Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ '. #ሀፍሲ '. ✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢን | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
#እውነተኛ_ታሪክ

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_ሶስት ʕ➌ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ሀናን ሀፍሲ ከቀጠረቻት ቦታ ስደርስ ሀፍሲ ጭንቅላቷን ጉልበቷ ላን ደፍታ ስታለቅስ አገኘቻት። አልቅሳ ይውጣላት ብላ አቅፋት ዝም አለች፤ ሀፍሲ ሀኑን ስታገኝ እስከዛሬ ታምቆ የነበረው እምባዋ ያለገደብ ወረደ፤ ሀዘኗን በእንባዋ ጎርፍ ምትሸኘው ነበር ምትመስለው። ሀኑ የሀፍሲን መረጋጋት እየጠበቀች አንድም ቃል ሳትተነፍስ በስስት ታያት ነበር።
..............................................................
ሀፍሲ አሁን ተረጋግታለች፤ "ይቅርታ ሀኑ በማታውቂው ነገር አልቅሼ አሴጨነኩሽ አይደል? ያው ታውቂያለሽ እንዳንቺ ምቀርበው አንድም ሰው የለም፤ እስከዛሬም አምቄ የያዝኩት እናንተን ሳላስጨንቅ ብቻዬን ቀና ለማለት ነበር፤ ግን አልቻልኩም። ዛሬ ደርሼ ደከምኩብሽ፤ ዛሬ ከትላንት የተሻለ ይሆናል ብዬ ነበር፤ ግን ከትላንት የባሰ ዛሬን እንጂ ላገኝ አልቻልኩም፤ ነገዬ ጨለመብኝ።"
ሀፍሲ መንሰቅሰቋን ቀጠለች ሀኑም ከዚ በላይ ዝም ማለትን አልፈለገችም ዝምታዋን ሰበረችው "ሀፍሲዬ እኔም አንቺም ለቤተሰቦቻችን አንድ ብርቅ ሴት ልጆች ነን፤ እኔም ካንቺ ሌላ እህት፤ አንቺም ከኔ ሌላ እህት እንደሌለን ውስጣችን ያውቃል፤ ምንም ውስጥሽ ያለውን ነገር ባታወሪኝም፤ የተከፋሽበትን ነገር ባላውቅም ተከፍቻለው፤ የሰበረሽን ነገር ባላውቅም ተሰብሬያለው፤ ቤተሰቦቻችን ስለአንቺ ተጨንቀዋል፤ ከኔ ምንም እንደማትደብቂ ስለሚያውቁ፤ ለኔ ነግረሽኝ የደበኳቸው ነገር እንዳለ ነው ሚያስቡት።" ሀፍሲን ከተደገፈችው የራሷ ትከሻ ላይ ሁለት ትከሻዋን ይዛ ቀና አደረገቻት፤ "ይሀውልሽ ሀፍሲ ከዚ በላይ ብቻሽን ስትሰቃይ ማየት አልችልም፤ ምንም ይሁን ምንም አብሬሽ እንደምጋፈጠው ቃል ገባልሻለው፤ በቃሽ ፍቀጂልኝ እና ህመምሽን ልታመምልሽ፤ እባክሽ ሀኑ" የእንባዋ ከረጢቶች ተዘረገፉ ሀፍሲ ደነገጠች ደስም አላት፤ ህመሞን ሚታመም ሰው በመኖሩ በትንሹም ቢሆን ውስጧን ቅልል ሲላት ተሰማት። "እሺ ሀኑ ነግርሻለው፤ ግን አሁን ርቦኛል፤ ምሳ እንብላ ከዛ ወደ አንድ ቦታ ወስድሽ እና አወራሻለው" አለቻት እና ተያይዘው ከተቀመጡበት ተነስተው ሄዱ።
.........................................................................
ቦታው አረንጓዴነቱና ጭር ማለቱ ሀኑን በጣም አስገርሟታል፤ "ደሞ ይህን ቦታ ምን ስትሆኚ አወቅሽው?" አለቻት ወደሀፍሲ ዞራ በግርምት፤ ሀፍሲ ሳቋን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስ ሳቀች "ቆይ እኔ ምለው አንቺ ምታቂውን ብቻ ነው ሀፍሳ ምታውቀው ያለሽ ማነው?" አሁንም ሳቀች ሀናን የሀፍሳ ፈገግታ ምን ያህል ርቋት እንደነበር የተረዳችው ሀፍሳ ስትስቅ ነበር፤ ከልቧ አዘነችላት "አይ ፈንዲሻዬ ምን ይሁን ያከሰለሽ?" ስትል ለራሷ ጠየቀች ነገሩን ለማወቅ እና ሀፍሳን ለመርዳት አሁን በይበልጥ ጎግታለች፤
መኪናቸውን ፓርክ አድርገው በሀፍሲ መሪነት በእግራቸው የሚያምረውንና ለአይን ሚማርከውን መናፈሻ ንፋስ እየወሰዱ ከአንድ ፀጥ ወዳለበት ጥግ ደረሰው ተቀምጡ።
ሀፍሲ ምን ብላ እንደምትጀምር ግራ ገብቷታል፤ ሀኑም የሀፍሲን ንግግር በጉጉት እየተጠባበቀች ነው...............
ሀፍሲን ግን ከሚያምረው ፈገግታዋ ያከሰላት ምን ይሆን?

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_አራት ʕ➍ʔ ይቀጥላል
╬╬═════════════
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
@eslamik_tube
@eslamik_tube
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤