Get Mystery Box with random crypto!

፡፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ክፍል 19 ፀሀፊ fuad seid ግን እዉነታ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

፡፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 19

ፀሀፊ fuad seid


ግን እዉነታዉ ይህ አይደለም፡፡ትዳር ተፈጥሯዊ ተቋም ነው፡፡የሰዉ ልጅ ስሜት በተፈጥሯዊ መንገድ
መርካት አለበት። ለዚህ ደግሞ ትዳር የመጀመሪያዉ እና
የመጨረሻዉ አማራጭ ነዉ። ይሄ ተቋም በቀላሉ እንዲመሰረት
ወላጆች ልጆቻቸዉን ሊያግዙ ይገባል። አሁን ግን ትዉልዱ
የትዳርን በር ጠርቅሞ የዝሙትን በር ከበረገደዉ ቆይቷል።
የተዘጋዉ በር ሊከፈት ግድ ይላል!!
.
በነጋታዉ አምስት ሰዓት አካባቢ ወደነሀያት ቤት ሄድን። ኒካህ
ስለሆነ ግርግር አላበዛንም። በሶስት መኪና ነበር የሄድነዉ።
ሰዒድም ከኛ ጋር መጥቷል። እነሀያት ቤት ስንደርስ የሴቶቹ
ጭፈራ ለጉድ ነዉ። መድረሳችንን ሲያዉቁ ደግሞ ጭፈራዉን
የበለጠ አደመቁት። ቤተሰቦቿ በር ላይ ወጥተዉ ተቀበሉንና ወደ
ዉስጥ ገባን። የሴቶቹ የጭፈራ ድምፅ ይሰማኛል። እዚህ ደግሞ
ሀዩን እያሞገሱ እኔን ይነቁራሉ። ስገምት መግፊራ ትመስለኛለች
አሊያም ሌላ ሰዉ የሚያወጣዉ እንዲህ አሉ
"ለምነህ ለምነህ ፣ተሀጁድ ሰግደህ
እንዲሁም አልቀረህ ሀዩን አገኘህ።" ተሀጁድ በለሊት ሰዉ
በተኛበት የሚሰገድ ስግደት ነዉ።
ነቆራቸዉን ቀጠሉ
"ነጭ ትለብሳለች ፣ ነጭ ትወዳለች
እዉነት ለመናገር ትቦንሰዋለች።
እንቁላል ቢሰበር እንቁላል ይተካል፣
የኔማ ሀዩዬ ፣ አይኗ ብቻ ይበቃል።"
"ሰዒድ እየሳቀ ኧረ በግጥም ወረዱብን እኮ!" አለኝ። "ሀዩን
ሊሰጡንማ ቢገርፉንም እንችለዋለን።" አልኩት እየሳቅኩ።
.
ገብተን ትንሽ እንደተቀመጥን የኒካህ ዝግጅቱ ተጀመረ።
በሀይማኖታዊ ስርዓቱ መሰረት የጋብቻ ንግግር በሀይማኖት
አዋቂ ተደርጎ ሀያት ጥሎሽ የምትጠየቅበት ሰዓት ደረሰ። ለወጉ
ሁለት ሺህ ብር አለች። ወዲያዉ ጥሎሹን ሰጥተን የጋብቻ
ወረቀቱ ላይ ተፈራረምን። ሀዩን አገባኋት። ልክ ሀያት ያለችበት
ክፍል ወረቀቱ ተልኮ ስትፈርም ሴቶቹም ግጥማቸዉን
ሁለታችንንም የሚያወድስ አደረጉት
" ከዚህ እስከመስጂዱ ወርቅ ይነጠፍበት፣
አክረምና ሀዩ፣ ይመላለሱበት።
ጥቁር ይወዳሉ ጥቁር ይለብሳሉ፣
ለሀቁ ከሆነ ይመጣጠናሉ።" በድቤ ታጅቦ በሴቶቹ ዉብ ድምፅ
ይቀለፃል። ከሁሉም ያሳቀኝ ግጥም
"ግቢያችሁን እጠሩት ዳር ዳሩን አጥር፣
እስከአሁን ፆመሀል ከእንግዲህ አፍጥር።" የሚለዉ ነዉ።
እስከአሁን ፆመሀል ያሉት ከሚስት ጋር ሊደረጉ ከሚችሉ ነገሮች
ሁሉ ነዉ። እና ይኸዉ በሀዩ አፍጥር(ፆምህን ግደፍ) ማለታቸዉ
ነዉ።
.
ቤተሰቦቿ ሀዩን ለኔ መፍቀዳቸዉን ለማብሰር ግንባሯን
እንድስማት እሷ ወዳለችበት ክፍል ይዘዉኝ ሄዱ። ሀዩ በጣም
ተዉባ በሚያማምሩ ሴቶች ተከባ ተቀምጣለች። ራሄልም አብራት
ነበረች። ሚዜ አይደለችም ግን ሀዩን አጅባ ተቀምጣለች። ዛሬ
ሪቾዬን ባገባ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ሳያት አሳዘነችኝ። እኔን
የምታጣበት ድግስ ላይ መገኘቷ ግርም ብሎኛል። ምን አይነት
መቻል ይሁን ፈጣሪ የሰጣት? እስክንድር ጉዳይዋ እንዳልሆነ
በደንብ አዉቃለሁ። አይኗን ከኔ ለማዞር እንዲያግዛት ነዉ
የተወዳጀችዉ። ሪቾን ሳላስባንን አየኋትና የሀዩን የአይንእርግብ
ገልጬ ግንባሯን ሳምኳት። ሴቶቹ እልልታዉን አቀለጡት።
የማህበረሰቡን እሴት ስትጠብቅ ወላጅ እንዲህ እልል እያስባለ
ልጁን ያስምሀል።
.
ይቀጥላል.........

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube