Get Mystery Box with random crypto!

እለታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @eletawizena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-29 08:45:03 ‘እየሱስን ለማግኘት’ ጾም ላይ የቆዩ 100 የሚጠጉ ሰዎች አስከሬን የተገኘበት ስፍራ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpvxwz7d1x5o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

እየሱስን ለማግኘት እራሳቸውን በጾም አድክመው እንዲሞቱ በሚያበረታታ የእምነት ቡድን ስብከት የተነሳ የሞቱ ወደ 100 የሚደርሱ ሰዎች አስከሬን በምሥራቅ ኬንያ ተገኝቷል። አሁንም በዚሁ ስፍራ ከሃይማኖታዊው ትዕዛዝ አናፈነግጥም ብለው በርካታ ሰዎች በጾም ላይ እንደሚገኙ ፖሊስ አስታውቋል። በዚህም ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል። የኬንያ መንግሥትም በእንዲህ አይነቱ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ዙሪያ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት እየተደረገበት ነው።
6 views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 08:44:04 በሱዳን ግጭት ውስጥ የአካባቢው ዋነኛ አረብ አገራት ሚና ምንድን ነው?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyjpmn7jydzo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

በሱዳን በኃያላኑ የጦር ጄኔራሎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት በቀጠናው እና በዓለም ዙሪያ ያሉ አገራት ክስተቱን በዓይነ ቁራኛ እንዲከታተሉት አድርጓቸዋል። ቁልፍ የሆነው የቀይ ባሕር የንግድ መስመርን የምታዋስነው ሱዳን፤ ግዙፍ የእርሻ፣ የወርቅ እንዲሁም የነዳጅ ሃብት ባለቤት ነች። በሱዳን ግጭት ውስጥ የአካባቢው ዋነኛ አረብ አገራት የሳዑዲ አረቢያ፣ የግብፅ እና የአረብ ኤሚሬቶች ሚና ምንድን ነው?
6 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 01:25:05 ቅዳሜ፡-ጋቢና VOA
https://av.voanews.com/clips/VAM/2023/04/28/20230428-213000-VAM131-program_original.mp3

Gabina VOA is designed to be an infotainment youth radio show broadcasting to Ethiopia and Eritrea in the Amharic language. The show brings varied perspectives on issues concerning young people in the Horn of Africa region. “Gabina” in the Amharic language is a front-row taxi ride.
33 views22:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 00:36:10 ኢትዮጵያ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በየዓመቱ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ታጣለች
https://amharic.voanews.com/a/7070807.html

ኢትዮጵያ፣ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት፣ በየዓመቱ 3ነጥብ3 ቢሊዮን ዶላር እንደምታጣ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተደረገው ይኸው ጥናት፣ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት ከሚላከው ገንዘብ 78 በመቶ የሚኾነው፣ ከባንክ ውጭ ባሉ ሕገ ወጥ መንገዶች በኩል እንደሚገባ አመልክቷል፡፡


ጥናቱን ለዐዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አባላት ያቀረቡት አቶ ይርጋ ተስፋዬ፣ በጥቁር ገበያው ያለው የውጭ ምንዛሪ መጠን፣ በባንኮች ካለው ከግማሽ በላይ የበለጠ ስለኾነ፣ በተጠቃሚው ተመራጭ እንደሚያደርገው አስረድተዋል፡፡ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ፣ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችን እንደሚያስከትልም፣ ጥናት አቅራቢው አመልክተዋል፡፡


ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
34 views21:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 00:35:09 ለወገን ደራሹ የበጎ አድራጎት ድርጅት
https://amharic.voanews.com/a/amhara-assassination/7070923.html

ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትንና ቤተሰቦቻቸውን በመርዳት ሥራ ላይ የተሰማራ፣ “ወገኔ የኢትዮጵያውያን ማኅበር” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማኅበርን በአሁኑ ወቅት፣ በዐዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ ለተለያዩ የቤተሰብ አባላት ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።


“ወገኔ የኢትዮጵያውያን ማኅበር” ከ23 ዓመታት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ በሚኖሩ አሥር ኢትዮጵያውያን የተመሠረተ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ “በብዙ ችግሮች ውስጥ የምትገኘውን የትውልድ አገራችንን በምን ልናግዝ እንችላለን?’ ብለን ስንወያይ ነው ሐሳቡ የመጣልን” ይላሉ፡ መስራቾቹ ስለወገኔ አመሰራረት ሲናገሩ።


ከዚያም በየወሩ ጥቂት ገንዘብ እያዋጡ፣ በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ የሚገኙ ችግረኛ ቤተሰቦችን ማንሳት እንደጀመሩም ይገልጻሉ፡፡ “ወገኔ” በ23 ዓመታት ዕድሜው ከ800 በላይ ቤተሰቦችን ደግፏል፡፡


ከነዚህም ብዙዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ከመርዳት በተጨማሪ፣ ልጆቻቸውንም አስተምሮ ለቁም ነገር አብቅቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከ360 በላይ ለሚሆኑ ቤተሰቦች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ 23ኛ ዓመቱን በዐዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል፡፡


ከዝግጅቶቹ በአንዳቸው ላይ የታደመው ዘጋቢያችን ያሰናዳውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
31 views21:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 00:34:10 አብን፥ የአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ “የተጠያቂነት አለመኖር ክትያ ነው” አለ
https://amharic.voanews.com/a/amharaassassination/7070935.html

በዐማራ ክልል የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ የአምስት ሰዎች መገደል፣ ከዚኽ ቀደም በክልሉ አመራሮች ላይ ግድያ የፈጸሙ ሰዎች ተጠያቂ አለመኾናቸውን ተከትሎ የመጣ ጥቃት እንደኾነ፣ የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አስታወቀ።


ገዥው ፓርቲ ብልጽግና በበኩሉ፣ ምልአተ ሕዝቡን ያሳተፈ ጠንካራ የፖለቲካ ትግል በማድረግ፣ ሕግ የማስከበር ርምጃዎችን በማጠናከር ጽንፈኝነትን ለመግታት፣ ከምንጊዜውም በበለጠ ጠንክሮ እንደሚሠራ አስታውቋል፡፡


አቶ ግርማ የሺጥላ፣ ካለፈው ዓመት መስከረም ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በጽ/ቤት ሓላፊነት የመሩት የዐማራ ብልጽግና ፓርቲ ደግሞ፣ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ በአሰፈረው መልእክቱ፥ የታጠቁ ጽንፈኛ ኃይሎች ያላቸው አካላት፣ ትላንት በአደረሱት ድንገተኛ ጥቃት ከሞቱት ውስጥ፥ የአቶ ግርማ ሹፌር የነበሩት ልየው መንጌ እና አጃቢዎቻቸው እንደሚገኙበት አረጋግጧል።


ትላንት ኀሙስ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ተወልደው በአደጉበት ሰሜን ሸዋ መሀል ሜዳ የተገደሉትን የዐማራ ክልል የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ የአቶ ግርማ የሺጥላን ግድያ የሚያወግዙ መግለጫዎች፣ ከልዩ ልዩ ተቋማት እየወጡ ነው።


የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(ዐብን) የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ጣሂር መሐመድ ከዚኽ ቀደም በክልሉ የተፈጸመው ወንጀል ተሸፋፍኖ መቆየቱ፣ ዐዲስ ወንጀል እንዲፈጸም የሚገፋፋ ኾኗል የሚል አቋም አንጸባርቀዋል።


አቶ ጣሂር በክልሉ መንግሥት አመራሮች ላይ ተደጋግሞ እየተፈጸመ ያለው የግድያ ጥቃት፣ ክልሉን የቀውስ ማዕከል በማድረግ ሕዝቡን ለጸጥታ ስጋት እንደዳረገው ጠቅሰዋል። ከአምስት ዓመት በፊት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩትን ዶክተር አምባቸው መኮነንን ጨምሮ የአራት ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች በተመሳሳይ መልኩ መገደላቸውንም አስታውሰዋል።




የክልሉን መንግሥት መግለጫ ይፋ ያደረገው የዐማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ(መሀል ሜዳ) ወደ ደብረ ብርሃን በመመለስ ላይ ሳሉ መንዝ ጓሳ በተባለው አካባቢ፣ በግል ጥበቃዎቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ፣ “ኢመደበኛ” ሲል በጠራቸው ታጣቂዎች ጥቃት፣ አቶ ግርማን ጨምሮ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አድርጎ ነበር።


የዐማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልእክቱ፣ የታጠቁ ጽንፈኛ ኃይሎች ያላቸው አካላት፣ ትላንት በአደረሱት ድንገተኛ ጥቃት ከሞቱት ውስጥ፥ የአቶ ግርማ ሹፌር የነበሩት ልየው መንጌ እና አጃቢዎቻቸው እንደሚገኙበት አረጋግጧል።


ብልጽግና ፓርቲ በአወጣው የኀዘን መግለጫ፣ በሐሳብ የተለየን ሰው ሞግቶ፣ በአመለካከት የተለየን በአመለካከት ረትቶ፣ ለአገር እና ለወገን የሚበጀውን ሐሳብ ማስፋት ሲቻል፣ ለዚያውም እንደ ግርማ የሺጥላ ዐይነቱን የሕዝብ እና የወገን አለኝታ ምሁር፣ በእንዲህ ዓይነት መልኩ መግደል መሸነፍ ነው፤ ብሏል፡፡


ፓርቲው፥ ምልአተ ሕዝቡን ያሳተፈ ጠንካራ የፖለቲካ ትግል በማድረግ፣ ሕግ የማስከበር ርምጃዎችን በማጠናከር፣ ጽንፈኝነትን ለመግታት ከምንጊዜውም በበለጠ ጠንክሮ እንደሚሠራ አስታውቋል፡፡


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ “ነውጠኛ ጽንፈኞች” ያሏቸውን አካላት፣ ለግድያው ተጠያቂ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአቶ ግርማን መገደል በአስታወቁበት የፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ፤ “ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች፣ የፈጸሙት አስነዋሪ እና አሠቃቂ ተግባር ነው፤” ሲሉ ድርጊቱን በአጽንዖት ኮንነዋል።


አያይዘውም፣ “ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው፤” ብለዋል።


በሕግ እና በሥርዐት እንጂ በደቦ ፍርድ የግልም ኾነ የቡድን፣ የሕዝብንም ሆነ የአገር ጥቅምና ፍላጎት ማሳካት እንደማይቻል የገለጹት፣ የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በበኩላቸው፣ ሥርዐት አልበኝነትንና ሕገ ወጥነትን፣ ከመንግሥት ጎን ቆሞ እንዲያወግዝና እንዲታገል ለሕዝቡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡


ዐብን በአወጣው መግለጫ፣ ድርጊቱ አግባብነት ባላቸው ተቋማት ሳይጣራና አጥቂዎቹ ተለይተው ሳይታወቁ፣ ከጥቃቱ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ሲባል በአደባባይ እየተደረጉ ናቸው ያላቸውን ፍረጃዎች እና መግለጫዎች በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡


መንግስታዊ አካላት ግድያውን የፈጸሙት ታጣቂዎች፣ ጽንፈኞችና ኢመደበኛ አደረጃጀት ያላቸው በማለት ቢጠቅሱም እስካሁን ከግድያው ጋር ተያይዞ ኃላፊነት የወሰደ አካል ግን የለም፡፡


ግድያው ተፈጸመ የተባለበት የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ስለ ጉዳዩ ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ መግለጫ እንደሚሰጥ ቢያሳውቀንም፣ በተባለው ሰዓት ስንደውል ስልካቸው ሊመልስ አልቻለም፡፡


አቶ አቶ ግርማ የሺጥላ ማናቸው?


አቶ ግርማ የሺጥላ የዛሬ ሁለት ዓመት የአማራ ክልል የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮ ሓላፊ እጩ ኾነው ሲቀርቡ ለክልሉ ምክር ቤት በተነበበው የሕይወት ታሪካቸው መሰረት፤ የትውልድ ቦታቸው ሰሜን ሸዋ ዞን መሐል ሜዳ ሲኾን 48 ዓመታቸውን ነው።


የወቅቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር አቶ ግርማ የሸጥላን ለክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሓላፊነት ለክልል ም/ቤት በእጩነት ሲያቀርቡ ባሰሙት አጭር የህይወት ታሪካቸው ከ1988 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በሰሜን ሸዋ ዞን የአንጾኪያ ገምዛ የወረዳ ሥራ አስፈጻሚና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ፤ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን አደረጀጃት ዘርፍ ኃላፊ፣ የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ ኾነው አገልግለዋል።


የማስታወቂያ ወጣት ስፖርት ባህል ቱሪዝም ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የደብረ ብርሃን ፓርቲ ጉዳይ ኃላፊ፣ የባሶና ወረና ወረዳ አስተዳደር ማስታወቂያ ጸ/ቤት ኃላፊ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትልና ዋና አስተዳዳሪ ኾነው መሥራታቸውም ተገልጾ ነበር።


ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማእረግ የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ በትምህርት ደረጃቸው በቢዝነስ አድሚነስትሬሽን ሁለተኛ ድግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡


በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈው አቶ ግርማ የሽጥላ ወልደ ጻዲቅ ባለትዳርና የልጆች አባት መሆናቸው ታውቋል፡፡


አቶ ግርማ ከመገደላቸው አንድ ቀን አስቀድሞ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን ከተማ የሥራ ጉብኝት ማካሄዳቸው ተገልጾ ነበር።


የአቶ ግርማ የሽጥላ የአስከሬን ሽኝት እሁድ አዲስ አበባ ላይ እንደሚደረግ ፓርቲው የቀብር አስፈጻሚውን ኮሚቴ ጠቅሶ ይፋ አድርጓል። ቀብራቸውም በወላጆቻቸው ጥያቄና ፍላጎት መሰረት በትውልድ አገራቸው ስሜን ሸዋ ዞን መሃል ሜዳ ይፈጸማል ብሏል።
33 views21:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 00:33:09 ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከሱዳን የሚያወጣ ግብረ ኃይል ማቋቋሟን አስታወቀች
https://amharic.voanews.com/a/foreign-ministry-presser/7070790.html

በሱዳን የሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ውጊያ ከተጀመረበት እስከ ዛሬ ድረስ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና የሌሎች ሀገራት ዜጎች ከሱዳን እንዲወጡ፣ ኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።


የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፣ ለዚኹ ጉዳይ የተቋቋመ፣ የመንግሥት ኃይለ ግብር፣ በድንበር አካባቢ ተሠማርቶ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡


ቃለ አቀባዩ በዛሬው መግለጫቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መሪዎች ጋራ በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡አያይዘውም፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል፣ በታንዛኒያዋ ዛንዚባር ደሴት ላይ የሚደረገው ድርድር፣ በሒደት ላይ እንደኾነ ቢጠቅሱም፣ ከዚኽ ያለፈ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም፡፡


ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
28 views21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 23:05:50 በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያ ውይይቱ ቀጥሏል
https://amharic.voanews.com/a/tanzania-ethiopia-ola-talks/7070862.html

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት ላይ የሚያደርጉት ውይይት እንደቀጠለ ነው፡፡ ድርድሩ፥ በሁለቱ ወገኖች መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ሁከት እና አለመረጋጋት የማስቆም ተስፋ ተጥሎበታል።


በኬንያ እና በኖርዌይ አደራዳሪነት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል፣ ውይይቱ ባለፈው ማክሰኞ የተጀመረው፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በጎሣ ግጭት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ውጥረት እያየለ በመጣበት ወሳኝ ወቅት ነው።


የሰላም ድርድሩ፣ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቀጠለውን ግጭት እና አለመረጋጋት እንደሚያስቆም ተስፋ የሚያደርጉ ብዙዎች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገውን ውይይት በአዎንታ ተቀብለውታል።


በታንዛንያ የውጭ ግንኙነት ማዕከል መምህር እንደኾኑት አባስ ሙዋሊሙ ያሉ ተንታኞች፣ ኹኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ነው። የቅድመ ድርድር ንግግር መጀመሩ፣ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ የሚወስድ ርምጃ ነው፤ ያሉት ግጭቶቹን ሲከታተሉ የቆዩት ሙዋሊሙ፣ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ የበለጠ መሠራት እንዳለበት ያሠምሩበታል።


የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ለሰላም ንግግር መቀመጣቸው፣ ግጭቱ እያሳደረ ያለውን ጫና መረዳታቸውን እንደሚያሳይና አሁን በጋራ ችግሩን ለመፍታት ማሰባቸውን እንደኾነ መምህሩ አስረድተዋል፡፡ ንግግራቸው ስኬታማ የመኾን ዕድል እንዳለው ጠቁመው፣ ነገር ግን ሕገ መንግሥቱን ለመከለስና ኢትዮጵያን አንድ በሚያደርግ መልኩ ለማየት ቢመርጡ የበለጠ ስኬት ሊመጣ እንደሚችል መክረዋል፡፡


 




እንደ ሙዋሊሙ አስተያየት፣ አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ ክልሎች የራሳቸው አስተዳደር እንዲኖራቸው መፍቀዱ፣ ሕዝቦች የመገንጠል ፍላጎት እንዲኖራቸው ያበረታታል።


በቀጣናው ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን የሚከታተሉት ሌላው ተንታኝ፣ ኢብራሂም ራሂብ በበኩላቸው፣ የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ብሔራዊው የጸጥታ ተቋማት ለማካተት በሚደረገው ጥረት፣ እያየለ የመጣው ውጥረት የሚያሳየው፣ ተጨማሪ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ሒደቱን በጥንቃቄ ማስኬድ እንዳለበት ነው፤ ይላሉ።


የኢትዮጵያ መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ብሔራዊ የጸጥታ ተቋማቱ ለማካተት ያሳለፈው ውሳኔ ከፍተኛ ውጥረት መፍጠሩን ኢብራሂም ያወሳሉ፡፡ በኢትዮጵያ ኹሉም ክልሎች፣ የታጠቁ ኃይሎችን ጨምሮ ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ የሚያስተዳድሩ በመኾኑ፣ መንግሥት ከሁሉም ክልሎች የጦር መሣሪያዎችን በአንድ ጊዜ ማንሣት የሚችልበትን መንገድ መፈለግ እንደሚኖርበት ያሳስባሉ፡፡


በዛንዚባር ደሴት ላይ እየተካሔደ ስላለው ድርድር አስተያየታቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት የመንግሥቱ ዋና ቃል አቀባይ ቻርለስ ሂላሪ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የሚደረገው ንግግር፣ በዝግ እየተካሔደ በመኾኑ፣ ስለ ውይይቱ ምንም ዐይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ዛንዚባር ለውይይቱ የሚኾን ቦታ ከማዘጋጀት ውጪ፣ የድርድሩ አካል አለመኾኗንም ጨምረው አብራርተዋል።




የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ሰራዊት ጋራ ለመደራደር የሚያደርገው ጥረት የተለያዩ ምላሾችን እያስተናገደ ነው። አንዳንዶች፣ ንግግሩ ግጭቱን ለመፍታት የሚያስችል አንድ ርምጃ ነው፤ ብለው ያበረታታሉ፡፡ እንደ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ ያሉ ሌሎች አካላት ደግሞ፣ ትርጉም ያለው ድርድር ከመካሔዱ በፊት፣ “ሸኔ” በማለት የሚጠሩት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሚያደርሰው ጥቃት ስለ መቆሙ መረጋገጥ አለበት፤ ይላሉ።


የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ፣ ረቡዕ ዕለት በአወጣው መግለጫ፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ማኅበረሰቦች፣ በእነዚህ ኃይሎች ጥቃት ሊሰነዘርባቸው ይችላል፤ የሚለው ስጋት መቀረፍ ይኖርበታል፡፡ አልያ ትርጉም ያለው ድርድር ሊካሔድ አይችልም፤” ብሏል፡፡ በተደጋጋሚ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል እየፈጸሙ እና በንጹሐን ሰላማዊ ዜጎች ላይ


እልቂት እያደረሱ ያሉት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት - ሸኔ የሚፈጽማቸው ጥቃቶች መቆማቸውን ማረጋገጥ ዋና ነገር እንደኾነም፣ ኮሚቴው አመልክቷል።


ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በቁጥር እያደገ መጥቷል፤ የኦሮሚያ ክልልም፣ ከፍተኛ ብሔር ተኮር ጥቃት እያስተናገደ ነው። መንግሥት ለነዚኽ ጥቃቶች፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ተጠያቂ ቢያደርግም፣ ቡድኑ ግን አይቀበለውም። ግጭቱን ለማስቆም፣ መንግሥት በአጸፌታ የሚወስደው ርምጃም፣ ከባድ እና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ምሬት እንዲፈጠር አድርጓል።




ይህም ኾኖ ታጣቂው ሠራዊት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ስጋት ለመፍጠር፣ አደረጃጀት እና የጦር መሣሪያ እጥረት እንዳለበት፣ አንዳንድ ባለሞያዎች አስተያየት ይሰጣሉ።


ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገው ውይይት፣ ለተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል የሚጠበቅ ሲኾን፣ ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል።


/ቻርለስ ኮምቤ ከዳሬሰላም ያደረሰንን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች/
40 views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 23:04:50 “ሸዋሊድ”ን በቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ ነው
https://amharic.voanews.com/a/harari-shuwal-eid/7070744.html

በኢትዮጵያ ሐረሪ ክልል፣ በየዓመቱ የሚከበረውን ሸዋሊድ በዓልን በቅርስነት የማስመዝገብ ዕድል መኖሩ ተጠቆመ። በዓሉን አስመልክቶ በተዘጋጀ የጥናት ውይይት ላይ፣ በመጪው ኅዳር ወር በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ በቅርስነት ሊመዘገብ እንደሚችልም ተመልክቷል።


“ሸዋሊድ”፥ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ የወርኀ ረመዳን ጾም ከተጠናቀቀ በኋላ፤ የእምነቱ ተከታዮች እንደፍላጎታቸው በተጨማሪ የሚጾሟቸው ስድስት የወርኀ ሸዋል ቀናት ሲጠናቀቁ የሚከበር በዓል ነው። በኢትዮጵያ ይህ በዓል የሚከበረው፣ በሐረሪ ክልል በሐረር ከተማ ውስጥ ነው።


ትላንት ኀሙስ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከበረው በዚኽ በዓል ላይ በተዘጋጀ ዐውደ ጥናት፣ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ሓላፊ ኤልያስ ሽኩር፤ በዓሉ በመጪው ኅዳር ወር ከኢትዮጵያ የማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርሶች አምስተኛው ኾኖ ሊመዘገብ እንደሚችል ተናግረዋል።


“ሸዋሊድ” ሃይማኖታዊ መነሻ እንዳለው በክልሉ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ገልጸዋል። ያም ኾኖ አከባበሩ ባህላዊ እንደኾነ ይስረዳሉ። በባህላዊ ልብስ አጊጦ በባህላዊ ጭፈራ የሚከበር የአደባባይ በዓል ነው። ከዚኽ ቀደም፣ የሐረሪ ሴቶች ባላቸው አልባሳት እና መዋቢያዎች አጊጠው በአደባባይ ሲጫወቱ የሚውሉበት ብቸኛ ቀን ስለነበር፣ ወንዶች ሴቶችን በግላጭ የሚያዩበት ብቸኛ አጋጣሚ እንደነበር ተሳታፊዎች አውስተዋል። በዚኽም ምክንያት በዓሉ እንደ መተጫጫ ይቆጠርም ነበር፤ ይላሉ።


ሴቶች፣ እንደቀደሙት ዘመናት ቤት የሚውሉ ባለመኾናቸውና ዘመናዊ የመገናኛ አማራጮችም በመኖራቸው፣ ሸዋሊድ ዋነኛ የመተጫጫ ቀንነቱን ያጣ ቢመስልም፣ ሁሉም ወደ አደባባይ ወጥቶ የሚገናኝበት ቀን መሆኑ ስላልቀረ፣ በዚች ዕለት ተያይተው ለትዳር የበቁ በርካቶች እንደኾኑ ተሳታፊዎቹ ይናገራሉ።


የሐረሪ ክልል፣ ጀጎልን በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርስነት ያስመዘገበች፣ የሰላም ከተማ ተብላ የተሰየመች፣ እንዲሁም “የጅብ ምገባ”ን የመሰሉ ትዕይንቶች የምታስተናግድ ከተማ እንደኾነች የሚናገሩት ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ፣ ሸዋሊድ፥ የሐረሪ ብሔረሰብ በዓል ብቻ መኾኑ ቀርቶ፣ ከሌሎች ጋራ ወንድማማችነትን የምናጠብቅበት በዓል ይኾናል፤ ብለዋል።


በበዓሉ ላይ ከሶማሌ፣ ከኦሮሚያ እና ከአፋር ክልሎች፣ እንዲሁም ከዐማራ ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ፣ ከደቡብ ክልል የስልጤ ዞንና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የባህል ቡድን ተወካዮች ተገኝተዋል።


አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪ፣ ሌሊቱን ሙሉ ሳይተኛ በዓሉን በሚያከብርበት የሸዋሊድ ላይ ያገኘናቸው ቱርካዊ ጎብኚ፣ ሐረር በብዙ ነገር ከአገራቸው ጋራ እንደምትመሳሰል ገልጸዋል።


በዚኹ የ“ሸዋሊድ” በዓል ላይ ለመታደም፣ ድሬዳዋ እና ዐዲስ አበባን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ክፍላተ ዓለማት በሺሕ የሚቆጠሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች ሐረር ከተማ ገብተዋል።
39 views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 23:03:50 ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
https://amharic.voanews.com/a/7070843.html

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች።
39 views20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ