እስክንድር ወደ ማታ ደዉሎ ላግኝህ አለኝ።
ምሽቱን ሀያት ቤተ መፅሀፍ ስለነበረች ብቻዬን አገኘሁት።
ግቢያችን ዉስጥ ሜንላዉንጅ የሚባለዉ ቦታ ተቀምጠን አንዳንድ
ነገሮችን ካወራን በኋላ ሊያገኘኝ ወደ ፈለገበት ጉዳይ ገባን።
"ራሄልን ግን በደንብ አስተዉለሀታል?" አለኝ ትኩር ብሎ እያየኝ።
እዉነት ለመናገር ከጋብቻዉ በኋላ ብዙም ትኩረቴ ወደሷ
አልነበረም። በርግጥ የምግብ ሰዓቶች ላይ እንደድሮዉ አብረን
ነዉ የምንበላዉ።
ዝም ስለዉ "አኩሻ ጤናዋ እየተዛባ ነዉ።" አለኝ።
"እንዴት?" አልኩት ያላስተዋልኩትን ነገር ስለነገረኝ እየተገረምኩ
"አክረሜ ገና አንተ የሀያት እንደሆንክ ካወጅክ ጀምሮ ደህና
አይደለችም። ፈገግታዋ እና ጨዋታዋ ሁሉ አንተን ደስ ለማሰኘት
እንጂ የእዉነት አይደለም። እየሳምኳት ራሱ የምትጠራዉ ያንተን
ስም ነዉ። ዛሬም ከምንም በላይ ታፈቅርሀለች።" አለኝ።
በነገረኝ ነገር በጣም አዘንኩ። ግን ምን ማድረግ እችላለሁ? እኔ
አሁን ባለትዳር ነኝ።
"ምን ማድረግ የምችል ይመስልሀል?" አልኩት እስክንድርን
"ቢያንስ ቀረብ ብለህ እንደድሮዉ አዉራት፣ አማክራት።" አለኝ።
እስክንድር ምን ያህል ጉዳዩ እንዳሳሰበዉ ከፊቱ ይነበባል።
.
በነጋታዉ ክፍል ዉስጥ እየተማርን ሪቾ ራሷን ስታ ወደቀች።
የተቀመጠችዉ ከአጠገቤ ስለነበር አቅፌ ከክፍሉ ይዣት ወጣሁ።
እነሀያት ዉሀ ገዝተዉ መጡና ሰዉነቷን ለማቀዝቀዝ ሞከርን።
ልክ እንደነቃች አይኗን ስትገልፅ እቅፌ ዉስጥ ነች። ድክም ባለ
ፊቷ ላይ ፈገግታ ለመርጨት እየሞከረች "እዚህ እቅፍ ዉስጥ
እንኳ ብሞትም አይቆጨኝም!" አለችኝ። ደግነቱ ሀዩ ሪቾ ስትነቃ
የምትበላዉ ነገር ልግዛ ብላ ሄዳ ነበር። ከእቅፌ አዉጥቼ
አስተካክዬ ላስቀምጣት ስል ገና አካላቶቿ መታዘዝ
አልጀመሩም። እዛዉ እቅፌ ዉስጥ እንዳለች ማዉራት ጀመርን።
"መቼ ነዉ የጀመረሽ? ማለቴ ህመሙ?" አልኳት።
"ትንሽ ቆየ ባክህ! ጤናዬ አንተ ነበርክ ፤ የኔ እንደማትሆን
ካወቅኩ ጀምሮ ሰላም አይደለሁም።" አለችኝ።
ያኔ ሽንፈቷን በፀጋ ተቀበለች ብዬ ተገርሜ ነበር። ለካ በዉስጧ
አፍናዉ ነበር።
.
የሴሚስተሩ ትምህርት እንዳለቀ ለክረምት ወደ አዲስ አበባ
ተመለስን። እህቴ መርየም ኒካህ አድርጋለች። አሁን ሰርጉ
ሊደገስ ነዉ። ከባህርዳር እንደተመለስን ራሄል በተደጋጋሚ
ልታገኘኝ እንደምትፈልግ ብትነግረኝም ሀዩ ሊከፋት ይችላል
በሚል ሳላገኛት ቀረሁ። እሁዱን የመርየም ሰርግ ሊካሄድ
ቅዳሜዉን ሴቶቹ እኛ ቤት ተሰብስበዉ እየጨፈሩ ነዉ። እኔ ሰርግ
ላይ ሴቶቹ ሲጨፍሩ የሚሏቸዉ ግጥሞች ስለሚያዝናኑኝ በቅርብ
ርቀት ከሰዒድ ጋር ሆኜ እሰማለሁ። አንድ የጎረቤታችን ልጅ
እያወጣች ሌሎቹ እየተቀበሉ እንዲህ አሉ
"ሽንኩርት ከተፍ ከተፍ ፣ ሽንኩርት ከተፍ ከተፍ፣
ያላገባ ካለ ፣ አሁን ይቀላጠፍ።" ሰዒድን እያየሁት እስቃለሁ።
ኢስራዕ ማዉጣት ጀመረች፣ ሌሎቹ ይቀበላሉ
"በጎድጓዳ ሳህን፣ ይመታል አብሽ፣
የኔማ መርየሜ፣ የቀይ ድንቡሽቡሽ።
መስታወት ፊት እንጂ ፣ አያሳይም ሀገር፣
አደራ ጌታዬ ፣ የመርየምን ነገር።" አለችና ዛቻናልመና የቀላቀሉ
ግጥሞችን ማዉጣት ጀመረች።
"መርየም ዘረ ብዙ ፣ መርየም ዘረ ብዙ፣
ትናገራትና ብዙ ነዉ መዘዙ።
አምናም አጨብጫቢ ፣ ዘንድሮም አጃቢ፣
ኧረ የኛን ነገር ፣ ያረቢ ያረቢ።"
.
ከሰዒዶ ጋር ግጥሞቹን ተመስጠን እያዳመጥን ሪቾ ደወለች።
"ወዬ ሪቾዬ" አልኩ ስልኩን አንስቼ።
"አክረሜ እንዴት ነህልኝ?" አለች።
"የራሄል አምላክ ይመስገን ደህና ነኝ!" አልኳት እየሳቅኩ።
"አሁን ሰፈራችሁ ነኝ። አስፓልቱ ጋር ና ላግኝህ።" አለችኝ።
ሄጄ አገኘኋት። የአባቷን መኪና ይዛ ነበር የመጣችዉ። መኪናዉ
ዉስጥ ገብቼ ማዉራት ጀመርን። ቆይ ግን ምድር ላይ የቀረሁት
ወንድ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ? ይሄን የመሰለ ዉበት ይዛ እኔን ደጅ
መጥናቷ ጨነቀኝ። ሪቾኮ በጣም ዉብ ናት። ድሮም ፎንቃ ይሉት
ነገር መዘዙ ብዙ ነዉ። ይኸዉ ሪቾን ራሱ አሳመመብኝ።
ሪቾ ብዙ የማላዉቃቸዉ በህይወቷ ዉስጥ ተፈጥረዉ የነበሩ
ነገሮችን ተረከችልኝ። ከዛም አይን አይኔን እያየች "አክረሜ
ሁሌም እወድሀለሁ ግን ከዚህ በላይ መሰቃየት አልችልም።
ከዚህ በኋላም የማስቸግርህ አይመስለኝም።" አለችኝ። እንባዋ
ከአይኖቿ ፈሰሰ። በጣም ልቤን ነካችዉ። እጆቼ እንባዋን ሊጠርጉ
ወደ ጉንጮቿ ሄዱ። ያዘቻቸዉ! ሁለቱንም መዳፎቼን ሳመቻቸዉ።
ልቤ ስፍስፍ ብሏል። እጆቼን በኃይል ጎትታ ከንፈሮቼን ወደ
ከንፈሮቿ አስጠጋች። ልቤ ቀጥ አለ። የማስቆምበት አቅም
አልነበረኝም። ሁሉ ነገሬን ተቆጣጥራዋለች። ወዲያዉ ስልኬ
ጠራ። ተመስገን ሙዷን አወረደዉ። ለቀቀችኝና መሪዉ ላይ
ተኛች። ሀዩ ነበረች የደወለችዉ። አነሳሁት። ቤት እንደመጣች እና
ቶሎ እንድመጣ ነገረችኝ። ዛሬ ያዉ የባሏ እህት ሰርግ ዋዜማም
አይደል? ለሊቱን ከእህቶቼ ጋር ሲጨፍሩ ሊያድሩ ነዉ።
ስልኩን አናግሬ ስጨርስ ራሄል ከመሪዉ ላይ ፊቷን አንስታ
በሶፍት እንባዋን እየጠራረገች "በቃ ልሂድ!" አለችኝ። ትክዝ ብዬ
አየኋትና "አላህ ይጠብቅሽ!" አልኳት። አትሄጂም ብዬ በሆነ
ተዓምር ሚስቴ መሆኗን ባስረዳት ደስ ይለኝ ነበር። ግን
እዉነታዉ ሪቾ ሚስቴ ያለመሆኗ ሀቅ ነዉ።
.
የሰርጉ ቀን አልፎ በማግስቱ ራሄል አራት ነጥብ በሚሴጅ
ላከችልኝ። ትርጉሙ አልገባኝም ነበር። ስደዉልላት አታነሳም።
በነጋታዉ ጠዋት ሀያት ደወለችልኝ "አኩዬ የት ነህ?" አለችኝ።
"ቤት ነኝ ሀዩዬ!" አልኳት።
"እሺ አልጋህ ላይ በወገብህ ተኛ አንዴ!" አለችኝ። ዛሬ ደሞ ምን
አይነት ሮማንስ ነዉ ባካችሁ?
"አንቺ አዘሽኝ አይደለም አልጋ ላይ የጦር ጫፍ ላይ አልተኛም
ብለሽ ነዉ?" አልኩ እንዳዘዘችኝ በወገቤ አልጋዉ ላይ
እየተጋደምኩ።
"እሺ አኩዬ እንዳልኩህ ተኛህ?" አለችኝ።
"አዎ ሁቢ አሁን ምን ላድርግ?" አልኳት።
መጋደሜን እንዳረጋገጠች ድምጿ በሳግ እየታፈነ "አኩዬ

ይቀጥላል...........

ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ከፈለጉ ይቀላቀሉን
@eslamik_tube
3.0K views"ųmį¥ę": , 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:27:48 ፡፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 19

ፀሀፊ fuad seid


ግን እዉነታዉ ይህ አይደለም፡፡ትዳር ተፈጥሯዊ ተቋም ነው፡፡የሰዉ ልጅ ስሜት በተፈጥሯዊ መንገድ
መርካት አለበት። ለዚህ ደግሞ ትዳር የመጀመሪያዉ እና
የመጨረሻዉ አማራጭ ነዉ። ይሄ ተቋም በቀላሉ እንዲመሰረት
ወላጆች ልጆቻቸዉን ሊያግዙ ይገባል። አሁን ግን ትዉልዱ
የትዳርን በር ጠርቅሞ የዝሙትን በር ከበረገደዉ ቆይቷል።
የተዘጋዉ በር ሊከፈት ግድ ይላል!!
.
በነጋታዉ አምስት ሰዓት አካባቢ ወደነሀያት ቤት ሄድን። ኒካህ
ስለሆነ ግርግር አላበዛንም። በሶስት መኪና ነበር የሄድነዉ።
ሰዒድም ከኛ ጋር መጥቷል። እነሀያት ቤት ስንደርስ የሴቶቹ
ጭፈራ ለጉድ ነዉ። መድረሳችንን ሲያዉቁ ደግሞ ጭፈራዉን
የበለጠ አደመቁት። ቤተሰቦቿ በር ላይ ወጥተዉ ተቀበሉንና ወደ
ዉስጥ ገባን። የሴቶቹ የጭፈራ ድምፅ ይሰማኛል። እዚህ ደግሞ
ሀዩን እያሞገሱ እኔን ይነቁራሉ። ስገምት መግፊራ ትመስለኛለች
አሊያም ሌላ ሰዉ የሚያወጣዉ እንዲህ አሉ
"ለምነህ ለምነህ ፣ተሀጁድ ሰግደህ
እንዲሁም አልቀረህ ሀዩን አገኘህ።" ተሀጁድ በለሊት ሰዉ
በተኛበት የሚሰገድ ስግደት ነዉ።
ነቆራቸዉን ቀጠሉ
"ነጭ ትለብሳለች ፣ ነጭ ትወዳለች
እዉነት ለመናገር ትቦንሰዋለች።
እንቁላል ቢሰበር እንቁላል ይተካል፣
የኔማ ሀዩዬ ፣ አይኗ ብቻ ይበቃል።"
"ሰዒድ እየሳቀ ኧረ በግጥም ወረዱብን እኮ!" አለኝ። "ሀዩን
ሊሰጡንማ ቢገርፉንም እንችለዋለን።" አልኩት እየሳቅኩ።
.
ገብተን ትንሽ እንደተቀመጥን የኒካህ ዝግጅቱ ተጀመረ።
በሀይማኖታዊ ስርዓቱ መሰረት የጋብቻ ንግግር በሀይማኖት
አዋቂ ተደርጎ ሀያት ጥሎሽ የምትጠየቅበት ሰዓት ደረሰ። ለወጉ
ሁለት ሺህ ብር አለች። ወዲያዉ ጥሎሹን ሰጥተን የጋብቻ
ወረቀቱ ላይ ተፈራረምን። ሀዩን አገባኋት። ልክ ሀያት ያለችበት
ክፍል ወረቀቱ ተልኮ ስትፈርም ሴቶቹም ግጥማቸዉን
ሁለታችንንም የሚያወድስ አደረጉት
" ከዚህ እስከመስጂዱ ወርቅ ይነጠፍበት፣
አክረምና ሀዩ፣ ይመላለሱበት።
ጥቁር ይወዳሉ ጥቁር ይለብሳሉ፣
ለሀቁ ከሆነ ይመጣጠናሉ።" በድቤ ታጅቦ በሴቶቹ ዉብ ድምፅ
ይቀለፃል። ከሁሉም ያሳቀኝ ግጥም
"ግቢያችሁን እጠሩት ዳር ዳሩን አጥር፣
እስከአሁን ፆመሀል ከእንግዲህ አፍጥር።" የሚለዉ ነዉ።
እስከአሁን ፆመሀል ያሉት ከሚስት ጋር ሊደረጉ ከሚችሉ ነገሮች
ሁሉ ነዉ። እና ይኸዉ በሀዩ አፍጥር(ፆምህን ግደፍ) ማለታቸዉ
ነዉ።
.
ቤተሰቦቿ ሀዩን ለኔ መፍቀዳቸዉን ለማብሰር ግንባሯን
እንድስማት እሷ ወዳለችበት ክፍል ይዘዉኝ ሄዱ። ሀዩ በጣም
ተዉባ በሚያማምሩ ሴቶች ተከባ ተቀምጣለች። ራሄልም አብራት
ነበረች። ሚዜ አይደለችም ግን ሀዩን አጅባ ተቀምጣለች። ዛሬ
ሪቾዬን ባገባ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ሳያት አሳዘነችኝ። እኔን
የምታጣበት ድግስ ላይ መገኘቷ ግርም ብሎኛል። ምን አይነት
መቻል ይሁን ፈጣሪ የሰጣት? እስክንድር ጉዳይዋ እንዳልሆነ
በደንብ አዉቃለሁ። አይኗን ከኔ ለማዞር እንዲያግዛት ነዉ
የተወዳጀችዉ። ሪቾን ሳላስባንን አየኋትና የሀዩን የአይንእርግብ
ገልጬ ግንባሯን ሳምኳት። ሴቶቹ እልልታዉን አቀለጡት።
የማህበረሰቡን እሴት ስትጠብቅ ወላጅ እንዲህ እልል እያስባለ
ልጁን ያስምሀል።
.
ይቀጥላል.........

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube
3.4K views"ųmį¥ę": , 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:27:48 ፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡

ክፍል 18

ፀሀፊ fuad seid

ከሀያት ጋር ከታረቅንና ለመጋባት ከወሰንን በኋላ በአራታችን
መካከል የነበረዉ የቀድሞዉ የጓደኝነት መንፈስ ተመለሰ።
ከሀያት ጋር ኒካህ ለማሰር መወሰኔን ቀድሜ ደዉዬ የነገርኩት
ለሰዒድ ነበር። ለልብ ጓደኛዬ! የእዉነት እኔ ሳይሆን እሱ
የሚያገባ ያህል ነበር የተደሰተዉ። በነገራችን ላይ እህቶቼ
መርየምና ኢስራዕ ከኔ ጋር ያላቸዉ ቅርበት ጨምሯል። ቢያንስ
በሳምንት ሶስት ቀን ይደዉሉልኛል።
የሀያት እህት መግፊራ ደወለችልኝና "የክፍለ ዘመኑን ምርጥ
ዉሳኔ ነዉ የወሰንከዉ!" አለችኝ እየሳቀች። እሷም እንደእህቷ
ፍልቅልቅ ናት።
"የእህትሽን ባል እንዲህ ነዉ የምታናግሪዉ? አክብሪኝ እንጂ!"
አልኳት እየሳቅኩ። በዉሳኔያችን በጣም መደሰቷን ነግራኝ
አንዳንድ ነገሮችን አወራን።
እኔ የመጀመሪያ ስራ ብዬ ያቀድኩት እህቶቼን ከሀዩ ጋር
ማስተዋወቅ ነዉ። እነሱ ከወደዷት እናቴ ላይ በጣም ተፅዕኖ
ይፈጥራሉ። ለነገሩ ከእናቴ ጋር ቀረቤታም ስለሌለኝ እነሱዉ
ቢጨርሱልኝ ይሻላል። ለእህቶቼ ዉሳኔዬን ነግሬ የሀያትን ፎቶ
ቫይበር ላይ ላኩላቸዉ። በፎቶ ወደዋት ሊሞቱ ምንም
አልቀራቸዉም። ስልኳን ሰጥቼያቸዉ ተዋወቋት። በዉሳኔያችን
መደሰታቸዉንም ነገሯት። ይህቺ የደስታናየሀዘን መግለጫ
በመንግስታት ብቻ ሳይሆን በግለሰብም ደረጃም አለች።
ከእህቶቼ ጋር በደንብ ካስተዋወቅኳት በኋላ ለአባቴ ደዉዬ
ነገርኩት። አባዬ "ኒካህ ማሰርህ ደስ ይለኛል ግን የልጅቷን
መልክ ብቻ አይተህ ከሆነ አይሆንም።" አለኝ። በሱ የደረሰዉ በኔ
እንዳይደገም ብሎ ይመስለኛል። እናቴ ቆንጆ ናት ግን ምንም
ስርዓት የላትም። ይኸዉ ህይወቱን ሙሉ ስታቆስለዉ እና
ሲደበድባት አለች። ከዚህ ቀደምም ወደፊት ሳገባ ስነ ምግባሯ
ያማረ ሴት እንድመርጥ መክሮኝ ያዉቃል። እኔም ከሀዩ ጋር
ያለንን ቅርበት ፣ ስነ ስርዓቷን ፣ ሀይማኖቷ ላይ ያላትን እዉቀት
ስነግረዉ "እንደዛ ከሆነች መህር(ጥሎሽ) አንድ ሚሊየን ብር
ብትጠይቅህ ደስ እያለኝ እኔ እሰጥሀለሁ።" አለኝ። አባቴ ስልኳን
ወስዶ ሀያትን አወራት። የሀያት ቤተሰቦችም ደዉለዉ ብዙ ነገር
አወሩኝ። እንግዲህ መተጫጨቱ ተጧጡፏል።
እናቴ ቅር እንዳይላት ብዬ ደወልኩና ኒካህ ለማሰር ማሰቤን
ነገርኳት። "ልጅቷ ከየት ናት?" አለችኝ አስቀድማ! ሰዉ አሁን
ብሔር ላይ ምን እንዲህ ያጣድፈዋል? ድሮም እኮ እናቴ ሸሯ
ይቀድማል። ግን ደስ የሚለዉ የሀዩ ቤተሰቦችና የእናቴ ብሔር
ተመሳሳይ ነበር። እንጂማ አይሆንም ብላ ቀዉጢ ትፈጥር ነበር።
አዲስ አበባ ታድጎ እንዴት ብሔር እንደ ዋና መስፈርት ይታያል?
ድድብና ነዉ!
የሀዩ እና የእኔ ቤተሰቦች እነ ሀያት ቤት ተገናኝተዉ ጉዳዩ ላይ
መከሩበት። ኒካህ ልክ ሴሚስተሩ አልቆ በመጣን በሳምንቱ
እንዲደረግ እና ትምህርታችንን እስከምንጨርስ በየቤታችን
እንድንኖር ወሰኑ። ይህ ሁሉ ነገር ሲካሄድ እኔና ሀዩ ባህርዳር
ነን።
ዉሳኔያቸዉን ስንሰማ ትዳር ምን ያህል ቤተሰብ የበላይ ጠባቂዉ
ሆኖ ሲደግፈዉ ደስ እንደሚል ተረዳን። ምናለ ሁሉም በስሜት
ተቃጥሎ ፍቅረኛ የሚሉት የዝሙት መንደርደሪያ ላይ ከሚቆምና
ቁልቁል ተንደርድሮ ዝሙት ዉስጥ ከሚዘፈቅ ቤተሰብ አጋብቶ
ራሳቸዉን ሲችሉ አብረዉ መኖር እንዲጀምሩ ቢያደርግ?
ማህበራዊ ቀዉሱን በጣም መቀነስ ይቻል ነበር።
አሁን እኔናሀዩ ፈተና ጨርሰን ወደ ሸገር ስንመለስ ኒካህ
እናስራለን። ይሄ ማለት ሀዩ ሚስቴ ሆነች ማለት ነዉ። ኒካህ
ከታሰረ በኋላ ብስማት አሊያም ብተኛት ዝሙተኛ አይደለሁም።
ሚስቴ ነቻ! ግን በቤተሰቦቻችን ዉሳኔ መሰረት ትምህርት
እስከምንጨርስ የምንኖረዉ በየቤታችን ነዉ።
ራሄል የሀያት እና የኔ ጉዳይ መስመር ሲይዝ ፤ ዘወትር
ካልተነጠፍንልሽ ከሚሏት ወንዶች አንድ ጨዋ የሆነ እስክንድር
የሚባል የነሱ ቸርች ልጅ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀመረች። ከጎኗ
የሲጃራ ፓኮ አዉጥቶ አንዱን የመምዘዝ ያህል ነበር
ያቀለለችዉ። ድሮም እኔን ብላ እንጂ እንኳን የሱ ልትባል ቀርቶ
አብሯት ስለቆመ የአደም ዘር በሙሉ የሚኮራባት አይነት ዉብ
ልጅ ነች። በርግጥ ትንሽ ዉጥረቷን ለማርገብ እንዲረዳት ብላ
እንጂ ልጁን አፍቅራዉ አይደለም። እስክንድር የጓደኝነት ክበባችን
ዉስጥ ሲጨመር አምስት ሆንን። እስክንድር ተጫዋች ነዉ። እኔ
በጣም ተመችቶኛል። ኢኮኖሚክስ የሚያጠና የሸገር ልጅ ነዉ።
ፈተና እንዳለቀ ወደ አዲስ ለመመለስ ተነሳን። እንደተለመደዉ
ሀጅራ ወደ ኮምቦልቻ በጠዋት ሄደች። እኔ ፣ ሀዩ ፣ ሪቾ እና
እስክንድር ደግሞ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዲስ አበባ በረርን።
በረራዉ እንደተጀመረ ሀዩ ወደኔ ዞር አለችና "ለኒካሁ አንድ
ሳምንት አብሮ መኖር ለመጀመር አንድ አመት ከአንድ ሴሚስተር
ቀረን!" አለችኝ።
ገና ከአሁኑ ቀን መቁጠር መጀመሯ አሳቀኝ። ነገ አይንህ ይበራል
ቢባል ዛሬን እንዴት አድሬ እንዳለዉ አይነስዉር ሆነችብኝ።
አዲስ አበባ በገባን በሳምንቱ እሁድ ቀን የኒካህ ዝግጅቱ
እንዲደረግ ተወሰነ። እኛ ቤት የድግሱ ዝግጅት ሰርግ ነዉ
የሚመስለዉ። ሞቅ አድርገዉታል። ገና ቅዳሜዉን ድንኳን
ደኩነዋል። ሴቶቹ ቤት ዉስጥ ግጥም እየገጠሙ ፣ ከበሮ
እየመቱ ጭፈራዉን ያስነኩታል። ሴቶቹ የሚገጥሙት ግጥም
ብዙዉን እኔን የሚያሞግስ ነበር። ከሰዒድ ጋር ከሚጨፍሩበት
ክፍል አጠገብ ትንሽ ቆመን ሰማናቸዉ። መርየም ታወጣለች
ሌሎቹ ይቀበላሉ።
"የወንድ ልጅ ሱሪ ፣ያልቃል ከጉልበቱ፣
አክረሜን አትንኩት፣ አንድነዉ ለእናቱ።
እንጀራዉን ጋግሩ ፣ በስሱ በስሱ
አክሩ እና ሀዩዬ ፣ እንዲጎራረሱ።" ይላሉ በየመሀሉ ከበሮዉ
ይደለቃል። ዜማቸዉ ቀልብን ይገዛል። የሚሏቸዉ ግጥሞች እኔን
ከማሞገስ ባለፈም ላላገቡት መልዕክት የሚያስተላልፉ ነበሩ።
ኢስራዕ እያወጣች ሌሎቹ እየተቀበሉ
"በፌስቡክ በዋትስአፕ ፣ ከምትጀነጅናት፣
ምትወዳት ከሆነ ፣ ኒካህ እሰርላት።" ፈገግ አልኩና "ሰዒዶ እኔ
እንግዲህ ላገባ ነዉ ይሄ ላንተ ይመስላል። ምትጀነጅናት ካለች
መክረዉሀል።" አልኩት።
እኔ ከሰዒድ ጋር ለኒካሁ ቀን የሚያስፈልጉኝን አልባሳት ገዛዝቼ
ጨርሻለሁ። በተለምዶዉ ሙሽራዉ የኒካህ ቀን ሙሽራዋን
ወደቤቱ የማይወስዳት ከሆነና ከዛ በኋላ በሰርግ ሊወስዳት
ካሰበ ሙሽራዋ በኒካሁ ቀን ወደ ወንዱ ቤት አትሄድም። እኛ ጋር
ግን አባዬ ድግስ ስለደገሰና እንዲደምቅ ስለፈለገ ሀያት መጥታ
ትንሽ ድግሱን አድምቃ እንድትመለስ አባቴ ከቤተሰቦቿ ጋር
ተስማምቷል።
ኒካሁ ነገ ሊሆን ቅዳሜ ማታ ሁለት አሮጊቶች ድንኳኑ ዉስጥ
ቁጭ ብለዉ ያወራሉ። እኔ በድንኳኑ ጀርባ በኩል ነኝ። አያዩኝም።
"ቆይ ልጁ መች ከሀያ አመት ዘለለ እና ነዉ ለጋብቻ ያስሮጠዉ?"
አለች አንዷ ሴትዮ
"ምን የዛሬ ልጆች ገና ቂጣቸዉን ሳይጠርጉ ነዉ ሚስት ማለት
የሚጀምሩት!" አለች ሁለተኛዋ አሮጊት!
ሳላስባንን በድንኳኑ በር በኩል እያለፍኩ አሮጊቶቹ እነማን
እንደሆኑ ተመለከትኩ። የአንዷ ልጅ ሳታገባ ዲቃላ አንጠልጥላ
ይዛባት መጥታ አሮጊቷ እያሳደጉ እንደሆነ መርየም ነግራኝ
ነበር። ታዲያ ምን ታድርግ ትዳርን እንዲህ ቅዠት አድርጋ
የምታሳይ እናት ካለቻት ሌላ አማራጭ መፈለጓ አይቀሬ ነዉ።
ሁለተኛዋ ደግሞ ልጇ ብዙም ወጣ ያለ ባይሆንም ፍቅረኛ
እየቀያየረ ስሜቱን ሲያስታግስ የኖረ ነዉ።
አሁን የልጆቹ ዝቅጠት መነሻ ወላጆቹ መሆናቸዉ ገባኝ። ገና ስለ
ትዳር ሲነሳ የሆነ ሆረር ፊልም አድርገዉ ያሳዩሀል። አንተ
መወጣት የማትችለዉ የሀላፊነት መዓት የተደረደረበት መጋዘን
አድርገዉ ይነግሩሀል። ምንም ደስታ የሌለበት የችግር መሰረት
አድርገዉ ይስሉልሀል።

@eslamik_tube
3.2K views"ųmį¥ę": , 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ