Get Mystery Box with random crypto!

፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡ ክፍል 21 ፀሀፊ fuad seid አኩ ሪቾኮ ራሷን | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 21

ፀሀፊ fuad seid

አኩ ሪቾኮ ራሷን አጠፋች! አለችኝ፡፡ እጄ ስልኬን መሸከም ከበደዉ፡፡ ስልኬ እንደዚህ ይከብድ ነበር እንዴ? ራሄልየተገናኘንበት ምሽት ላይየነገረችኝ ነገር ስንብት መሆኑ ገባኝ ፡፡ ሀዩ አልጋየ ላይ መሆኔን አረጋግጣ የነገረቺኝ ጉዳት እንዳይደርስብኝ በመስጋት ነበር፡፡ እንደነገረችኝ የተኛሁበት ቤት መታ እስክታነሳኝ ድረስ አልነቃሁም፡፡ አሁን ለቅሶ ስደርስ አላፍርም? በኔ ምክንያት ሙታ ሂጄ ባለቅስማላገጥ አይመስልም ሪቾዬ ጠልቻት እኮ አይደለም። ግን ሁኔታዎች
አንድ ላይ እንዳንሆን አደረጉ። ሀይማኖታችን ተለያየ። ምን
ላድርግ? ምን ያህል ታፈቅረኝ እንደነበር እኮ በደንብ ነበር
የምረዳዉ። መላ አካሌን የማዘዝ ስልጣን የነበረዉ ዉበት እኮ
ነበራት። ግን የፈጣሪ ዉሳኔ የሀዩ አደረገኝ። እነዛ ለዛ ያላቸዉ
ግጥሞቿስ? ወይኔ ሪቾዬ! አሁን ማለቃቀሱ ምን ይጠቅማል?
ምንም!!
.
በሀያት አስገዳጅነት የራሄልን ለቅሶ ለመድረስ ሄድን። እስክንድር
ቀድሞን ሄዶ ስለነበር ስንደርስ ተቀበለን። በጣም እየተለቀሰ
ነበር። ሀጅራ ለቅሶ ልትደርስ ከኮምቦልቻ እየመጣች ነዉ። ሪቾ
በመርየም ሰርግ ቀን ራሷን ያላጠፋችዉ ደስታዬን ላለማደብዘዝ
ብላ መሆኑ ገባኝ። እሷ እየተሰቃየች ለኔ ድርብ ደስታ
ትጨነቃለች። ለቅሶ ቤት ገብተን ትንሽ እንደተቀመጥን የራሄል
አባት ወደ ሀያት መጥተዉ የሆነ ነገር አወሯት። ሀዩ ወደኔ
ጠቆመቻቸዉ። አባቷ ወደኔ መጡና "ና እስኪ አንዴ!" ብለዉ
ይዘዉኝ ወደ ዋናዉ ቤት ገቡ። ወደ ራሄል መኝታ ቤት ስንገባ
ራሄል ተገንዛ አልጋዉ ላይ ተጋድማለች። አልተከፈነችም። ከላይ
አንሶላ ለብሳለች። አባትየዉ በሩን ከዘጉት በኋላ አንሶላዉን
ከፊቷ ላይ አነሱት። ራሄል ሞታለች። ሳያት እንባዬ ከአይኔ
ያለማቋረጥ ፈሰሰ። ልቤ በጣም ተነክቷል። አባትየዉ የሆነ
የመድሀኒት ብልቃጥ እየጠቆሙኝ "በዚህ ነዉ ራሷን
ያጠፋችዉ።" አሉኝ። የሰዉ ልጅ ጤዛ ነዉ። አሁን ታይቶ በቅፅበት
ዉስጥ የሚጠፋ። ግን ምንም አይነት ፈተና ቢጋረጥ ነብስ
ማጥፋት በፍፁም እንደመፍትሄ ሊታይ አይገባም። ምክንያቱም
ከዚህ ከተኬደ በኋላ እዛ ሰማይ ቤት የሚጠብቀንን ስቃይ
ካለንበት ችግር ጋር አወዳድረን አላየነዉምና!
.
ትንሽ የአልጋዉ ራስጌ ጋር ተቀምጬ ካነባሁ በኋላ አባትየዉ
አንድ ወረቀት ከኮታቸዉ የዉስጥ ኪስ ዉስጥ አዉጥተዉ ሰጡኝ።
እዛዉ ከፍቼ አነበብኩት። የራሄል ፅሁፍ ነዉ።
"እንደምወድህ ከማዉቀዉ በላይ እንደምትወደኝም አዉቅ ነበር።
አንተን የኔ እንዳትሆን ያገደህ ሀይማኖታችን መለያየቱ ብቻ ነዉ።
ልክ ስታጣኝ እዉነታዉን መጋፈጥ ትጀምራለህ። ሁሌም ደስተኛ
ሆነህ እንድትኖር እመኝልሀለሁ። ግን ናፍቆትህን አልችለዉምና
ሞት እስኪያገናኘን ካላስቸገርኩህ ቢያንስ በአመት አንድ ቀን
መቃብሬ አጠገብ እየመጣህ እንድታጫዉተኝ አደራ እልሀለሁ።
ተዉቤ እጠብቅሀለሁ። አፈቅርሀለሁ።" ይላል።
.
ራሄል የፃፈችዉ ደብዳቤ ዉስጥ አንድም ሀሰት አልነበረም። ግን
ማነዉ ከሴቶች ጋር ጓደኝነት መስርት ያለኝ? ሴትናወንድ መካከል
ተፈጥሯዊ መፈላለግ መኖሩ እንዴት ጠፋኝ? ብሽቅ ነኝ።
ራሄልን እወዳት ነበር። ግን የወደፊት ህይወትን፣ ትዳርን ሳስብ
ሀይማኖታችን መለያየቱ ትዝ አለኝ። እየወደድኳት አታዛልቀኝም
በሚለዉ ሀያትን መረጥኩ። እንጂ እኮ ራሄል አጠገቤ ስትቆም
በራሱ መላ ሰዉነቴን ነበር የምትቆጣጠረዉ። እወዳት ነበር።
የራሄልን ደብዳቤ ጥብቅ አድርጌ ያዝኩት። በህይወት እያለሁ
ላልጥለዉ ለራሴ ቃል ገባሁ።
.
ይቀጥላል.......

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube