Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ሲኖዶስ በኦሮሚያ ክልል በኢሉአባቦራ ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲቋቋም ተሻሽሎ የቀረ | EOTC TV

ቅዱስ ሲኖዶስ በኦሮሚያ ክልል በኢሉአባቦራ ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲቋቋም ተሻሽሎ የቀረበውን ጥናት መርምሮ አጸደቀ!
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ፭ኛ ቀን የዛሬው ውሎ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የኢሊአባቦራ ሀገረ ስብከት አሻሽሎ ያቀረበውን የመንፈሳዊ ኮሌጅ ማቋቋሚያ ሰነድ መርምሮ ማጽደቁን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ በዕለታዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

ባለፈው ጊዜ የቀረበው የኢሊአባቦራ ሀገረ ስብከት የመንፈሳዊ ኮሌጅ ማቋቋሚያ ሰነድ ተሻሽሎ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተሻሽሎ መቅረቡን የገለጹት ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት የኮሌጁ መቋቋም በመርህ ደረጃ በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ መሆኑን ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና በምዕራብ ኦሮሚያ ማዕከላዊ በሆነ ቦታ አንድ ኮሌጅ እንዲቋቋም እንዲሁም በደቡብ ጎንደር እና በሰሜን ሸዋ አህጉረ ስብከት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ የቀረቡ ጥናቶች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የትምሕርት እና ማሰልጠኛ መምሪያ ዝርዝር ጥናቱ ተጠናቆ ከነበጀቱ ለጥቅምት የሲኖዶስ ጉባኤ ተጠንቶ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ መሆኑን አሳውቀዋል።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=