Get Mystery Box with random crypto!

EOTC TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV
የሰርጥ አድራሻ: @eotctvchannel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.58K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 60

2022-07-08 15:39:36 ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሚገኙ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን ተዟዙረው ጎበኙ፡፡
በመ/ር አቤል አሰፋ
(ኢኦተቤ ቴቪ ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም አዲስ አበባ)
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን በመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሚገኙ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጥንታዊ የሆነውን የቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ሕንጻና ውስጣዊ ይዞታ የጎበኙ ሲሆን ታሪካዊው የቤተመዛግብት ሕንጻ በእርጅና ምክንያት ጉዳት እንደደረሰበት ተመልክተዋል። በችግሩም ዙሪያ ከቤተመዛግብቱ ሠራተኞች ማብራሪያ ቀርቦላቸዋል፡፡ ቤተ መዛግብቱ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት ቅርሶችና ማይክሮ ፊልሞች የያዘ ሲሆን በእርጅና ምክንያት የተከሰተው ፍሳሽ ቅርሶቹ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የትንሣኤ አሳታሚ ድርጅትን የጎበኙ ሲሆን በማሳተሚያ ድርጅቱ ንብረት ክፍል የሚገኙ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የታተሙ በሥርጭት ላይ የሚገኙና ተከማችተው ያሉ መጻሕፍትንና የኅትመት ውጤቶችን ተመልክተዋል፡፡ በማሳተሚያ ድርጅቱ ኃላፊዎችም በድርጅቱ እንቅስቃሴ ላይ ማብራሪያ ቀርቦላቸዋል፡፡
ቅዱስነታቸውና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትን የንብረት ክፍል አሠራርም ተመለከቱ ሲሆን መሻሻል በሚገባው ጉዳይ ላይ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው እድሳት የሚያስፈልጋቸውን የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ሕንጻ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሕንጻ ፣የቅዱስ ፓትርያርክ እንግዳ መቀበያ ፣ እና የጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩን ሕንጻ እና ቅጥረ ግቢውን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቅዱስነታቸውና የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጉብኝት ዓላማ በቀጣይ ለሚሰጡት መመሪያ ሁኔታዎችን በአካል በማየት ተግባራዊ ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችላቸው መሆኑን በመግለጽ ቅዱስነታቸው በጉብኝቱ በመገኘታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጉብኝጡ ማጠናቀቂያ በሰጡት አስተያየት ጉብኝቱ ያሉትን ችግሮች እንዲመለከቱና እንዲረዱ እንዳስቻላቸው በመግለጽ በአደጋ ውስጥ የሚገኘውን ታሪካዊው የቤተመዛግብት ሕንጻ ጨምሮ ሌሎቹም በሚጠገኑበትና በሚስተካከሉበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በንብረት አያያዝና አወጋገድ ላይ በቀጣይ መመሪያ እንደሚሰጥ ተናግረው ጉብኝቱን ያሰናዱትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን አመስግነዋል፡፡
EOTC TV
++++++++++++++++++++++++++++++++
የወቅታዊ መረጃ ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ የፌስ ቡክ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ሊንኮች በመጫን ሰብስክራይብ እና ላይክ ያድርጉ፡፡ ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
1.2K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:03:15

1.6K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:41:22

1.6K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:16:46

1.6K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:56:05
1.8K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ