Get Mystery Box with random crypto!

📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamik_tube — 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamik_tube — 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖
የሰርጥ አድራሻ: @eslamik_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.31K
የሰርጥ መግለጫ

አሠላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ የቻናሌ ቤተሠቦች👇👇👇
➬እስላማዊ ትምርቶች
➬እስላማዊ ታሪኮችን
➬ሶሒህ የሆኑ ሀዲሶችንም ያገኙበታል!!!
ስለ ቻናሉ ሀሠሳብ
አስተያየት እና cross ለመሠራራት ለምፈልጉ
👉 @Muba_ya👈

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-20 07:55:06
   በልብሶቻችሁ ከማጌጣቹህ በፊት በህሊናቹህ አጊጡ፡፡ የአንድ አበባ ውበት ሽታ ከሌለው ሙሉ አይሆንም፡፡

መልካም የስራ ሳምንት
:¨·.·¨: ❀
@Eslamik_Tube||ኢስላሚክ Tube
2.6K views"ųmį¥ę": , 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 20:54:05 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
#እውነተኛ_ታሪክ

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_ሶስት ʕ➌ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ሀናን ሀፍሲ ከቀጠረቻት ቦታ ስደርስ ሀፍሲ ጭንቅላቷን ጉልበቷ ላን ደፍታ ስታለቅስ አገኘቻት። አልቅሳ ይውጣላት ብላ አቅፋት ዝም አለች፤ ሀፍሲ ሀኑን ስታገኝ እስከዛሬ ታምቆ የነበረው እምባዋ ያለገደብ ወረደ፤ ሀዘኗን በእንባዋ ጎርፍ ምትሸኘው ነበር ምትመስለው። ሀኑ የሀፍሲን መረጋጋት እየጠበቀች አንድም ቃል ሳትተነፍስ በስስት ታያት ነበር።
..............................................................
ሀፍሲ አሁን ተረጋግታለች፤ "ይቅርታ ሀኑ በማታውቂው ነገር አልቅሼ አሴጨነኩሽ አይደል? ያው ታውቂያለሽ እንዳንቺ ምቀርበው አንድም ሰው የለም፤ እስከዛሬም አምቄ የያዝኩት እናንተን ሳላስጨንቅ ብቻዬን ቀና ለማለት ነበር፤ ግን አልቻልኩም። ዛሬ ደርሼ ደከምኩብሽ፤ ዛሬ ከትላንት የተሻለ ይሆናል ብዬ ነበር፤ ግን ከትላንት የባሰ ዛሬን እንጂ ላገኝ አልቻልኩም፤ ነገዬ ጨለመብኝ።"
ሀፍሲ መንሰቅሰቋን ቀጠለች ሀኑም ከዚ በላይ ዝም ማለትን አልፈለገችም ዝምታዋን ሰበረችው "ሀፍሲዬ እኔም አንቺም ለቤተሰቦቻችን አንድ ብርቅ ሴት ልጆች ነን፤ እኔም ካንቺ ሌላ እህት፤ አንቺም ከኔ ሌላ እህት እንደሌለን ውስጣችን ያውቃል፤ ምንም ውስጥሽ ያለውን ነገር ባታወሪኝም፤ የተከፋሽበትን ነገር ባላውቅም ተከፍቻለው፤ የሰበረሽን ነገር ባላውቅም ተሰብሬያለው፤ ቤተሰቦቻችን ስለአንቺ ተጨንቀዋል፤ ከኔ ምንም እንደማትደብቂ ስለሚያውቁ፤ ለኔ ነግረሽኝ የደበኳቸው ነገር እንዳለ ነው ሚያስቡት።" ሀፍሲን ከተደገፈችው የራሷ ትከሻ ላይ ሁለት ትከሻዋን ይዛ ቀና አደረገቻት፤ "ይሀውልሽ ሀፍሲ ከዚ በላይ ብቻሽን ስትሰቃይ ማየት አልችልም፤ ምንም ይሁን ምንም አብሬሽ እንደምጋፈጠው ቃል ገባልሻለው፤ በቃሽ ፍቀጂልኝ እና ህመምሽን ልታመምልሽ፤ እባክሽ ሀኑ" የእንባዋ ከረጢቶች ተዘረገፉ ሀፍሲ ደነገጠች ደስም አላት፤ ህመሞን ሚታመም ሰው በመኖሩ በትንሹም ቢሆን ውስጧን ቅልል ሲላት ተሰማት። "እሺ ሀኑ ነግርሻለው፤ ግን አሁን ርቦኛል፤ ምሳ እንብላ ከዛ ወደ አንድ ቦታ ወስድሽ እና አወራሻለው" አለቻት እና ተያይዘው ከተቀመጡበት ተነስተው ሄዱ።
.........................................................................
ቦታው አረንጓዴነቱና ጭር ማለቱ ሀኑን በጣም አስገርሟታል፤ "ደሞ ይህን ቦታ ምን ስትሆኚ አወቅሽው?" አለቻት ወደሀፍሲ ዞራ በግርምት፤ ሀፍሲ ሳቋን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስ ሳቀች "ቆይ እኔ ምለው አንቺ ምታቂውን ብቻ ነው ሀፍሳ ምታውቀው ያለሽ ማነው?" አሁንም ሳቀች ሀናን የሀፍሳ ፈገግታ ምን ያህል ርቋት እንደነበር የተረዳችው ሀፍሳ ስትስቅ ነበር፤ ከልቧ አዘነችላት "አይ ፈንዲሻዬ ምን ይሁን ያከሰለሽ?" ስትል ለራሷ ጠየቀች ነገሩን ለማወቅ እና ሀፍሳን ለመርዳት አሁን በይበልጥ ጎግታለች፤
መኪናቸውን ፓርክ አድርገው በሀፍሲ መሪነት በእግራቸው የሚያምረውንና ለአይን ሚማርከውን መናፈሻ ንፋስ እየወሰዱ ከአንድ ፀጥ ወዳለበት ጥግ ደረሰው ተቀምጡ።
ሀፍሲ ምን ብላ እንደምትጀምር ግራ ገብቷታል፤ ሀኑም የሀፍሲን ንግግር በጉጉት እየተጠባበቀች ነው...............
ሀፍሲን ግን ከሚያምረው ፈገግታዋ ያከሰላት ምን ይሆን?

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_አራት ʕ➍ʔ ይቀጥላል
╬╬═════════════
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
@eslamik_tube
@eslamik_tube
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
3.0K views"ųmį¥ę": , 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 20:48:03 ፍቅሯን አርባ ዓመት መደበቅ ትችላለች
ቅናቷን ግን አርባ ሰከንድ መደበቅ አትችልም ይሉን ነበር አንድ ሸህ ስለነርሱ ሲነግሩን።

ወንድሜ አትናደድ አፈጣጠራቸዉን ልመድ።


@Eslamik_Tube||እስላሚክ Tube
3.5K views"ųmį¥ę": , 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 20:02:37 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_ሁለት ʕ➋ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ከመኪናው ጩሀት ይልቅ የባለታክሲው ጩሀት ሀፍሲን አስደንግጧታል፤ ዛሬ የመጀመሪያዋ ባይሆንም ከሁሉም ቀን ዛሬ በተለየ መልኩ ደንግጣለች፤ "እያየሽ አትሄጂም? ምን እንደ በግ ይነዳሻል!? ካልቻልሽበት አሻግሩኝ በይ! ወይስ ከገጠር ነው የመጣሽው? ቀልቃላ!" እነዚህ ሁላ ቃሎች ለሀፍሲ ከሹፌሩ ነበር የተዘነዘረው በስራዋ ስላፈረች ሹፌሩን ቀና እንኳን ብላ ሳታየው የነበረችበትን ቦታ ለቃ ሄደች።
......................................................
እናቷ፣ ወንድሞቿ በሀፍሲ የባህሪ ለውጥ ተጨንቀዋል። እነሱ ፊት ደህና እንደሆነች ልታስመስል ብትጥርም አልሆነላትም፤ መከደን የማያውቀው ጥርሷ ዛሬ ግን ደክሞል፤ በመንገድ ስትሄድ ትልቅ ትንሹን ሰላም ሳትል የማታልፈዋ ሀፍሲ ዛሬ ግን አይደለም ለሰላምታ ለአይንም ተሰውራለች፤ ከአለት የጠነከረ ልቧ ዛሬ ተሸርሽሯል፤ እንደዛ ምትጓጓለት ትምህርቷ ዞር ብላ ማየት ትታለች፤ ለደቂቃ ከተቀመጠችበት እንድትነሳ ማትፈቅድላት እናቷ ዛሬ በስራ ስትጠመድ እያየች የማገዝ ሞራሏ ሞቷል፤ ከቤት ሲወጡ እንደ ሙሽራ አሽሞንሙና ምትልካቸው ወንድሞቿን ዛሬ ከነመፈጠራቸው ረስታቸዋለች፤ ሲመጡ በፍቅር ምትቀበላቸው የትልቁ ወንድሟ ልጆች ዛሬ ድምፃቸው ጫጫታ ሆኖ እየረበሻት እነሱ ሲመጡ ከቤት እየወጣች መጥፋት ጀምራለች። በቃ ሀፍሲ ማንነቷ ሞቷል። ምን እንደሆነች ምን እንደተፈጠረ ብዙዎች ቢጠይቆትም ለማንም ለመናገር ግን አልደፈረችም፤ ዛሬም ሰዎችን ሳታስቸግር ሳታስጨንቅ ጠንክራ ለመቆም ትፍጨረጨራለች ግን አልቻለችም፤ ትወድቃለች ደጋፊ እንደሚያስፈልጋት ብታውቅም የመናገር ድፍረቱን አጥታለች፤ ምትይዘው ምትጨብጠው ነገር ጠፍቶባታል፤ በፍፁም እንደዚ በቀላሉ እሸነፋለው ብላ አስባም አታውቅም ነበር፤ መሸነፏን ብትወደውም የተሸነፈችለት ነገር ግን የማይሆን መሆኑን ስታውቅ ልቧ ስብር ይላል፤ ሀዘን አንገቷን ያስደፋታል፤ አባቷ የተደባለቁበት አፈር መደባለቅ ትፈልጋለች፤ በዚ ስሜት ስትዋዥቅ ይሀው እንደ ቀልድ ከእድሜዋ ላይ 5 ወራትን ቀነሰች መወሰን ተቸግራ፣ መቁረጥ አቅቷት መተው የማትችለው ነገር ሆኖባት ትሰቃያለች............................................................
ዛሬ ግን መቁረጥ ባትችልም ስቃዩ እንደሚቀጥል ብታውቅም ፤ ስትተነፍሰው ከቀለላት፤ ህመሞ ከቀነሰላት፤ ብላ ለምትወዳት ከእህት በላይ ለምትቀርባት ለወንድሟ ሚስት ሁሉን ነገር ልትነግራት ወስነች። ሌላው ቢቀር ከአእምሮዬና ከልቤ ጋር ተጣልቼ በእግሬ ከምመራ በሷ ልብና አእምሮ ብመራ ከውስጤ ስቃይ ባልድንም ከአደጋ አመልጣለው ስትል ወሰነችን። ስልኳን አወጣችና ሀናን ጋ ደወለች ሀናን በሀፍሳ መደወል ተደናግጣለች የሀፍሲ ወንድም አህመድ አጠገቧ ቢሆንም ሀፍሳ 1 ነገር ሆና ይሆናል ብላ ስላሰበች ኔትወርክ እንዳስቸገረው ሰው ሆና ስልኳን ይዛ ወጣች።
"ሄለው ሀኑ" ሀፍሲ ነበረች በተሰበረ ድምፅ ከድምፆ ይልቅ ተስፋ መቁረጥ መሰበር መድከም ገነው ይሰማሉ
"ወዬ ሀፍሲ"
ሀፍሲ የሀናን ድምፅ ስትሰማ አለቀሰች....
ሀኑ ደንግጣለች "ምንድነው የሆንሽው?"
ሀፍሲ ሲቃ በተሞላበት ድምፅ ለሀናን ያለችበትን ቦታ፤ የምትነግራት ነገር እንዳለ እና ለማንም ሳትናገር እንድትመጣ አስጠንቅቃት ሰልኩን ዘጋችው።
ሀናን ለባሏ ሀፍሲ ጋር ልትሄድ እንደሆነ እንዲያውቅ ስለፈለገች ለእናቷ ደውላ ሀፍሲ ያለችበትን እና አሁን ወደሶ ልትሄድ እንደሆነ እና ለባሏም አንቺ ፈልገሽኝ እንደጠራሽኝ ቶሎ እንደምመለስ ነግረዋለው ብላ ነገረቻቸው። የሀኑ እናት ሀፍሲን በጣም ነው ሚወዷት እሳቸውም አንድ ሴት ስለሆነች ያለቻቸው ልጃቸውም እህት እንዳገኘች ለሳቸውም ሁለተኛ ሴት ልጅ እንዳገኙ ነው ሚያስቡት በሀፍሲ ከጊዜ ቡሀላ በመጣ የባህሪ ለውጥ መጨነቃቸው እንቅልፍ ማጣታቸው አልቀረም ለዚህም ነው ምንም ሳያቅማሙ በልጃቸው ሀሳብ የተስማሙት ግን ደሞ ለልጃቸው ባይናገሩትም ሀፍሲ አንድ ነገር ሆና እንዳይሆን ውስጣቸው ሰግቷል።
ሀናንም በዚ ሰዐት ሀፍሲ ያለችበት ሁኔታ ከባድ እንደሆነ ስላወቀች ከእናቷ ጋር የተስማሙትን ለባሏ አስረድታ ወደሀፍሲ ለመሄድ የመኪናዋን ቁልፍ አስነስታ በረረች ውስጧ ፈርቷል እ.......
ሀፍሲ ምን ገጥሟት ይሆን???


⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_ሶስት ʕ❸ʔ ይቀጥላል
╬╬═════════════╬╬

╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
@eslamik_tube
@eslamik_tube
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
3.6K views"ųmį¥ę": , 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 20:01:49 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
#እውነተ_ታሪክ

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_አንድ ʕ❶ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ፒፕፕፕፕፕፕፕፕፕፕፕ......................የታክሲው ጩሀት ከገባችበት ሀሳብ አባነናት ፤ወዴት መሄድ እንዳለባት እንኳን በቅጡ ሳትወስን ነበር ከቤቷ ብድግ ብላ የወጣችው። ለካንስ በሀሳብ ባህር ውስጥ ሰምጣ፤ አስፋልት መሀል ገብታለች፤ ምን ልትሰራ እዚህ መጣች? እሷም አታውቀውም እግሯን ተከትላ ለጊዜው አስፋልት መሀል ተገኝታለች፤ ልቧ እና አእምሮዋ ተጣልተውባት በእግሯ መመራት ከጀመረች ይሀው እንደቀልድ 5 ወር ሆናት። ከመኪና አደጋ ስታመልጥ ይህ የመጀመርያዋ አደለም፤ ጀሊሉ በቁድራዉ ይሸፍናታል እንጂ እንደሷማ ቢሆን ይሄኔ ቤተሰቦቿ እሷን በማስታመም እየማቀቁ ወይ ሰደቃ ሊያወጡላት ደረታቸው እየደቁ ነበር።
አይ ሀፍሲ ምን ይሆን እንደዚ ከጥንካሬሽ ማማ አውርዶ ዘጭ ያደረገሽ??
...............................................................................
ሀፍሳ ትባላለች በሰፈር ስሟ (ፈንዲሻዬ) በጣም ሳቂታ ስለነበረች የሰፈር ሰው ሁላ ተስማምተው ያፀደቁት ሁለተኛ ስሟ ነው ከልጅነቷ ጀምሮ ጠንካራ ጥሩ ፀባይ ያላት ሰው አክባሪ ታዛዥ......... በቃ ጥሩ የተባሉ ነገሮች ሁላ እሷ ላይ አሉ ለቤተሰቦቿ የመጨረሻ ልጅ ለዚያውም ብቸኛ ሴት ናት እናቷ እድሌ ብለው ይጠሯታል አባቷ ደግሞ መድመቂያዬ ይሏታል ወንድሞቿ ለሰከንድ ተከፍታ አይደለም ደብሯት ማየት አይፈልጉም አለም ትገልበጥልኝ ካለች አለምን ለመገልበጥ ማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ልጅቷ ሀፍሲ ናታ የቤቱ እንቁ የቤቱ ድመቀት......................................
እሷ ግን እንደዚ አልነበረችም ቤተሰቦቿ እንዳቀበጧት ቀበጥ አይደለችም ጠንካራ ሴት መሆን የልጅነት ህልሟ ስለነበር አሁን እስካለችበት የአምስተኛ አመት የህክምና ትምህርቷ ድረስ ውጤቷን ለማንም ያላስደፈረች በት/ት ቤትም በኮሌጅ ቆይታዋም የተመሰገነች ጎበዝ ተማሪ ነበረች እናት እና አባቷ ዩኒቨርስቲ ገብታ እንድትመረቅ ቢፈልጉም የወንድ ልጆቻቸው ሀሳብ አሸንፎ ከፍተኛ ውጤት ብታመጣም እዚው አ.አ ቀርታለች የእድሜ እኩዮቿ በቤተሰቦቻቸው ሲመከሩ የሀጂ መሀመድን ልጅ አታይም እስቲ እንደሷ ሁኚ እየተባሉ ነበር።
..........................................................................

ሀፍሲ ለመጀመርያ ጊዜ ትጎዳለች፤ ከትምህርቷ ያዘናጋታል፤ አረ እንደውም ፀባይ ሁላ ልትቀይር ትችላለች፤ ተብሎ በቤተሰብም፤ በዘመድ አዝማድ፤ በሰፈርሰ ው፤ አጠቃላይ በሚያውቃት ሁሉ ተፈርቶ የነበረው የ1ኛ አመት ተማሪ ሆና አባቷ ጋሽ መሀመድ ሲሞቱ ነበር። ሀፍሲ ግን ሰው እንደጠበቃት አልነበረችም እንደውም ወንድሞቿን ተቆጪ እናቷን "ሰብር አድርጊ" ብላ ስታፅናና ነበር። "ለአባቴ ዱዐ እንጂ ለቅሶ አያስፈልገውም፤የሚወደው ይቅራለት፤ ዱዐ ያድርግለት" ብላ ሚያለቅሱትን ሁላ እያስቆመች በምትኩ ቁርዐን ትሰጣቸው ነበር። "ሀዘኗን በውስጧ ይዛ ቤተሰቡን ለማፅናናት ነው እንጂ ሀፍሳማ ያባቷ ነገር እንዲ በቀላሉ አይወጣላትም" እያሉ ብዙዎቹ በግርምትም በማዘንም አምተዋታል። አንዳንዶቹ እናቷ ጋ እየመጡ "ዋ ይቺ ልጅሽን ተይ በያት ሀዘን በውስጧ አምቃ ቡሀላ የሆነ ነገር እንዳትሆንብሽ፤ አልቅሳ ቢወጣላት ነው ሚሻለው!" ብለው ስሞታ አቅርበዋል ሀፍሲ ግን ወይ ፍንክች ሀዘን ማመቅ የለ፤ መጎዳት የለ፤ ጠንክራ ቤተሰቡን ያጠነከረች ጀግና ሆነች፤ ቆይታ ሀዘኗን ይዛ እንዳትባል ይሀው አባቷ ከሞቱ 3 አመት አለፋቸው። ሀፍሲ ግን የድሮዋ ሀፍሲ ነበረች።
እና ዛሬስ ሀፍሲን ሚሰብር በሀሳብ የሚያዋዥቅ ከራሷ ሚያጣላ ምን ገጥሞት ይሆን ...............

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_ሁለት ʕ❷ʔ ይቀጥላል
╬╬═════════════╬╬
4.3K views"ųmį¥ę": , 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 22:32:05 #ሀፍሲ......

*ኢንሻአላህ ነገ ማታ 2:00 በኢስላሚክ Tube
4.3K views"ųmį¥ę": , 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 22:03:47 #ፈጅር እና ፈረጅ ሁሌም
አብረው የሚሄዱ መንትያዎች ናቸው
⇨ ቀኑን በፈጅር የከፈተ በርግጥም
በፈረጅ ከፍቶታል ።

» @Eslamik_Tube||እስላሚክ Tube㋡
4.4K views"ųmį¥ę": , 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 22:01:19 ነገራቶችን ለአላህ አሳልፈህ
ስትሰጣቸው በራሳቸው ጊዜ
ውብ ሆነው ይመጡልሃል ።

» @Eslamik_Tube||እስላሚክ Tube㋡
4.0K views"ųmį¥ę": , 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 18:34:37
ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡
@Eslamik_Tube||እስላሚክ Tube
4.6K views"ųmį¥ę": , 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 22:20:32 ስለቻናሉ ሀሳብ(አስተያየት) ያላቹሁ ካለምንም ፍራቻ(መጨነቅ) @MUBA_YA ላይ አሳውቁኝ

መልካም እንቅልፍ ተመኘሁላቹሁ ውዶቼ
4.8K views"ųmį¥ę": , 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ