Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ሲኖዶስ በመሪ እቅድና የኪራይ ቤቶች አስተዳደርና ልማት ድርጅትን በተመለከቱ አጀንዳዎች ውሳ | EOTC TV

ቅዱስ ሲኖዶስ በመሪ እቅድና የኪራይ ቤቶች አስተዳደርና ልማት ድርጅትን በተመለከቱ አጀንዳዎች ውሳኔ አሳለፈ።
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ // ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
ዘጋቢ ሶምሶን በዛብኅ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በስድስተኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።
የመጀመሪያው የመሪ ዕቅድን በተመለከተ ሲሆን በዚህ ውስጥ መንፈሳዊ ልማት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና አስተዳደር ጉዳዮችን ተመልክቷል ። በዚሁ አጀንዳ (ሀ) የመንፈሳዊ ልማት ዓላማ የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ጉዳይ በምድሪቱ ላይ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ መፍጠር፣ መገንባት የሚያስችል ሆኖ መጽደቁን የተናገሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዚሁ መሠረት ወደ ሥራ እንደሚጀመር ገልጸዋል።
በዚሁ አጀንዳ (ለ) ቤተክርስቲያን በብዙ የልማት ሥራዎች ውስጥ የምትሳፍበት እድል መኖሩ የተመላከተ ሲሆን ይኸው ወደ ተግባር እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሁሉም ሰው በመሪ እቅዱ ትግበራ ላይ እንዲተባበረር ጥሪ አቅርበዋል ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ ሁለት የኪራይ ቤቶች አስተዳደርና ልማት ድርጅትን ጉዳይ በተመለከተ በሁለት ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት ተደምጦ ጠቅላይ ቤተክህነት በቀረበው የመፍትሔ ሀሳብ መሠረት ተከታትሎ እንዲያስፈፅም ትዕዛዝ በመስጠት የዕለቱ ስብሰባ ማጠናቀቁን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት ዕለታዊ ማብራሪያ አስታውቀዋል።
የብፁዕነታቸውን ማብራሪያ በዩቲዩብ ገጻችን እንድትመለከቱ እንጋብዛለን ።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=