Get Mystery Box with random crypto!

የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የአብነት ተማሪዎችን ተቀብሎ ትምህርት የማስጀመር መርሐ ግብር አከና | EOTC TV

የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የአብነት ተማሪዎችን ተቀብሎ ትምህርት የማስጀመር መርሐ ግብር አከናወነ።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++
የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከአምስቱ ወረዳዎች የተዉጣጡና በገጠሪቱ አብያተ ክርስቲያናት የአገልጋይ ችግር ከአለባቸዉ ወረዳዎችና አካባቢዎች 30 የሚደርሱ የአብነት ተማሪዎችን የአካባቢዉ ቋንቃ መናገር ማስተማር መቀደስ የሚችሉ ማለትም የአማርኛ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናገሪዎችን ደቀ መዛሙርት በመቀበል ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የአብነት ተማሪዎችንም በመቀበል ትምህርት የማስጀመርና የእንኳን ደህና መጣቹ ሥርዓት አቀባበል በፈለገ አእምሮ የአብነት ትምህርት ቤትና የካሕናት ማሠልጠኛ በክቡር የሐገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ እና በሐገረ ስብከቱ ትምህርትና ማሰልጠኛ በሐገረ ስብከቱ የየክፍል ሐላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይም ጸሎተ ወንጌል ደርሶ በሐገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ሐላፊ በሊቀ ማዕምራን ኃይለ መለኮት ግርማ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቶቷል። በማስቀጠልም በሐገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የእንኳን ደሕና መጣቹና ምክር የተሰጣቸዉ ሲሆን ባላቸዉ ጊዜ በርትተዉና ጠንክረው እንዲማሩ የመጡበትን አላማ በአግባቡ እንዲያሳኩና ተምረዉ የቤተክርስቲያንን ችግር እንዲፈቱ በቤተክርስቲያን ስም የአደራ መልዕክታቸዉን ሥራ አስኪያጁ አስተላልፈዋል።
ከተለያዩ ስፍራዎች የመጡት የአብነት ተማሪዎች ቁጥራቸዉ 30 እንደሚደርስና የአካባቢያቸዉን ቋንቋ በአግባቡ የሚናገሩ በመሆናቸዉ የቤተክርስቲያንን የአገልጋይ እጥረትና በአካባቢዉ ቋንቋ አገልግሎት የመስጠት ችግር ሊፈቱ እንደሚችሉ በትምህርት ማሠልጠኛዉ ኃላፊዉ የተገለፀ ሲሆን ተማሪዎቹ የሚማሩት የፊደል ንባብ ፣ውዳሴ ማርያም ፣ሰዓታት ፣ቅዳሴ እና ለቅስና አገልግሎት የሚያበቋቸዉን ትምህርት እና የነገረ ሐይማኖት ትምህርቶችንና የስብከት ዘዴ እንደሚማሩ ተገልፆ በመጨረሻም በክቡር ሥራ አስኪያጁ ጸሎት መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
ዘገባው የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ነው።