Get Mystery Box with random crypto!

እለታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @eletawizena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-23 01:53:06 ዐርብ፡-ጋቢና VOA
https://amharic.voanews.com/a/7129323.html

Gabina VOA is designed to be an infotainment youth radio show broadcasting to Ethiopia and Eritrea in the Amharic language. The show brings varied perspectives on issues concerning young people in the Horn of Africa region. “Gabina” in the Amharic language is a front-row taxi ride.
14 views22:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 23:47:58 ሐሙስ፡-ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና
https://amharic.voanews.com/a/7127937.html

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።


ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
22 views20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 22:13:33 ፈንድቃ የኪነ-ጥበብ ማዕከል እንዳይፈርስ ጥሪ ቀረበ
https://www.dw.com/am/%E1%8D%88%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%89%83-%E1%8B%A8%E1%8A%AA%E1%8A%90-%E1%8C%A5%E1%89%A0%E1%89%A5-%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%8A%A8%E1%88%8D-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B3%E1%8B%AD%E1%8D%88%E1%88%AD%E1%88%B5-%E1%8C%A5%E1%88%AA-%E1%89%80%E1%88%A8%E1%89%A0/a-66008098?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

የአዲስ አበባ ብሎም የኢትዮጵያ አንዱ ድምቀት የሆነዉ ፈንዲቃ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያን ሕዝብ የጋራ ባህል፤ እውቀት፣ ታሪክና የአብሮነት መገለጫዎች በሙዚቃ፣ በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በሥነ-ሥዕል፣ በሥነ-ጽሑፍ እና በተያዩ ኪነ-ጥባባዊ ክንዋኔዎች የሚያስተዋውቀዉ ማዕከል ፍረስ መባሉን ብዙዎችን አስደንግጧል አሳዝኗል።
33 views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:53:11 በኦሮሚያ ክልል የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ በታጣቂዎች ተገደሉ
https://amharic.voanews.com/a/oromia-killing/7148586.html

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ፣ ባለፈው ማክሰኞ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ)፣ ስለ ግድያው መረጃው ቢደርሰውም፣ በቦታው ተገኝቶ ማጣራት አለመቻሉን ገልጿል።


በኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ በቀለ ቃቻ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ያስታወቀው፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ነው።


የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት፣ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው፣ አስተዳዳሪው፥ በአዳማ ከተማ ስብሰባ ተሳትፈው ከተመለሱ በኋላ፣ እሑድ ምሽት 3፡00 አካባቢ፣ ኢሉ ወረዳ፣ አስጎሪ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እንደተወሰዱ አመልክቷል።


ባለፈው ማክሰኞ፣ ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ደግሞ መገደላቸውን ጠቁሟል።


የደቡብ ምስራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ታዬ ጉዲሳ፣ ባሰፈሩት የኀዘን መግለጫ፣ “አቶ በቀለ፣ ጠላት በፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ተገድለዋል፤” ብለዋል።


“ጠላት” በማለት የጠቀሱትን አካል ማንነት ግን በስም ለይተው አልገለጹም።


ሟቹ አስተዳዳሪ፣ “የሕዝቡን ጥቅም ለማስከበር ቁርጠኛ የኾኑና ከራስ ወዳድነት ነፃ የኾኑ መሪ” ነበሩ፤ በማለትም አክለዋል አቶ ታዬ።


የአቶ በቀለ ቃቻ የቀብር ሥነ ሥርዐት፣ በዛሬው ዕለት መፈጸሙን፣ የሰዴን ሶዶ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።


በአስተዳዳሪው ግድያ ዙሪያ፣ ከሰዴን ሶዶ ወረዳ እና ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት፣ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።


በኦሮሚያ ክልል የዚኽ ዐይነቱ ግድያ ሲፈጸም፣ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።


በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ የኦዳ ባርጋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አብዲሳ ቀነኒ፣ ባለፈው ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በበካቴ ከተማ፣ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን፣ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ገልጾ ነበር።


በተመሳሳይ ኹኔታ፣ በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም. የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ፣ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን፣ የከተማው አስተዳደር መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል፡፡


ባለፈው ማክሰኛ፣ በሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ላይ የተፈጸመውን ጨምሮ፣ በሌሎችም አካባቢዎች እየተፈጸመ ስላለው ግድያ፣ መረጃ እንዳለው የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ)፣ በየሥፍራዎቹ ተገኝቶ፣ ስለ ኹኔታው እንዳያጣራ፣ የጸጥታ ኹኔታው ዕንቅፋት እንደኾነበት አስታውቋል።


በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች፣ በንጹሐን ዜጎች ላይ ስለሚፈጸሙ ግድያዎችም እንደዚኹ፣ መረጃ ቢደርሰውም፣ ባለው የጸጥታ ኹኔታ ምክንያት፣ በቦታው ተገኝቶ ለማጣራት አስቸጋሪ እንደኾነበት፣ ኮሚሽኑ ገልጿል።


መንግሥት፣ ለችግሩ እልባት እንዲሰጥና የሰላማዊ ሰዎችን ግድያ እና መፈናቀል፣ እንዲሁም ንብረት መውደም እንዲያስቆም፣ በተደጋጋሚ እያሳሰበ መቆየቱንም፣ ኢሰመኮ አውስቷል።
36 views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:52:11 ጋቢና ቪኦኤ
https://amharic.voanews.com/a/7148600.html

ጋቢና ቪኦኤ የአዲሱ ትውልድ ድምፅ

በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ክፍል ተዘጋጅቶ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ የሚቀርብ የወጣቶች መርኃግብር ነው፡፡ በየቀኑ በኢትዮጵያዊያን ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2፡00 እስከ 2፡30 ይቀርባል፡፡
32 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:51:11 የጀርመኑ መራሄ መንግስት ቻይና በሃይል ታይዋንን ከመቀላቀል እንድትታቀብ አስጠነቀቁ
https://amharic.voanews.com/a/Germany-s-Scholz-warned-china-on-using-force-against-Taiwan/7148582.html

ቻይና ሃይልን በመጠቀም ታይዋንን ለመቀላቀል እንዳትሞክር ማስጠንቀቃቸውን የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ለአገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል። ኦላፍ ሾልዝ ማስጠንቀቂያውን የተናገሩት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቻንግ ከተመራ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት መሆኑን ገልጸዋል።


“በተናጠል ውሳኔ እና በሃይል፣ በምሥራቅ እና ደቡብ ቻይና ባህር ላይ ያለውን ሁኔታ ለመቀየር የሚደረግ ማንኛውንም ጥረት እንቃወማለን” ብለዋል ሾልዝ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር።


“በቻይና በሚታየው የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የሕግ የበላይነት አለመከበር ያሳስበናል” ሲሉ አክለዋል።


ታይዋንን በኃይል ለመቀላቀል  የምትዝተው ቻይና፣ በታይዋን አቅራቢያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጨምራለች፡፡


ታይዋን በበኩሏ ጥቃት ቢደርስባት ራሷን እንደምትከላከል ታስታውቃለች፡፡
32 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:50:11 የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሜሪካንን በመጎብኘት ላይ ናቸው
https://amharic.voanews.com/a/biden-welcomes-modi-to-white-house-for-talks-state-dinner/7148566.html

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዋይት ሃውስ ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል።




“ዓለም የገጠማት ችግር ህንድ እና አሜሪካ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚጠይቅ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል ባይደን። “ያንንም በማድረግ ላይ ነን” ሲሉ አክለዋል፡፡


“የሞዲ ጉብኝት ነጻ፣ ግልጽ፣ የበለጸገ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ኢንዶ ፓሲፊክ ቀጠናን የሚፈጠር እና፤ በቴክኖሎጂ፣ መከላከያ፣ ንጹህ ሃይል እንዲሆም በህዋ መስክ የሁለቱን አገራት ትብብር የሚያጠናክር ነው” ብሏል ሁለቱ መሪዎች ከመገናኘታቸው ቀደም ብሎ የወጣው የዋይት ሃውስ መግለጫ።


 




ሞዲ በቆይታቸው ለአሜሪካ ኮንግረስ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ለሞዲ ባልተለመደ ሁኔታም፣ ሁለቱ መሪዎች አንድ ላይ በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።


ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ህንድ ቁልፍ አጋር መሆናን ለማሳየት፣ ከዚህ በፊት የነበሩት አራት ፕሬዝደንቶች 15 ሰዓታት የሚፈጀውን ጉዞ ወድ ህንድ አድርገዋል።


እንደ ባይደን ግን በዚህ ደረጃ ሞዲን በክብር የተቀበለ ፕሬዝደንት አልነበረም ሲሉ የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ዘጋቢዎች በሪፖርታቸው አመልክተዋል። ሙሉ የክብር ዘብ አቀባበል እና ከዋይት ሃውስ ባሻገር በሚገኘውና ብሌየር ሃውስ ተብሎ በሚጠራው የእንግዳ መቀበያ  የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል።
28 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 21:00:49 የመናገር ነጻነት አሁንም አደጋ ላይ ነው
https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8A%93%E1%8C%88%E1%88%AD-%E1%8A%90%E1%8C%BB%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%88%81%E1%8A%95%E1%88%9D-%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%8C%8B-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8A%90%E1%8B%8D/a-65993070?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

ዶይቸ ቬለ በየዓመቱ የሚያካሂደው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ተጠናቋል ። በሁለት ቀናቱ መድረክ ስለመናገርና ፕሬስ ነጻነት ብሎም የተለያዩ የመገናኛ አውታርን የሚዳስሱ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል ። የዶይቸ ቬለ የመናገር ነጻነት የዘንድሮ ሽልማት ለኤልሣልቫዶራዊው ጋዜጠኛ ኦስካር ማርቲኔዝ ተሰጥቷል ።
42 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 20:59:23 የዳኝነት ክፍያ በኢትዮጵያ
https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8B%B3%E1%8A%9D%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB/a-66006468?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ መጨመር ፍርድ ቤቶች ለዜጎች ቀልጣፋ ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የዳኝነት አግልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የሚያግዝ ቢሆንም የፍትሐ ብሔር አለመግባባቶች እንዳይፈቱ እንቅፋት እንዳይሆንም ሥጋት አጭሯል።
42 views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 20:58:23 እገታ፣ግድያና ሁከት በኦሮሚያ ክልል
https://www.dw.com/am/%E1%8A%A5%E1%8C%88%E1%89%B3%E1%8D%A3%E1%8C%8D%E1%8B%B5%E1%8B%AB%E1%8A%93-%E1%88%81%E1%8A%A8%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%A6%E1%88%AE%E1%88%9A%E1%8B%AB-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D/a-66006439?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብዶ እንደሚሉት ባለፈው ሳምንት በአዳማ ሲካሄድ የነበረውን የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባን ጨርሰው አስጎሪ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የተመለሱት የሰደን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃጫ “ባልታወቁ” ባሏቸው የታጠቁ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው የተወሰዱት ቅዳሜ ሌሊት ነበር፡
40 views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ