Get Mystery Box with random crypto!

EOTC TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotctvchannel — EOTC TV
የሰርጥ አድራሻ: @eotctvchannel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.54K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-03-22 20:14:02

6.9K viewsAbel ዐቤል, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:34:32
9.8K viewsAbel ዐቤል, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:34:31 ሰበር ዜና ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር ) አረፉ
(EOTC TV)
በመ/ር አቤል አሰፋ
(ኢኦተቤ ቴቪ መጋቢት ፲፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ)
ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ የሆኑት በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ ዶ/ር በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር ) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።
በረከታቸው ይደርብን።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
9.9K viewsAbel ዐቤል, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:13:23 በሕገ ወጥ ሹመቱ የተሳተፉ ግለሰቦች ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በመምጣት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተነጋገሩ።
መ/ር አቤል አሰፋ
(EOTC TV //መጋቢት ፲፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ )
በቤተ ክርስቲያን በተፈጸመውን ሕገ-ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ የተሾሙት ግለሰቦች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ቀርበው ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር በዝግ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱም ከቅዱስ ሲኖዶስ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ሹመቱን የሰጡት ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ሰፊ ውይይት ስምምነት ባደረጉባቸው 10 ነጥቦች መሠረት በማድረግ መከናወኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
10.3K viewsEOTC TV, 16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 21:13:59

4.1K viewsEOTC TV, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 15:33:25
5.2K viewsEOTC TV, 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 15:33:11 የመስቀለ ክርስቶስ በዓል በዋግኽምራ በታሪካዊው የደብረሰላም ውቅር መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተከበረ።
መ/ር ጌታቸው በቀለ
(EOTC TV  //መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ዋግኽምራ  )
በዋግኽምራ ሀገረ ስብከት በጥንታዊውና በታሪካዊው የደብረሰላም ውቅር መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢት ፲ ቀን የጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የተገኘበት ታላቅ በዓል በድምቀት ተከበረ።

በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስ እና ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል። የዕለቱን ትምህርት የሰጡት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ "ለሚፈሩት ምልክትን ሰጠሃቸው" በማለት ስለ ነገረ መስቀሉ ትምህርት ሰጥተዋል።

ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ፫:፲፰-፲፱ "ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለእነርሱ አልኋችሁ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ፤ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ ሐሳባቸው ምድራዊ ነው"  እንዲል ጉድገጓድ ቆፍረው በአይሁዳና በኢየሩሳሌም ሁሉ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣችበት ድረስ ለ፫፻ ዓመታት ያህል ተቀብሮ ኖረ።

የዕሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ በመስቀሉ ኃይል የክርስቲያኖች ጠላት የሆነውን መክስምያኖስን ድል ከነሣ በኋላ ክርስቲያን ሆነ፤ እርሷም ልጄ ክርስቲያን ከሆነ ኢየሩሳሌም ሄጄ የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት አሠራለሁ፤ የጌታዬን መስቀል ከተቀበረበት አስወጣለሁ ብላ ተስላ ነበር። ስለቷ በመፈጸሙ ደስ ተሰኝታ መስከረም ፲፮ ቀን ደመራን አስደምራለች። የእሳቱ ጢስ ወደ ሰማያት ወጥቶ መስቀሉ ካለበት ቦታ ላይ ተተከለ። በዚህም ፈጣሪዋን አመስግና ቁፋሮውን መስከረም ፲፯ ቀን አስጀመረች። ከዚያም መጋቢት ፲ ቀን በ፫፻፳፯ ዓም ጌታችን መድኃኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት ቅዱስ መስቀል ተገኘ።

ይህን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ መጋቢት ፲ ቀን መስቀሉ የተገኘበትን በድምቀት ታከብራለች።

በበዓሉ ላይም  በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
             


        "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 
          የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
                       የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ  +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=
5.3K viewsEOTC TV, 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 21:53:18

6.5K viewsAbel ዐቤል, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 16:05:02

7.2K viewsEOTC TV, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 15:54:07

7.1K viewsEOTC TV, 12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ