Get Mystery Box with random crypto!

፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡ ክፍል 23 ፀሀፊ fuad seid ግንባሩን ስሜው ወዲ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 23

ፀሀፊ fuad seid

ግንባሩን ስሜው ወዲያው ወደ ድንኳን ሄድኩ ሠው እየጮሀ ያለቅሣል፡፡ ተይማኖታችን ከማንባት በዘለለእየጮሁ ማልቀስን
ስለሚከለክል ሰዎቹ ዝም እንዲሉ ለመጠየቅ ሞከርኩ ግን
ሊሰሙኝ አልቻሉም። ኋላ ላይ አንድ ሽማግሌ ተቆጥተዉ
ወንዶቹን ስርዓት አስያዙልን። ድንኳን ዉስጥ እንደተቀመጥኩ
አንድ ጎረቤታችን ጠርታ ወደ ሴቶች ድንኳን ይዛኝ ሄደች።
በእስልምና እምነት መሰረት በሰርግም ሆነ በለቅሶ ወንዶች
ከሴቶች ጋር እንዲቀላቀሉ አይፈቀድም። የሴቶች ድንኳን ጋር
ስደርስ ሴትየዋ "ኧረ እናትህን ተይ በላት ፊቷን ቧጣ
ጨረሰችዉ። አላህም አይወደዉ!" አሉኝ። ወደ ሴቶች ድንኳን
ስመለከት እናቴ ደረቷን እየደበደበች ፊቷን እየቧጠጠች
ታለቅሳለች። ከአባዬ ሬሳ አርቀዉ ድንኳን ዉስጥ ያስገቧት
በጣም አስቸግራ መሆኑ ገባኝ። አባቴ በህይወቱ በነበረበት ጊዜ
ስታቆስለዉ ኖራ ዛሬ ታስመስላለች። እናቴ ሆና ክብሯ ባይዘኝ
ባጋጫት ሁላ ደስ ይለኝ ነበር። ወይ የሀይማኖት እዉቀት የላት!
ወይ ስነ ምግባር የላት፣ መልክ ብቻ!
እናቴ መምጣቴን ስታይ ትንሽ ተረጋጋች። እንዲሁ ለኔ ክብር
አላት። እህቶቼን ከቤት ጠርቼ ስርዓት እንዲያስይዟት ነገርኳቸዉ።
.
አባዬ ወዲያዉ ሰባት ሰዓት ላይ ተሰግዶበት ተቀበረ። በእስልምና
እምነት በሬሳ ላይ የሚሰገድ የስግደት አይነት አለ። ሬሳን ቶሎ
መቅበርም ይወደዳል።
በነጋታዉ ሰው ሀዘኑ እየበረደለት ድንኳኑ ዉስጥ መጫወት
ጀመረ። ግማሹ አስፈርሾ ይቅማል። ግማሹ ክብ ሰርቶ
ይጫወታል። ጮክ ብሎ ሚስቅ ሁሉ ነበር። አሪፍ የቤተሰብ
መሰብሰቢያ መድረክ ሆኗል። ለቅሶ መሆኑን ረሱት መሰለኝ።
ማታዉን ቤተሰብ ተሰብስቦ የአባዬን ስራ ማን ያስተዳድር
በሚለዉ ላይ መከረ። መጨረሻ ላይ እኔ ላይ እምነታቸዉን
ጥለዉ ትምህርቴን አቋርጬ የአባቴን ስራ እንድሰራ ወሰኑ።
.
ለቅሶዉ ቀዝቅዞ ፣ ድንኳኑ ፈራርሶ ፣ሰው እንደተበተነ ፤ ሀዩንም
ወደ ባህርዳር ሸኘኋት። ቢያንስ እስኪ ሰቃያችን ትመረቅ። እኔና
ሪቾ እንደሆነ ከትምህርት መስመር ወጥተናል። ትንሽ ቆይቼ
እኔም ወደ ባህርዳር ሄጄ ልብሶቼን ይዤና ዊዝድሮዉ ሞልቼ
ተመለስኩ። የህይወት መስመር መቼ እንደሚቀየር አይታወቅም።
ትናንት ተማሪ የነበርኩት ልጅ ይኸዉ ሰራተኛ ልሆን ነዉ።
.
ስራ በጀመርኩበት የመጀመሪያዉ ቀን ማታ የሪቾን መቃብር ሄጄ
ጎበኘሁ። ወደ ባህርዳር ስበር የፃፍኩትን ግጥም አነበብኩላት።
ሪቾ እንዳለችዉ የእዉነትም ተዉባ እየጠበቀችኝ ይመስለኛል።
እንዲህ ሱፍ ለብሼ የአባቴን መኪና ይዤ ሪቾ ብታየኝ ምን ትል
ነበር? እኔንጃ ብቻ ለየት ያለ ቃል አታጣም። የሆነ ነገር ትለኝ
ነበር።
.
የአባዬን ስራ እያስተዳደርኩ ቀናትም እየሮጡ ወራትም
እየተገነጠሉ ሰባት ወራት አለፉና የሀዩ እና ሀጅራ ምርቃት ደረሰ።
የፈጣሪ ዉሳኔ ነጠለን እንጂ እኔናሪቾም አብረን እንመረቅ ነበር።
በነገራችን ላይ የአባዬን ስራ በጣም ትርፋማ አድርጌዋለሁ።
በቅርቡ እንደዉም ባለን ተቀማጭ ገንዘብ ሌላ ተጨማሪ ስራ
ለማስጀመር እያሰብኩ ነዉ።
.
ቅዳሜዉን ዉዷ ሚስቴን ላስመርቅ ወደ ባህርዳር ሄድኩ።
ሀዩዬ የግቢዉን ትልቁን ዉጤት ነበር ያስመዘገበችዉ። አራት
ነጥብ! በጣም አኮራችኝ። ሀዩ ግን ከመመረቋ በላይ ጓግታለት
የነበረዉ አብረን የምንኖርበት ቀን መድረሱን ነዉ። በሰርግ ከቤቷ
በወጉ የምትወሰድበትን ቀን! የምንጠቃለልበትን እለት!
ሀዩን ሜዳሊያ አጥልቃና ዋንጫ ይዛ ሳያት በጣም ደስ አለኝ።
ሪቾ ከኛ ጋር ባለመሆኗ ግን አዘንኩ።
ሀዩ ፍልቅልቅ እንዳለች ዙሪያዋን የቆሙትን ቤተሰቦቿን እና እኔን
እያየች "የሀያትን ምርቃት ከሌሎች ምርቃቶች ለየት
የሚያደርገዉ በሰርጓ ዋዜማ መካሄዱ ነዉ።" አለች።
.
ይቀጥላል..........

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube