Get Mystery Box with random crypto!

እለታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @eletawizena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-22 20:47:05 የስፔን የባህር ዘቦች 70 ፍልሰተኞችን ታደጉ
https://amharic.voanews.com/a/7148519.html

የስፔን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በአንዲት ጀልባ ላይ ተሳፍረው በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ይጓዙ የነበሩ 70 ፍልሰተኞችን መታደጋቸውን አስታውቀዋል።


ግራን ካናሪያ ከተባለችው የስፔን ደሴት 105 ኪ.ሜ ላይ ጀልባይቱን እንዳገኙ ያስታወቁት የጠረፍ ጠባቂዎች፣ ከፍልሰተኞቹ መሃል ሕጻናትም ይገኙበታል ብለዋል።


ፍልሰተኞቹ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ደሴት ተወስደው በቀይ መስቀል እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።


ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ወደ  6 ሺሕ የሚጠጉ ፍልሰተኞች ካናሪ ደሴት መድረሳቸውን የስፔን መንግስት አስታውቋል። ይህም ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር 31 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
42 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 20:46:05 የተሰወረችውን ባሕር ሰርጓጅ ጀልባ ለማግኘት የተያዘው ጥረት ቀጥሏል
https://amharic.voanews.com/a/missing-sub-serach/7148411.html

አምስት ሰዎችን ይዛ ባለፈው እሁድ ወደ ባህር የጠለቀችውና ደብዛዋ የጠፋው ሰርጓጅ ጀልባ፣ የያዘችው ኦክሲጂን ዛሬ ሐሙስ እንደሚያልቅ ሲጠበቅ፣ ፍለጋው ተጧጡፎ ቀጥሏል።


ለ96 ሰዓት ሊያቆይ የሚችል መጠን ያለው ኦክሲጅን ይዛ፣ አምስት ቱሪስቶችን አሳፍራ፣ ከሴይንት ጆን፣ ካናዳ ባህር ዳርቻ ባለፈው ዓርብ የተነሳችው ሰርጓጅ ጀልባ፣ ከመቶ ዓመት በፊት የታይታኒክ መርከብ ወደሰጠመችበት አካባቢ በመጓዝ፣ ከዛም ወደታች 4 ኪ.ሜ ከባሕሩ ጠልቃ በመቅዘፍ ላይ ነበረች። ከእሁድ አንስቶ ግን ከተቆጣጣሪዋ እናት መርከብ ጋር የነበራትን ግኑኝነት አቋርጣለች፡፡


ለተጓዦቹ ሕይወት የሚሰጠው የየያዘችው ኦክሲጅን ዛሬ ሐሙስ ማለዳ እንደሚያልቅ ሲገመት፣ ዓለም አቀፍ የባህር ጉዳይ አዋቂዎች እና የነፍስ አድን ሠራተኞች በውስጧ ያሉትን ሰዎች በሕይወት ለማግኘት ርብርባቸውን ቀጥለዋል።


በውስጧም አንድ የታይታኒክ ታሪክ አዋቂ፣ ፓኪስታናዊ አባት እና ልጅ፣ አንድ አውሮፕላን አብራሪ እና አንድ እንግሊዛዊ ተጓዥ ይገኙበታል። 


ባለፉት ሁለት ዓመታት 46 የሚሆኑ ተጓዦች ታይታኒክ ወደ ሰመጠችበት አካባቢ በሰማጭ ጀልባዋ ጠልቀው የመጎብኘት ዕድል እንደነበራቸው ለማወቅ ይተችሏል። 
45 views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 18:45:40 VOA60 World - President Biden to Host Modi for Talks
https://amharic.voanews.com/a/voa60-world---president-biden-to-host-modi-for-talks/7148284.html

President Joe Biden hosts Indian Prime Minister Narendra Modi for talks Thursday at the White House. Washington wants India to be a strategic counterweight to China and sees India as a critical partner.
54 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 18:44:50 VOA60 America - U.S. Coast Guard, other agencies still searching for missing submersible
https://amharic.voanews.com/a/voa60-america---u-s-coast-guard-other-agencies-still-searching-for-missing-submersible/7148283.html

As a multinational search continues, time is running out for five people aboard a missing submersible that lost contact with its mother ship on Sunday as it descended to the wreck of the Titanic. The oxygen tanks would likely be depleted some time on Thursday morning.
52 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 18:43:40 VOA60 Africa - Increasing number of civilians fleeing Darfur hit by militia attacks
https://amharic.voanews.com/a/voa60-africa---increasing-number-of-civilians-fleeing-darfur-hit-by-militia-attacks/7148281.html

Sudan: An increasing number of civilians fleeing El Geneina, a city in Darfur hit by repeated militia attacks, have been killed or shot at as they tried to escape by foot to Chad since last week, the executive director of the Darfur Network for Human Rights said.
48 views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 17:42:22 ኢትዮጵያ ዓባይ ግድብን ለአራተኛ ግዜ ልትሞላ ነው
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-nile-dam-/7148258.html

ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ አራተኛ ዙር ሙሌት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ አስታውቀዋል።


4.2 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል የተባለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ አንስቶ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ተቃውሞ ቢገጥመውም፣ አገሪቱ ግንባታውን ቀጥላለች፡፡


“የህዳሴው ግድብ አራተኛ ሙሌት ተቃርቧል። ያለፉት ሶስት ሙሌቶች የታችኛው ተፋሰስ አገሮችን አላወኩም። ቀጣይ ሙሌቶችም የተለዩ አይሆኑም” ሲሉ ደመቀ መኮንን መናገራቸውን የኤኤፍፒ ሪፖርት አመልክቷል።


“የጋራ የሆነውን የአፍሪካ ወንዝ ለብቻ ለመጠቀም የሚሹ ኃይሎችን አሉታዊ ትርክት ተቋቁሞ፣ ፕሮጀክቱ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ነው” ሲሉ አክለዋል።


ኢትዮጵያ ሙሌቱን እንድታቆም ግብጽ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች፡፡


ደመቀ መኮንን በተናገሩበት ከፍተኛ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ከኡጋንዳ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳን እና ታንዛኒያ ተገኝተዋል።


ሱዳንም ሆነች ግብጽ በጉባኤው ላይ እንዳልተሳተፉ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።


የሱዳኑ ፕሬዝደንት አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን፣ አዲስ አበባ እና ካርቱም በግድቡ ጉዳይ “በአንድ ላይ የተሰለፉ እና የተስማሙ ናቸው” ሲሉ ባለፈው ጥር መናገራቸውን ዘገባው አስታውሷል።
55 views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 17:41:37 የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር እና የሶማሊያው ፕሬዝደንት በፔንታጎን ተወያዩ
https://amharic.voanews.com/a/Austin-welcomes-Somalia-s-president-to-the-pentagon/7148204.html

የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን፣ የሶማሊያውን ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ትናንት በፔንታጎን ተቀብለው አነጋግረዋል።


ሁለቱ ወገኖች በመከላከያ ትብብር እና በቀጠናው ባሉ የጸጥታ ስጋቶች ላይ ተነጋግረዋል። 


ሶማሊያ በአሁኑ ወቅት በአል ሻባብ ላይ የምታደርገውን ዘመቻ እና ሶማሊያውያን በመክፈል ላይ ያሉትን መስዋትነት ሎይድ ኦስትን አድንቀዋል። በማዕከላዊ ሶማሊያ በአል ሻባብ ላይ የተደረገው ውጤታማ ዘመቻ እና ቀጣይነት ያለው ድል እንዳበረታታቸውን ኦስትን ገልጸዋል። 


በሶማሊያ የሚገኘውን የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ለመቀነስ ዝግጅት በሚደረግበት በዚህ ወቅት፣ የዓለም አቀፍ ድጋፍ እና ቅንጅት አስፈላጊነት ላይ ሁለቱ ወገኖች መወያየታቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። 


የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ በበኩላቸው ጠንካራ እና የተረጋጋች ሶማሊያን ለመገንባት አሜሪካ በማሳየት ላይ ላለቸው ቀጣይነት ያለው ወታደራዊ እና ሲቪላዊ ትብብር አመስግነዋል።
51 views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 16:24:00 በሕንድ ቅንጡ ሆቴል ለሁለት ዓመት ሳይከፍል የቆየው የ70 ሺህ ዶላር ባለዕዳ ሆነ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c72vx03yv1qo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

አንድ ግለሰብ በሕንድ ዋና ከተማ ዴልሂ ውስጥ ካሉ ባለ አምስት ኮከብ ቅንጡ ሆቴሎች በአንዱ አምስት ሳንቲም ሳይከፍል ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ መክረሙ ተደረሰበት።
61 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 13:24:02 ኢላን መስክና ማርክ ዛከርበርግ በፍርግርግ አጥር ተከበው ቡጢ ለመግጠም ተስማሙ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2rjz3g14lo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

ሁለቱ ጉምቱ የዓለማችን የቴክኖሎጂ አውራዎች መስክና ዛከርበርግ ቡጢ ለመግጠም ተስማሙ። ከገጠምን አይቀር ከልካይ በሌለበት በፍርግርግ በታጠረ መድረክ ይሁን ያሉት ቢሊየነሮቹ በቡጢ ሊዋጣላቸው ነው።
69 views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 10:41:24 በኬንያ ራሳቸውን አስርበው ሲጸልዩ በነበሩ ሰዎች ሞት ከተጠረጠሩት አንዱ በእስር ላይ ሳለ ሞተ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4ne4jn1rkxo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

በኬንያ ሕጻናትን ጨምሮ የአንድ እምነት በርካታ አባላትን በረሃብ ለሞት በመዳረግ ከተጠረጠሩ 30 ግለሰቦች መካከል አንዱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እያለ ሕይወቱ አለፈ።
79 views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ