Get Mystery Box with random crypto!

EOTC TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV
የሰርጥ አድራሻ: @eotctvchannel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.58K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-06-01 21:26:08 ወቅታዊ መልዕክት ለምዕመናን
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የደብረ ኤልያስ ብሔረ ብፁዓን መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳምን በተመለከተ በበርካታ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችና የመገናኛ አውታሮች ልዩ ልዩ ዘገባዎች እየተላለፉ ይገኛሉ።
ይህን ተከትሎም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ገዳማት አስተዳደር መምሪያ ከሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ጋር በመገናኘት ተፈጸመ የተባለውን ችግር በተመለከተ በዝርዝር የማጣራት ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም በማዕከል ደረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ይገኛል።
ስለሆነም ዝርዝር ሁኔታው በሚገባ ተጣርቶ የተደረሰበት የማጣራት ውጤት እውነታውን በሚገባ በሚያሳይ መልኩ በቤተክርስቲያናችን ማዕከላዊ አስተዳደር የሚገለጽ ይሆናል።
በሌላ በኩል በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በጨፌ ሚሶማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ምሽት ላይ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ደረሰ ተብሎ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች የተገለጸውን ጥቃት በተመለከተ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የተሰማትን ጥልቅ ኃዘን እየገለጸች በሀገረ ስብከቱ በኩል ተጣርቶ በሚቀርቀው መረጃ መሰረት ጉዳዩን በሕግ አግባብ የምትከታተሐው መሆኑን ትገልጻለች።

ልዑል እግዚአብሔር የሟች ወገኖቻችንን ነፍስ በአብርሃም፣
በይስሐቅና በያዕቆብ ዘንድ እንዲያኖርልንም የቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዘወትር ጸሎቷ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ግንቦት ፳፬ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም

የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
12.0K viewsEOTC TV, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 19:37:24

9.3K viewsEOTC TV, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 19:05:24

5.7K viewsEOTC TV, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 15:18:01

2.8K viewsEOTC TV, 12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 20:29:06
6.4K viewsEOTC TV, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 20:29:01 ቅዱስ ሲኖዶስ በ፯ኛ ቀን ውሎው በአራት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ።
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ // ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
ዘጋቢ መ/ር ጌታቸው በቀለ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ሰባተኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባካሄደው ውይይት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርቷን ለትውልዱ የታስተምርበት ተቋማት አንዱ መንፈሳዊ ኮሌጆች መሆነቸውን አውስቷል፡፡ እነዚህ ኮሌጆች ወጥ የሆነ ሕግ ሳይኖራቸው የቆየ ሲሆን ; በቅርቡም በሐዋሳ እና በወልቂጤ የተቋቋሙት ኮሌጆች ባቀረቡት መተዳደሪያ ደንብ መሠረት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት አድርጎ ለሁሉም መንፈሳዊ ኮሌጆች የሚያገለግል ወጥ የሚሆን ሕግ አዘጋጅቶ ማጽደቁን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡
በሌላ አጀንዳ በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጀርመን ገዳም እንዲኖራት ያቀረበው በጥናት የተደገፈ ሰነድ ጸድቋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ አማካኝነት በሰሜን አሜሪካ በካሊፎርኒያ የተመሠረተው የኆኅተ ሰማይ ገዳምን በተመለከተ ጉባኤው የተወያየ ሲሆን ; ብፁዕነታቸው ገዳሙ የተመሠረተበትን ሰነድ ለጥቅምት ጉባኤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት እንደሚያስረክቡ አስታውቀዋል፡፡
ጉባኤው የአእምሮ ንብረትን የተመለከተ ጉዳይም በስፋት ተወያይቷል። ይህ ኮሚቴ በርካታ ሥራዎችን ሲሠራ የነበረ መሆኑ ታውቆ አሁንም በተጠናከረ መንገድ እንዲሠራ በጀት እንዲያዝለት ተወስኗል፡፡ በሌላ አጀንዳ የምስጢራት መፈጸሚያ የሆነው የጸሎት መጽሐፍም እንዲታተም ተወስኗል፡፡
ጉባኤው የጡረተኞችን አበልን የተመለከተ ጉዳይም ላይ ተወያይቷል።
የጡረተኞችን አበልን የተመለከተ ተጠንቶ እንዲቀርብ በታዘዘው መሠረት ጥናቱ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በዕድሜያቸው በቤተክርስቲያን ሲያገለግሉ ቆይተው በአነስተኛ ደመወዝ ጡረታ የወጡ ማስተካከያ የሚደረግበት ውሳኔም ተለልፏል፡፡
የዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት ማኅበረ ደናግል አንድነት ገዳምን የተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የተወያየበት ጉዳይ ነው፡፡ ገዳሙ ከተመሠረተ ከአንድ ሺሕ ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ በዚህ ገዳም ላይ ተነሥቶ የነበረው ችግር በተመለከተ ቅዱስ ተወያይቶበት የውሳኔ ሐሳብ አሳልፏ፡፡ ውሳኔውም እናቶች በጥንት ገዳሙ ሲተዳደርበት በነበረው አሠራር መሠረት እንዲቀጥል ገዳማውያን እናቶች በጥያቄያቸውም መሠረት አምልኮአቸውን እንዲፈጽሙ ውሳኔ ተወስኗል፡፡
ይህም ሰፊ ውይይት ተደርጎበት የእናቶች ገዳም አሠራር መሠረት እናቶች በቆየው ትውፊት፣ በጥያቄያቸው መሠረትም አምልኮታቸውንን እንዲፈጽሙ በመወሰን የዕለቱ ስብሰባ ማጠናቀቁን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት ዕለታዊ ማብራሪያ አስታውቀዋል።
የብፁዕነታቸውን ማብራሪያ በዩቲዩብ ገጻችን እንድትመለከቱ እንጋብዛለን ።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
6.3K viewsEOTC TV, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 19:26:16
7.8K viewsEOTC TV, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 19:24:53 ቅዱስ ሲኖዶስ በመሪ እቅድና የኪራይ ቤቶች አስተዳደርና ልማት ድርጅትን በተመለከቱ አጀንዳዎች ውሳኔ አሳለፈ።
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ // ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
ዘጋቢ ሶምሶን በዛብኅ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በስድስተኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።
የመጀመሪያው የመሪ ዕቅድን በተመለከተ ሲሆን በዚህ ውስጥ መንፈሳዊ ልማት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና አስተዳደር ጉዳዮችን ተመልክቷል ። በዚሁ አጀንዳ (ሀ) የመንፈሳዊ ልማት ዓላማ የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ጉዳይ በምድሪቱ ላይ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ መፍጠር፣ መገንባት የሚያስችል ሆኖ መጽደቁን የተናገሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዚሁ መሠረት ወደ ሥራ እንደሚጀመር ገልጸዋል።
በዚሁ አጀንዳ (ለ) ቤተክርስቲያን በብዙ የልማት ሥራዎች ውስጥ የምትሳፍበት እድል መኖሩ የተመላከተ ሲሆን ይኸው ወደ ተግባር እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሁሉም ሰው በመሪ እቅዱ ትግበራ ላይ እንዲተባበረር ጥሪ አቅርበዋል ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ ሁለት የኪራይ ቤቶች አስተዳደርና ልማት ድርጅትን ጉዳይ በተመለከተ በሁለት ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት ተደምጦ ጠቅላይ ቤተክህነት በቀረበው የመፍትሔ ሀሳብ መሠረት ተከታትሎ እንዲያስፈፅም ትዕዛዝ በመስጠት የዕለቱ ስብሰባ ማጠናቀቁን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት ዕለታዊ ማብራሪያ አስታውቀዋል።
የብፁዕነታቸውን ማብራሪያ በዩቲዩብ ገጻችን እንድትመለከቱ እንጋብዛለን ።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
7.7K viewsEOTC TV, 16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 22:30:55
8.4K viewsEOTC TV, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 22:30:42 ቅዱስ ሲኖዶስ በኦሮሚያ ክልል በኢሉአባቦራ ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲቋቋም ተሻሽሎ የቀረበውን ጥናት መርምሮ አጸደቀ!
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ፭ኛ ቀን የዛሬው ውሎ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የኢሊአባቦራ ሀገረ ስብከት አሻሽሎ ያቀረበውን የመንፈሳዊ ኮሌጅ ማቋቋሚያ ሰነድ መርምሮ ማጽደቁን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ በዕለታዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

ባለፈው ጊዜ የቀረበው የኢሊአባቦራ ሀገረ ስብከት የመንፈሳዊ ኮሌጅ ማቋቋሚያ ሰነድ ተሻሽሎ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተሻሽሎ መቅረቡን የገለጹት ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት የኮሌጁ መቋቋም በመርህ ደረጃ በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ መሆኑን ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና በምዕራብ ኦሮሚያ ማዕከላዊ በሆነ ቦታ አንድ ኮሌጅ እንዲቋቋም እንዲሁም በደቡብ ጎንደር እና በሰሜን ሸዋ አህጉረ ስብከት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ የቀረቡ ጥናቶች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የትምሕርት እና ማሰልጠኛ መምሪያ ዝርዝር ጥናቱ ተጠናቆ ከነበጀቱ ለጥቅምት የሲኖዶስ ጉባኤ ተጠንቶ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ መሆኑን አሳውቀዋል።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
8.5K viewsEOTC TV, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ