Get Mystery Box with random crypto!

እለታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @eletawizena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-17 10:17:06 አንድ የተከበሩ የሩሲያ የጦር ሹም ወደ ዩክሬን ተመለሱ
https://amharic.voanews.com/a/7052786.html

የዩክሬን ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ ትላንት ቅዳሜ ባደረጉት ዕለታዊ መግለጫቸው የዩክሬንን የሰላም ቀመር በተመለከተ ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ዘለግ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ። ዘለንስኪ ውይይታቸውን “ፍጹም ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ እና ጠለቅ ያለ” ሲሉ ገልጸውታል። ሁለቱ መሪዎች በመጪው በጋ ስለሚደረገው የሰሜን አትላንቲክ ጦር የመሪዎች ስብሰባ  በተመለከተም ተወያይተዋል።


በሌላ በኩል የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር በእሁድ እለት ባወጣው የስለላ መረጃ፤ የሩሲያ የዩክሬን ወረራ አስመልክቶ በሩስያ የቪዲቭ የአየር ወለድ ጦር አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ኮሎኔል ሚካሂል ቴፕሊንስኪ በጥር 2023 ከስራቸው ከተሰናበቱ በኋላ በዩክሬን ወገን በትልቅ ሚና የመመለሳቸው "ዕድል በጣም ከፍተኛ ነው" ብሏል።


ሚኒስቴሩ ቴፕሊንስኪን “በደረጃ እና በማዕረግ ሩሲያ ውስጥ በሰፊው ከሚከበሩት ጥቂት ከፍተኛ ጄኔራሎች መካከል አንዱ ሳይሆኑ አይቀርም” ሲል ገልጿል። አያይዞም “በስራቸው ላይ የቅርብ ጊዜ  የታየው ውዝግብ በሩሲያ በዩክሬን ስላለው የሩሲያ ወታደራዊ አካሄድ በአጠቃላይ በጦር ውስጥ ባሉ አንጃዎች መካከል ከፍተኛ አለመግባባት መኖሩን ያሳያል” ብሏል።


በተያያዘ ሩሲያ በተሰኘችው የዩክሬን ከተማ በፈጸመችው የአየር ድብደባ 21 ሰዎች ሞተዋል። ዘለንስኪ ስሎቫኒክ እና ዶንባስን ለማዳን የሚደረገው ተልዕኮ እንደሚቀጥል በመግለጫቸው አስታውቀዋል።


በአንጻሩ ዛሬ በተከበረው የትንሳኤ ክብረበዓል ላይ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን ሞስኮ በሚገኘው አዳኙ ክርስቶስ በተሰኘው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ካቴድራል የቅዳሴ ስነስርዓት ላይ ታድመዋል።


 
182 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 08:54:44 ቅዳሜ፡-ጋቢና VOA
https://av.voanews.com/clips/VAM/2023/04/14/20230414-213000-VAM131-program_original.mp3

Gabina VOA is designed to be an infotainment youth radio show broadcasting to Ethiopia and Eritrea in the Amharic language. The show brings varied perspectives on issues concerning young people in the Horn of Africa region. “Gabina” in the Amharic language is a front-row taxi ride.
173 views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 13:12:51 የጣራ ቆርቆሮ ሠርቀዋል በሚል የገንዘብ ሚኒስትሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
https://amharic.voanews.com/a/7052013.html

ዝቅተኛ የኑሮ ደርጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ቤት መሥሪያ የሚውል የጣራ ቆርቆሮ ሰርቀዋል በሚል የዩጋንዳው የገንዘብ ሚኒስትር አሞስ ሉጎሉቢ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።


ካራሞጃ በተባለው አካባቢ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ቤት መሥሪያ ሊውል የነበረውን ቆርቆር ስርቆት በተመለከተ 10 ሚኒስትሮች፣ 31 የምክር ቤት አባላትና ሌሎች 13 የመንግስት ባለሥልጣናትን እየመረመረ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።


የዩጋንዳው ተቃዋሚ መሪ ባቢ ዋይን ፕሮጄውን በሚመሩት ሚኒስትሮች ላይ የተፈጸመው እሥር “መሸፋፈኛ” ነው በማለት፣ ለረጅም ግዜ አገሪቱን የመሩትን ዩዎሪ ሙሴቪኒንና መንግስታቸውን የከፋ ሙስና በመፈጸም ወንጅለዋል።


የሙዚቃ ሥራቸውን ወደጎን በመተው ፖለቲካ ውስጥ የገቡት ባቢ ዋይን ሙሴቪኒን ጨምሮ ጠቅላላ ካቢኔያቸው በስርቆት ወህኒ መረውድ ነበረባቸው ማለታቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
84 views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:46:27 የጣሊያን የጠረፍ ጠባቂዎች 700 ፍልሰተኞችን ከሞት ታደጉ
https://amharic.voanews.com/a/italy-migrants/7048826.html

ትናንት ረቡዕ በሲሲሊው ካታኒያ ወደብ በአገልግሎት ብዛት አርጅቶ ከዛገው ጀልባ ውስጥ የጣልያን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከሞት ያዳኗቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ደስታቸውን ሲገልጹ ታይቷል፡፡


ነዳጅ አልቆባት ባህር ላይ ቆማ በነበረችው ጀልባ ውስጥ 700 የሚደርሱ ፍልሰተኞች እንደነበሩ ተነግሯል፡፡


በዚህ የአውሮፓውያኑ 2023 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ በአፍሪካና አውሮፓ ደቡባዊ የባህር ዳርቻዎች ባለው አደገኛ የባህር መስመር ላይ 441 ፍስልተኞች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡


ለብዙዎቹ ፍልስተኞች ሞት አስተዋጽኦ ያደረገው “በመንግሥት የሚመራው የነፍስ አድን ሥራ መዘግየቱ”  እንደሆነ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ትናንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡


የጣልያን ቀኝ ክንፍ መንግሥት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን ፍልሰተኞች ብዛትና ሞት ለመታደግ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ለስድስት ወራት የሚቆይ ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቷል፡፡ ከዚሁ በተያያዘ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ መሎኒ እና ካቢኔያቸው የ5 ሚሊዮን ዩሮ (5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር) ወጪ ፈቅዷል፡፡


ይህ የአውሮፓውያን ዓመት ከገባ ወዲህ የጣልያን ወታደራዊ ጀልባዎች ወይም የበጎ አድራጎት መርከቦች ባህሩ ላይ የደረሱላቸው ወይም ካለምንም ዕርዳታ የደረሱ 31 ሺ ፍልሰተኞች ጣሊያን መግባታቸውን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
121 views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:04:47 ጋና ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበትን የወባ ክትባት በማጽደቅ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2ermmznqe8o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

ባበለጸጉት ሳይንቲስቶች “ዓለምን ቀያሪ” የሚል ስያሜ የተሰጠወን የወባ ክትባት በማጽደቅ ጋና የመጀመሪያው ሀገር ሆናለች። R21 በመባል የሚጠራው ክትባቱ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ክትባቶች ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ውጤታማ ነው ተብሏል።
117 views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:30:43 ሱቶን ዩናይትድ አቻ ይለያያል፣ ቼልሲ ደግሞ ይሸነፋል አለ
https://www.bbc.com/amharic/articles/ckkq7q7q972o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን በዚህ ሳምንት በሚደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በሰጠው ግምት ዩናይትድ አቻ ይለያያል፣ ቼልሲ ደግሞ በሜዳው ሽንፈት ያስተናግዳል ብሏል። ክሪስ ሱቶን የ31ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ግምቶችን እንደሚከተውል ሰጥቷል።
131 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 16:36:37 የኦሮሚያ ክልል የልዩ ኃይል አደረጃጀትን ሥምሪት ማቆሙን አስታወቀ
https://amharic.voanews.com/a/oromia-regional-forces/7049395.html

የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማት በማስገባት መልሶ የማደራጀት ተግባር በማከናወን ላይ መኾኑን የገለጸው የኦሮሚያ ክልል፣ የልዩ ኃይል አደረጃጀትን ሥምሪት ማቆሙን፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ አስታወቁ።


የክልሉን የጸጥታ ማስከበር ሥራም፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ መረከባቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።


በተመሳሳይ መልኩ፣ የደቡብ እና የሶማሌ ክልሎችም፣ በፌዴራል መንግሥት የተላለፈውን የልዩ ኃይል መዋቅራዊ ለውጥ ውሳኔ በመተግበር ሒደት ላይ መኾናቸውን አስታውቀዋል፡፡


የልዩ ኃይል አባላቱ፣ በመደበኛ የጸጥታ ተቋማት ማለትም በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት እና በክልሎች ፖሊስ ሠራዊት ውስጥ እንደሚካተቱ የየክልሎቹ አመራሮች አስረድተዋል።


ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
113 views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 02:27:21 የደብረ ብርሃን፣ ጎንደርና ደሴ ከተሞች ከጸጥታ ጋር የተያያዙ ጥብቅ ክልከላዎችን ጣሉ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pq16dm30zo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

የክልሎችን ልዩ ኃይሎች መልሶ ለማዋቀር ከተወሰነው ውሳኔ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የአማራ ክልሎች ውጥረት መንገሱን ተከትሎ የደብረ ብርሃን፣ ጎንደርና ደሴ ከተሞችን ከጸጥታ ጋር የተያያዙ ጥብቅ ክልከላዎችን ጣሉ።
143 views23:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 02:05:10 ለፍቅር ሲል የምልክት ቋንቋ የተማረው አፍቃሪ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0exd6jdk5o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

ወጣቱ አፍቃሪ የሕይወት አጋሩ ጋር የተገናኙት ከሦስት ዓመት በፊት ነው። ፍቅረኛው መስማትም ሆነ መናገር አትችልም። እናም ከፍቅረኛው ጋር ለመግባባት የምልክት ቋንቋ ማጥናት ጀመረ። ከሦስት ዓመት በኋላ ቋንቋውን በሚገባ ተምሮ ፍቅራቸውን ከመግለጽ ባለፈ ሌሎች ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ለመርዳት እየሰሩ ነው።
135 views23:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:35:34 ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
https://amharic.voanews.com/a/7047707.html

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች።
161 views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ