Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ '. #ሀፍሲ '. ✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢን | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_ሁለት ʕ➋ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ከመኪናው ጩሀት ይልቅ የባለታክሲው ጩሀት ሀፍሲን አስደንግጧታል፤ ዛሬ የመጀመሪያዋ ባይሆንም ከሁሉም ቀን ዛሬ በተለየ መልኩ ደንግጣለች፤ "እያየሽ አትሄጂም? ምን እንደ በግ ይነዳሻል!? ካልቻልሽበት አሻግሩኝ በይ! ወይስ ከገጠር ነው የመጣሽው? ቀልቃላ!" እነዚህ ሁላ ቃሎች ለሀፍሲ ከሹፌሩ ነበር የተዘነዘረው በስራዋ ስላፈረች ሹፌሩን ቀና እንኳን ብላ ሳታየው የነበረችበትን ቦታ ለቃ ሄደች።
......................................................
እናቷ፣ ወንድሞቿ በሀፍሲ የባህሪ ለውጥ ተጨንቀዋል። እነሱ ፊት ደህና እንደሆነች ልታስመስል ብትጥርም አልሆነላትም፤ መከደን የማያውቀው ጥርሷ ዛሬ ግን ደክሞል፤ በመንገድ ስትሄድ ትልቅ ትንሹን ሰላም ሳትል የማታልፈዋ ሀፍሲ ዛሬ ግን አይደለም ለሰላምታ ለአይንም ተሰውራለች፤ ከአለት የጠነከረ ልቧ ዛሬ ተሸርሽሯል፤ እንደዛ ምትጓጓለት ትምህርቷ ዞር ብላ ማየት ትታለች፤ ለደቂቃ ከተቀመጠችበት እንድትነሳ ማትፈቅድላት እናቷ ዛሬ በስራ ስትጠመድ እያየች የማገዝ ሞራሏ ሞቷል፤ ከቤት ሲወጡ እንደ ሙሽራ አሽሞንሙና ምትልካቸው ወንድሞቿን ዛሬ ከነመፈጠራቸው ረስታቸዋለች፤ ሲመጡ በፍቅር ምትቀበላቸው የትልቁ ወንድሟ ልጆች ዛሬ ድምፃቸው ጫጫታ ሆኖ እየረበሻት እነሱ ሲመጡ ከቤት እየወጣች መጥፋት ጀምራለች። በቃ ሀፍሲ ማንነቷ ሞቷል። ምን እንደሆነች ምን እንደተፈጠረ ብዙዎች ቢጠይቆትም ለማንም ለመናገር ግን አልደፈረችም፤ ዛሬም ሰዎችን ሳታስቸግር ሳታስጨንቅ ጠንክራ ለመቆም ትፍጨረጨራለች ግን አልቻለችም፤ ትወድቃለች ደጋፊ እንደሚያስፈልጋት ብታውቅም የመናገር ድፍረቱን አጥታለች፤ ምትይዘው ምትጨብጠው ነገር ጠፍቶባታል፤ በፍፁም እንደዚ በቀላሉ እሸነፋለው ብላ አስባም አታውቅም ነበር፤ መሸነፏን ብትወደውም የተሸነፈችለት ነገር ግን የማይሆን መሆኑን ስታውቅ ልቧ ስብር ይላል፤ ሀዘን አንገቷን ያስደፋታል፤ አባቷ የተደባለቁበት አፈር መደባለቅ ትፈልጋለች፤ በዚ ስሜት ስትዋዥቅ ይሀው እንደ ቀልድ ከእድሜዋ ላይ 5 ወራትን ቀነሰች መወሰን ተቸግራ፣ መቁረጥ አቅቷት መተው የማትችለው ነገር ሆኖባት ትሰቃያለች............................................................
ዛሬ ግን መቁረጥ ባትችልም ስቃዩ እንደሚቀጥል ብታውቅም ፤ ስትተነፍሰው ከቀለላት፤ ህመሞ ከቀነሰላት፤ ብላ ለምትወዳት ከእህት በላይ ለምትቀርባት ለወንድሟ ሚስት ሁሉን ነገር ልትነግራት ወስነች። ሌላው ቢቀር ከአእምሮዬና ከልቤ ጋር ተጣልቼ በእግሬ ከምመራ በሷ ልብና አእምሮ ብመራ ከውስጤ ስቃይ ባልድንም ከአደጋ አመልጣለው ስትል ወሰነችን። ስልኳን አወጣችና ሀናን ጋ ደወለች ሀናን በሀፍሳ መደወል ተደናግጣለች የሀፍሲ ወንድም አህመድ አጠገቧ ቢሆንም ሀፍሳ 1 ነገር ሆና ይሆናል ብላ ስላሰበች ኔትወርክ እንዳስቸገረው ሰው ሆና ስልኳን ይዛ ወጣች።
"ሄለው ሀኑ" ሀፍሲ ነበረች በተሰበረ ድምፅ ከድምፆ ይልቅ ተስፋ መቁረጥ መሰበር መድከም ገነው ይሰማሉ
"ወዬ ሀፍሲ"
ሀፍሲ የሀናን ድምፅ ስትሰማ አለቀሰች....
ሀኑ ደንግጣለች "ምንድነው የሆንሽው?"
ሀፍሲ ሲቃ በተሞላበት ድምፅ ለሀናን ያለችበትን ቦታ፤ የምትነግራት ነገር እንዳለ እና ለማንም ሳትናገር እንድትመጣ አስጠንቅቃት ሰልኩን ዘጋችው።
ሀናን ለባሏ ሀፍሲ ጋር ልትሄድ እንደሆነ እንዲያውቅ ስለፈለገች ለእናቷ ደውላ ሀፍሲ ያለችበትን እና አሁን ወደሶ ልትሄድ እንደሆነ እና ለባሏም አንቺ ፈልገሽኝ እንደጠራሽኝ ቶሎ እንደምመለስ ነግረዋለው ብላ ነገረቻቸው። የሀኑ እናት ሀፍሲን በጣም ነው ሚወዷት እሳቸውም አንድ ሴት ስለሆነች ያለቻቸው ልጃቸውም እህት እንዳገኘች ለሳቸውም ሁለተኛ ሴት ልጅ እንዳገኙ ነው ሚያስቡት በሀፍሲ ከጊዜ ቡሀላ በመጣ የባህሪ ለውጥ መጨነቃቸው እንቅልፍ ማጣታቸው አልቀረም ለዚህም ነው ምንም ሳያቅማሙ በልጃቸው ሀሳብ የተስማሙት ግን ደሞ ለልጃቸው ባይናገሩትም ሀፍሲ አንድ ነገር ሆና እንዳይሆን ውስጣቸው ሰግቷል።
ሀናንም በዚ ሰዐት ሀፍሲ ያለችበት ሁኔታ ከባድ እንደሆነ ስላወቀች ከእናቷ ጋር የተስማሙትን ለባሏ አስረድታ ወደሀፍሲ ለመሄድ የመኪናዋን ቁልፍ አስነስታ በረረች ውስጧ ፈርቷል እ.......
ሀፍሲ ምን ገጥሟት ይሆን???


⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_ሶስት ʕ❸ʔ ይቀጥላል
╬╬═════════════╬╬

╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
@eslamik_tube
@eslamik_tube
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤