Get Mystery Box with random crypto!

‍ አጭር አስተማሪ ታሪክ ለምጣዱ ሲባል...! አንዲት ሴትዮ ጓዳቸው ውስጥ እየተ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

‍ አጭር አስተማሪ ታሪክ
ለምጣዱ ሲባል...!

አንዲት ሴትዮ ጓዳቸው ውስጥ እየተንጎዳጎዱ ድንገት አንዲት አይጥ ምጣዳቸው ላይ ትወጣለች ወንድ ልጃቸው እንጨት ያነሳና አይጧን ለመምታት ሊሰነዝር ሲል ሴትዮዋ አስቆሙትና "ልጄ አይጧን ስትመታ እንጀራ ማብሰያችንን ምጣዱን ሰበርከው ማለት ነው ስለዚህ እስኪ ግድ የለም ለምጣዱ ሲባል አይጧን ዝም እንበላት" አሉት ይባላል።

ከዚህ ታሪክ ሁሌም ለምንፈልገው ነገር ስንል ብዙ ነገሮች መታገስ እንዳለብን ፣ ከመወሰናችን በፊት ማስተዋል እንዳለብን እንረዳለን ።