Get Mystery Box with random crypto!

እለታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @eletawizena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-08 14:35:20 የፈረንሳዩ ማክሮን ቻይና ይገኛሉ
https://amharic.voanews.com/a/macron-china/7037562.html

ቻይና በዩክሬንና በሌሎችም ግጭት ባሉባቸው የዓለም ክፍሎች ሰላምን በተመለከተ በጋራ ሃላፊነት እንድትወስድ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግን በሚያገኙበት ወቅት አጽንኦት እንደሚሰጡት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ተናግረዋል፡፡


በቻይና የፈርንሳይ ኤምባሲ በመገኘት ለአገራቸው ዜጎች ንግግር ያደረጉት ማክሮን፣ ዩክሬን፣ ኢራን እና ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን፣ በተለይም ሰላምን በሚመለከት ቻይና በጋራ ሃላፊነት የምትወስድበትን ሁኔታ ከፕሬዚዳንት ሺ ጋር በሚኖራቸው ውይይት ትኩረት እንደሚሰጡት አስታውቀዋል፡፡


የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮንደር ላይን ከማክሮን ጋር አብረው ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የአውሮፓን አንድነት ለማሳየት ነው ተብሏል፡፡


በጉብኝታቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደው ጦርነት ዋና አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል፡፡
149 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 03:29:06 ማክሰኞ፡-ጋቢና VOA
https://av.voanews.com/clips/VAM/2023/04/03/20230403-213000-VAM131-program_original.mp3

Gabina VOA is designed to be an infotainment youth radio show broadcasting to Ethiopia and Eritrea in the Amharic language. The show brings varied perspectives on issues concerning young people in the Horn of Africa region. “Gabina” in the Amharic language is a front-row taxi ride.
155 views00:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 01:55:47 በርካታ የትራምፕ ደጋፊዎች ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ድጋፍ ለመግለጽ አደባባይ ወጡ
https://www.bbc.com/amharic/articles/czdj43vq2y9o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ ለቀድሞ ፕሬዝዳንት ያላቸው ድጋፍ ለመግለጽ አደባባይ ወጡ።
146 views22:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 22:26:39 ታሊባን አፍጋኒስታናውያን ሴቶችን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥራ አገደ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g69d99e44o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

አፍጋኒስታንን የሚያስተዳድረው ታሊባን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚሠሩ የአገሩ ሴቶችን ከሥራ ማገዱን ድርጅቱ አስታወቀ።
146 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 16:01:49 የ10 ሺህ ሰዎች አንጎል የተከማቸበት የዴንማርክ የሥነ አዕምሮ ምርምር ተቋም
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw08w9dld18o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

የደቡብ ዴንማርክ ዩኒቨርሲቲ 10 ሺህ የሚጠጉ በዓመታት ሂደት ውስጥ የተሰበሰቡ የሰው ልጅ አንጎሎችን አከማችቷል። እነዚህም በአዕምሮ ጤና ዙሪያ ለሚደረጉ ጥናት እና ምርምሮች እንዲረዳ በሚል ከ1940ዎቹ ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ ድረስ ለአራት አስርት ዓመታት የተሰበሰቡ ናቸው። የዚህ ስብስብ ብዛት በዓለም ላይ ካሉት ቀዳሚው የሰው ልጅ አንጎል ክምችት እንደሆነ ይታመናል። የሕክምና ሙያተኞች እንደሚሉት እነዚህ አንጎሎች ያለሕሙማኑ ፈቃድ የተሰበሰቡ ቢሆኑም፣ ከዕድሜ ጋር በሚከሰቱ እና በሌሎች የአዕምሮ ጤና እክሎች ላይ ለሚደረጉ ምርምሮች ጠቃሚ ሆነዋል።
154 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 11:46:47 እስራኤል ወታደሮችን ገጭቷል የተባለ ፍልስጤማዊ ገደለች
https://amharic.voanews.com/a/7032904.html

የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች፣ ትናንት ቅዳሜ ምሽት አንድ ላይ የነበሩ ሶስት እስራኤላውያን ወታደሮችን በመኪናው ገጭቷል የተባለ ተጠርጣሪ ፍልስጤማዊን ተኩሰው መግደላቸው ተነገረ፡፡


የእስራኤል መከላከያ ሶስቱም ወታደሮች ህክምናቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን ገልጾ አንደኛው ጽኑ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡


እስራኤል እና ፍልስጤማዊያን በኃይል በተያዘው ዌስት ባንክ የሚያደርጉት ግጭት ካለፈው ዓመት ወዲህ እየተባባሰ መምጣቱ ተመልክቷል፡፡


በዚሁ ግጭት በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ 86 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡


ፍልስጤማዊያኑ በእስራኤላውያን ላይ ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች መሞታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
160 views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 12:21:56 የዐዲስ አበባ ቤቶች ፈረሳ እና የነዋሪዎች ሮሮ
https://amharic.voanews.com/a/7032932.html

በዐዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ ሕገ ወጥ የተባሉ ቤቶችን የማፍረስ እና ነዋሪዎችን የማስነሣት ተግባር ተባብሶ ቀጥሏል፤ ሲሉ ተጎጂዎች ገለጹ።

አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ እና ቤታቸው መፍረሱን የተቃወሙ ግለሰቦች፣ ከእነቤተ ሰዎቻቸው፣ መጠለያ በማጣት ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ተጎጂዎች ስለ አቀረቡት ቅሬታ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ/ዶክተር/፣ ምላሽ ለመጠየቅ፣ የእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ሊነሣልን አልቻለም፡፡

ይኹን እንጂ ከንቲባው፣ ከዚኽ ቀደም ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ምላሽ፣ ርምጃው የተወሰደው፣ ሕገ ወጥ ግንባታ በአከናወኑቱ ላይ ነው፤ ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ርምጃው ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን የጣሰ እንደኾነ በመተቸት ትላንት መግለጫ ያወጣው ኢሰመኮ፣ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ በተፈጸመው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ የማስነሣት ርምጃ የተጎዱ ሰዎች፣ በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት ሊያገኙ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

የኮሚሽኑ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ብራይትማን ገብረ ሚካኤል፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ርምጃው እየተወሰደ ያለው፣ ኢትዮጵያ የአጸደቀችውን ዓለም አቀፍ ሕግ በተፃረረ መልኩ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።




 
86 views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 17:38:40 የተወካዮች ምክር ቤት የዶ/ር ጫላ ዋታን ያለመከሰስ መብት አነሳ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0d4kg8mkdjo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፓርላማ አባል የሆኑትን እና የቀድሞ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብት አነሳ። የእንደራሴው ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ለምክር ቤቱ ጥያቄ የቀረበው ዛሬ መጋቢት 25/2015 ዓ.ም ሲሆን፣ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ተወስኗል። ዶ/ር ጫላ ዋታ የቡሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ጊዜ የመንግሥት ግዢ ሥርዓትን ሳይከተሉ ግዢዎችን በመፈጸማቸው ነው የሕግ ከለላቸው የተነሳው።
113 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 12:33:22 የመጋቢት 25 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8C%8B%E1%89%A2%E1%89%B5-25-%E1%89%80%E1%8A%95%E1%8D%A3-2015-%E1%8B%93-%E1%88%9D-%E1%8B%A8%E1%88%B5%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8B%98%E1%8C%88%E1%89%A3/a-65219497?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

ሁለት ሽንፈቶችን አስተናግዶ የተመለሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ። ለመሆኑ ለተደጋጋሚ ሽንፈቱ ኃላፊነት የሚወስደው ማን ነው ተባለ? የስፖርት ተንታኝ አነጋግረናል ። ኢትዮጵያውያን ለድል ስለበቁበት የአትሌቲክስ ፉክክሮች መረጃዎችን እናቀብላችኋለን ። ሌሎች የየእግር ኳስ መረጃዎችንም አካተናል ።
121 views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 09:16:18 ሩሲያ ምግብ ለሰሜን ኮሪያ ሰጥታ በምላሹ ጦር መሳሪያ ልትቀበል መሆኑን አሜሪካ ገለጸች
https://www.bbc.com/amharic/articles/crgjed2vye0o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

ሩሲያ ምግብ በጦር መሣሪያ ለመለወጥ ልዑካን ቡድን ወደ ሰሜን ኮሪያ ልትልክ መሆኗን የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅነንት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ተናገሩ።
118 views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ