Get Mystery Box with random crypto!

EOTC TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV
የሰርጥ አድራሻ: @eotctvchannel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.58K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-03 20:58:59 የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የአብነት ተማሪዎችን ተቀብሎ ትምህርት የማስጀመር መርሐ ግብር አከናወነ።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++
የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከአምስቱ ወረዳዎች የተዉጣጡና በገጠሪቱ አብያተ ክርስቲያናት የአገልጋይ ችግር ከአለባቸዉ ወረዳዎችና አካባቢዎች 30 የሚደርሱ የአብነት ተማሪዎችን የአካባቢዉ ቋንቃ መናገር ማስተማር መቀደስ የሚችሉ ማለትም የአማርኛ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናገሪዎችን ደቀ መዛሙርት በመቀበል ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የአብነት ተማሪዎችንም በመቀበል ትምህርት የማስጀመርና የእንኳን ደህና መጣቹ ሥርዓት አቀባበል በፈለገ አእምሮ የአብነት ትምህርት ቤትና የካሕናት ማሠልጠኛ በክቡር የሐገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ እና በሐገረ ስብከቱ ትምህርትና ማሰልጠኛ በሐገረ ስብከቱ የየክፍል ሐላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይም ጸሎተ ወንጌል ደርሶ በሐገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ሐላፊ በሊቀ ማዕምራን ኃይለ መለኮት ግርማ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቶቷል። በማስቀጠልም በሐገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የእንኳን ደሕና መጣቹና ምክር የተሰጣቸዉ ሲሆን ባላቸዉ ጊዜ በርትተዉና ጠንክረው እንዲማሩ የመጡበትን አላማ በአግባቡ እንዲያሳኩና ተምረዉ የቤተክርስቲያንን ችግር እንዲፈቱ በቤተክርስቲያን ስም የአደራ መልዕክታቸዉን ሥራ አስኪያጁ አስተላልፈዋል።
ከተለያዩ ስፍራዎች የመጡት የአብነት ተማሪዎች ቁጥራቸዉ 30 እንደሚደርስና የአካባቢያቸዉን ቋንቋ በአግባቡ የሚናገሩ በመሆናቸዉ የቤተክርስቲያንን የአገልጋይ እጥረትና በአካባቢዉ ቋንቋ አገልግሎት የመስጠት ችግር ሊፈቱ እንደሚችሉ በትምህርት ማሠልጠኛዉ ኃላፊዉ የተገለፀ ሲሆን ተማሪዎቹ የሚማሩት የፊደል ንባብ ፣ውዳሴ ማርያም ፣ሰዓታት ፣ቅዳሴ እና ለቅስና አገልግሎት የሚያበቋቸዉን ትምህርት እና የነገረ ሐይማኖት ትምህርቶችንና የስብከት ዘዴ እንደሚማሩ ተገልፆ በመጨረሻም በክቡር ሥራ አስኪያጁ ጸሎት መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
ዘገባው የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ነው።
4.6K viewsEOTC TV, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 14:06:28

6.1K viewsAbel ዐቤል, 11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 21:02:33

2.8K viewsAbel ዐቤል, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:51:08

3.1K viewsEOTC TV, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:43:28

3.0K viewsEOTC TV, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:41:39

2.9K viewsEOTC TV, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 16:31:33
5.1K viewsAbel ዐቤል, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 16:31:22 በመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የተዋቀረው የትምህርትና ስልጠና ግብረ ኃይል ዐቢይ ኮሚቴ የሰባክያነ ወንጌል ስምሪት አከናወነ፡፡
መ/ር ማርቆስ ተበቃ
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ //መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም)
መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተከናወነው መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው በስምሪቱ ለሚሳተፉ አካላት መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡
በተለያዩ አካበባቢዎች የሚሠማሩት መምህራንም በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ፈተና እንደ አንድ ግብዓት በመውሰድ ምዕመናን በሃይማታቸው ጸንተው ቤተ ክርስቲያንን እንዲጠብቁ፤ እንዲሁም በዕምነታቸው ምክንያት ችግር የገጠማቸው ምዕመናንን የማጽናናት ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲያከናውኑም አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡
በስምሪቱ ወቅት በትምህርት መልክ የሚሰጥ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እና የቤተ ክርስቲያን ሚናን በተመለከተ የሥልጠና ማንዋል መዘጋጀቱንም የኮሚቴው አባላት ገልጸዋል፡፡
EOTC TV
++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
5.2K viewsAbel ዐቤል, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 20:18:03
1.0K viewsAbel ዐቤል, 17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 20:17:50 የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶችና መንፈሳውያን ማኅበራት አንድነት ሁለተኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ አደረገ።
እሌኒ ክፍሌ
(ኢኦተቤ ቴቪ// EOTC TV //መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
ጥቅምት ፳/፳፻፲፭ ዓ.ም የተመሠረተው የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶችና መንፈሳውያን ማኅበራት አንድነት
በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከትና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ጠቅላላ ጉባኤ የጉራጌ ሀገረ ስብከት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የየወረዳ አብያተ ክህነት ሊቃነ ካህናትና የሰንበት ት/ቤቶች ክፍል ኃላፊዎች፣ የማኀበራት ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች በተገኙበት ተካሒዷል።
በጉባኤውም የበገና ዝማሬዎችና መነባንብ ቀርቦ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። የሰንበት ት/ቤቶችና ማኅበራት አንድነት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን መንፈሳዊ ተግባራት የሥራ ዘገባና በቀጣይ ሊሠሩ የታሰቡ ሥራዎች ዕቅድ ቀርቧል።

በዕለቱ የጉባኤው ታዳሚዎች ከቀረበው መረጃ ተነስተው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከተሰጡት አስተያየቶችም መካከል የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሐዋርያዊ አገልግሎት በዕውቀት፣ በአሳብ፣ በገንዘብም ከማኅበሩ ጎን በመሆን አገልግሎቱን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከትና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር ማኀበሩ ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰራቸውን ዘርፈ ብዙ ሥራዎች አድንቀው ለሌሎችም የሀገራችን ክፍሎች አርአያ የሚሆን ጠንካራ ማኅበር መሆኑንም ገልጸዋል።
መሰል ጉባኤያት በሁሉም ወረዳዎች እየተዘዋወራችሁ በማድረግ አንድነታችሁን ማጠናከርና በሀገረ ስብከታችሁ ውስጥ ያሉ ወረዳና አብያተክርስቲያናትንም መጎብኘት አለባችሁ ሲሉም አክለዋል።
በመጨረሻም ሁሉም የጉባኤው ታዳሚ በሚችለው አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን ብፁዕነታቸው ማኅበሩ ለሚያከናውነው አገልግሎት ድጋፍና ማበረታቻ 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) ቃል ገብተዋል።
ጉባኤው በብፁዕነታቸው ጸሎተ ምዕዳን ተጠናቋል።
EOTC TV
++++++++++++++++++++++++++++++++
የወቅታዊ መረጃ ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ የፌስ ቡክ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ሊንኮች በመጫን ሰብስክራይብ እና ላይክ ያድርጉ፡፡ ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
1.0K viewsAbel ዐቤል, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ