Get Mystery Box with random crypto!

የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶችና መንፈሳውያን ማኅበራት አንድነት ሁለተኛ ዙር ጠቅላላ ጉባ | EOTC TV

የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶችና መንፈሳውያን ማኅበራት አንድነት ሁለተኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ አደረገ።
እሌኒ ክፍሌ
(ኢኦተቤ ቴቪ// EOTC TV //መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
ጥቅምት ፳/፳፻፲፭ ዓ.ም የተመሠረተው የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶችና መንፈሳውያን ማኅበራት አንድነት
በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከትና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ጠቅላላ ጉባኤ የጉራጌ ሀገረ ስብከት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የየወረዳ አብያተ ክህነት ሊቃነ ካህናትና የሰንበት ት/ቤቶች ክፍል ኃላፊዎች፣ የማኀበራት ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች በተገኙበት ተካሒዷል።
በጉባኤውም የበገና ዝማሬዎችና መነባንብ ቀርቦ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። የሰንበት ት/ቤቶችና ማኅበራት አንድነት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን መንፈሳዊ ተግባራት የሥራ ዘገባና በቀጣይ ሊሠሩ የታሰቡ ሥራዎች ዕቅድ ቀርቧል።

በዕለቱ የጉባኤው ታዳሚዎች ከቀረበው መረጃ ተነስተው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከተሰጡት አስተያየቶችም መካከል የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሐዋርያዊ አገልግሎት በዕውቀት፣ በአሳብ፣ በገንዘብም ከማኅበሩ ጎን በመሆን አገልግሎቱን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከትና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር ማኀበሩ ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰራቸውን ዘርፈ ብዙ ሥራዎች አድንቀው ለሌሎችም የሀገራችን ክፍሎች አርአያ የሚሆን ጠንካራ ማኅበር መሆኑንም ገልጸዋል።
መሰል ጉባኤያት በሁሉም ወረዳዎች እየተዘዋወራችሁ በማድረግ አንድነታችሁን ማጠናከርና በሀገረ ስብከታችሁ ውስጥ ያሉ ወረዳና አብያተክርስቲያናትንም መጎብኘት አለባችሁ ሲሉም አክለዋል።
በመጨረሻም ሁሉም የጉባኤው ታዳሚ በሚችለው አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን ብፁዕነታቸው ማኅበሩ ለሚያከናውነው አገልግሎት ድጋፍና ማበረታቻ 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) ቃል ገብተዋል።
ጉባኤው በብፁዕነታቸው ጸሎተ ምዕዳን ተጠናቋል።
EOTC TV
++++++++++++++++++++++++++++++++
የወቅታዊ መረጃ ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ የፌስ ቡክ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ሊንኮች በመጫን ሰብስክራይብ እና ላይክ ያድርጉ፡፡ ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel