Get Mystery Box with random crypto!

እለታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @eletawizena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-13 10:05:16 የጉራጌ የክልልነት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ እና ምላሹ
https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8C%89%E1%88%AB%E1%8C%8C-%E1%8B%A8%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%95%E1%8C%88-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B3%E1%8B%8A-%E1%8C%A5%E1%8B%AB%E1%89%84-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%88%9D%E1%88%8B%E1%88%B9/a-65260966?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 47 መሰረት ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በማንኛውም ጊዜ የክልልነት ጥያቄ ማንሳት ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል ። ለመሆኑ የጉራጌ ሕዝብ ክልል ልሁን፤ ራሴን በራሴም ላስተዳድር ብሎ ያቀረበው ጥያቄ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ከመንግሥት የተገኘው ምላሽስ ምንድን ነው? ሳምንታዊ እንወያይ መሰናዶ።
3 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 05:33:23 እስራኤል በሊባኖስና ፍልስጤም ላይ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ሰነዘረች
https://www.bbc.com/amharic/articles/ckv302484zpo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

እስራኤል በሊባኖስና ፍልስጤም ላይ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ሰነዘረች
38 views02:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 00:42:35 መርዛማ እባብ ጀርባው ላይ የወጣበት አብራሪ አውሮፕላኑን ካለ ችግር አሳረፈ
https://amharic.voanews.com/a/s-african-pilot-lands-plane-with-poisonous-cobra-on-his-back/7040908.html

አንድ ደቡብ አፍሪካዊ አውሮፕላን አብራሪ አደገኛ እባብ ጀርባው ላይ ከወጣ በኋላ አውሮፕላኑን ካለ ችግር በማሳርፉ አድናቆት ተችሮታል።


አራት ሰዎችን ጭኖ አንዲት አነስተኛ የግል አውሮፕላን ሲያበር የነበረው ሩዶልፍ ኢራስመስ ወደ ፕሪቶሪያ በማቅናት ላይ ሳለ፣ አደገኛና ገዳይ መርዝ እንዳለው የሚታወቀው ኬፕ ኮብራ የተሰኘው የእባብ ዓይነት በጀርባው ላይ ሲሄድ ተሰምቶታል።


የእባቡ ዓይነት በአብዛኛው በደቡብ አፍሪካ የሚገኝና መድሃኒት ካላገኙ መርዙ ገዳይ መሆኑን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።


ቀዝቀዝ ያለ ነገር ጀርባውን ሲጫነው እባቡ እንደወጣበት ማወቁን ኢራስመስ ተናግሯል።


የአገሪቱ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ለአብራሪው አድናቆቱን ገልጿል።
50 views21:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 17:34:14 ኢራን ሂጃብ ያላደረጉ ሴቶችን ለመከታተል ካሜራዎችን ገጠመች
https://www.bbc.com/amharic/articles/c3gz2n500xgo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

የኢራን ባለስልጣናት ሂጃብ ያልለበሱ ሴቶችን ለመለየት ህዝብ በሚሰበሰቡባቸው ቦታዎች ካሜራዎችን መትከል መጀመራቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
98 views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 07:49:05 "ልዩ ኃይልን ወደ ሌላ መዋቅር ለማስገባት በሚደረገው ጥረት የአፍራሽ ሚና በሚጫወቱት ላይ እርምጃ ይወሰዳል"
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd17p4lmjrno?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ሌላ የጸጥታ መዋቅር ለማስገባት በሚያደርገው ጥረት ላይ አፍራሽ ሚና በሚጫወቱት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል አሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥታቸው የክልል ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌላ መዋቅር ለማስገባት ሲዘጋጅበት የቆየ መሆኑን አስታውሰው በዚህ ተግባር ላይ “ሆን ብለው የአፍራሽነት ሚና በሚጫወቱት ላይ ተገቢው የሕግ ማስከበር እርምጃ ይወሰዳል። ለዚህም በቂ ዝግጅት ተደርጓል” ሲሉ የአስተዳደራቸውን ጠንከር ያለ አቋም አንጸባርቀዋል።
132 views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 21:37:06 በአፍሪካ የጂሃዲስቶችን እንቅስቃሴ ለመግታት አሜሪካ ድጋፍ ልታደርግ ነው
https://amharic.voanews.com/a/7042121.html

በአይቮሪኮስት፣ ቤኒን እና ቶጎ የሚታየው የጂሃዲስቶች ሁከት ወደ ምዕራብ አፍሪካ እንዳይዛመት አሜሪካ የረጅም ግዜ ድጋፍ ለማግኘት ዝግጅት ላይ መሆኗን አንድ ባለሥልጣን አስታውቁ።


ባለሥልጣኑ ለአሶስዬትድ ፕረስ እንደተናገሩት፣ የሩሲያ ቅጥር ወታደራዊ ቡድን የሆነው ዋግነርን እንቅስቃሴ ለመግታት የምዕራባውያን ድጋፍ አስፈላጊ ነው። በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምዕራብ አፍሪካ ሃላፊ ማይክል ሂዝ እንዳሉት ስጋቱ እያደገ የመጣና አገራቱ ከዚህ በፊት ገጥሟቸው የማያውቅ ነው።


በቀጠናው ጉብኝት አድርገው በቅርቡ የተመለሱት ሃላፍው ጨምረው እንዳሉት አሜሪካ አገራቱ የሚያስፈልጋቸውን የድጋፍ ዓይነት በመለየት ላይ ነች።


ሩሲያ በፈረንሳይኛ ተናጋሪ አፍሪካ አገሮች በኩል የሚታየውንና ቅኝ ግዛት ያስከተለውን ቅሬታ በመጠቀም ሃስተኛ መረጃ በማሰራጨትና ዋግነር ቡድንን በመጠቀም አገራቱን እያወከች ነው ስትል አሜሪካ ትከሳለች።
43 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 07:06:43 እሁድ፡-ጋቢና ቪኦኤ
https://av.voanews.com/clips/VAM/2023/04/08/20230408-213000-VAM131-program_original.mp3

Gabina VOA is designed to be an infotainment youth radio show broadcasting to Ethiopia and Eritrea in the Amharic language. The show brings varied perspectives on issues concerning young people in the Horn of Africa region. “Gabina” in the Amharic language is a front-row taxi ride.
110 views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 02:00:52 ጊኒ በቶን የሚገመት ኮኬይን ከወደቧ ላይ ወረሰች
https://amharic.voanews.com/a/guinea-cocaine/7039311.html

ጊኒ፣ በሴራሊዮን ሰንደቅ ዓላማ ከሚቀዝፍ መርከብ ላይ፣ 1ነጥብ 5 ቶን ኮኬይን ያዘች።


ካስማር በተባለ ወደቧ መልሕቁን ከጣለው እና በሴራሊዮን ባንዲራ ከሚቀዝፈው መርከብ ላይ፣ 1ነጥብ 5 ቶን የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ቁስ መውረሷን ጊኒ አስታውቃለች፡፡


ሮይተርስ እንደዘገበው፣ እያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ግራም ኮኬን የያዙ 60 ጥቅሎች፣ በመርከቡ ላይ መገኘታቸውን፣ የጊኒ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በመርከቡ ላይ የተገኙ ዐሥሩም ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ የጊኒ መንግሥት የዜና ማሠራጫ አመልክቷል፡፡


ሱስ አስያዥ መድኃኒትን በድብቅ የሚያስተላልፉ አካላት፣ የምዕራብ አፍሪካን ሀገራት፣ ከደቡብ አሜሪካ ወደ አውሮፓ ለማቀባበል፣ በብዛት እንደሚጠቀሙባቸው ሮይተርስ ጠቁሟል፡፡ ባለፈው ነሐሴም በጊኒ የባሕር ጠረፍ ላይ፣ ሦስት ቶን ኮኬይን እንደተያዘ፣ ዜናው አክሎ አውስቷል፡፡
118 views23:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 10:56:46 ያገረሸው የእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት
https://www.dw.com/am/%E1%8B%AB%E1%8C%88%E1%88%A8%E1%88%B8%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%8D%8D%E1%88%8D%E1%88%B5%E1%8C%A5%E1%8A%A4%E1%88%9D-%E1%8C%8D%E1%8C%AD%E1%89%B5/a-65251196?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

በእስራኤል እና ፍልስጥኤማውያን መካከል እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል። ከእስራኤል ወገን አንድ ወታደር መቁሰሉ ተረጋግጧል። ከ 400 በላይ ፍልስጥኤማውያን በእስራኤል ወታደሮች ቁጥጥር ስር ውለዋል። የፍልስጥኤም እስላማዊ ታጣቂ ቡድን የሮኬት ጥቃት ሲያደርስ እስራኤል በበኩሏ ለአጸፋው የአየር ጥቃት ሰንዝራለች።
144 views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 06:24:28 ባለፉት ሱስት ወራት ብቻ 14 ሺህ ፍልሰተኞች መያዟን ቱኒዚያ አስታወቀች
https://amharic.voanews.com/a/7042114.html

የቱኒዚያ የባህር ድንበር ጠባቂዎች ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ 14 ሺህ ፍልሰተኞችን መያዛቸውን አስታወቁ። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ግዜ ጋር ሲነጻጸር ቁጥሩ በአምስት ዕጥፍ ያደገ ነው ተብሏል፡፤


አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ከሳሃራ ግርጌ ካሉ አገራት ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ ናቸው ሲል መግለጫው አስታውቋል።


ባለፈው ወር የቱኒዚያው ፕሬዝደንት ካይስ ሳይድ ከአህጉሪቱ የሚመጡ ስድተኞችን ያሚያጥላላ ንግግር ከተናገሩ በኋላ፣ ፍልሰተኞቹ ከተከራዩበት ቤት እንዲወጡና ጥቃት እንዲደርስባቸው አድርጓል። በደርዘን የሚቆጠሩትም ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ ባህር ውስጥ ሰምጠዋል።


የጣልያን መንግስት በበኩሉ ባለፉት ሶስት ወራት 14 ሺህ የሚሆኑ ፍልሰተኞች ወደ አገሪቱ መግባታቸውን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ግዜ ጣልያን የገቡት ፍልሰተኞች 5ሺህ 300 እንደነበር መንግስት ጨምሮ ገልጿል።
148 views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ