Get Mystery Box with random crypto!

እለታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eletawizena — እለታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @eletawizena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 152

2022-07-11 09:51:04 የስሪ ላንካ ተቃዋሚዎች ከቤተ-መንግሥቱ ለመልቀቅቅድመ ሁኔታ አስቀመጡ  
https://www.bbc.co.uk/amharic/articles/cqvl6pj01g3o?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA
41 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 09:50:04 የዋጋ ንረት ምንድን ነው? እንዴትስ ሊቀረፍ ይችላል?
https://www.bbc.co.uk/amharic/articles/c80pxpr49neo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ዓመታት የኑሮ ውድነት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሻቅቧል። የሁሉም ምርቶችና አገልግሎቶች ዋጋ በብዙ እጥፍ ጨምሮ፣ የብር የመግዛት አቅም በእጅጉ አሽቆልቁሏል። በዓለም ላይ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ በአገር ውስጥ የተከሰተው ጦርነት እንዲሁም በዓለም ገበያ ያለው የነዳጅና የምግብ ምርቶች ዋጋ መጨመር ለዚህ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ግን ግን የዋጋ ንረትን እንዴት በቀላሉ ልንረዳው እንችላለን? መፍትሔውስ ምንድነው?
39 views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:04:10 ዕሁድ፡- ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና
https://av.voanews.com/clips/VAM/2022/07/10/20220710-180000-VAM068-program_original.mp3

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።


ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) - ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
75 views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:51:20 እሁድ፡-ጋቢና ቪኦኤ
https://av.voanews.com/clips/VAM/2022/07/10/20220710-170000-VAM131-program_original.mp3

Gabina VOA is designed to be an infotainment youth radio show broadcasting to Ethiopia and Eritrea in the Amharic language. The show brings varied perspectives on issues concerning young people in the Horn of Africa region. “Gabina” in the Amharic language is a front row taxi ride—symbolic of the show’s content as a fun ride that takes audiences from point “A” to point “B”. Gabina VOA’s main goal is Enlightening young people, introducing them to cutting-edge technological innovations, exposing them to new processes and ideas so they can be productive, informed and self-governing citizens.
76 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:50:33 የሀገሪቱ መሪ ስልጣን እስኪለቁ ድረስ ፣ ከቤተመንግስት እንደማይወጡ የሲሪ ላንካ ተቃውሞ ሰልፈኞች አስታወቁ
https://amharic.voanews.com/a/6652784.html

 


የሀገራቸውን ፕሬዚደንት ጎታባያና ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤት በመቆጣጠር ፣ በሀገሪቱ የባህር ኃይል ድጋፍ እንዲሸሹ ብሎም ከስልጣን እንዲለቁ ያደረጉት የሲሪ ላንካ ተቃዋሚ ሰልፈⶉች አሁንም ከፕሬዚደንቱ መኖሪያ ቤት ለመልቀቅ አልፈቀዱም ።


የተማሪዎች እንቅስቃሴ ፕሬዚደንት የሆነው ፣ ላሂሩ ዊራስካራ “ትግላችን ገና አላበቃም!” ሲል ለዘጋቢዎች ተናግሯል፣ በአሁኑ ሰዓት በደሴቲቱ ደቡባዊ የባህር ወሰን ላይ በሚገኝ መርከብ ውስጥ የተጠለሉት ራጃፓክሳ ፣ ከስልጣን መልቀቃቸውን ረቡዕ ዕለት ካስታወቁ በኃላ፣ ከስልጣን የመልቀቃቸው ነገር እርግጥ እስኪሆን ድረስ ፣ ትግሉ እንደማይቆም ዊራስካራ አክሏል ።


የቅዳሜው ዕለት ክስተት ፣ በደቡባዊ እስያዊት ደሴት የደረሰው ያልተጠበቀ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና የራጃፓክሳ ቡድን የአመራር ድክመት እና ሙስና የቀሰቀሰው ለወራት የዘለቀው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጣሪያ ተደርጎ ተቆጥሯል።


በመቶሺ የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች ራጃፓክሳ ፣ በአንድ ወቅት በተነጻጻሪነት ሀብታም የነበረችውን ሀገር በማሽመድመድ በህዝቧ ላይ መከራን ላመጣው፣ የመድሃኒት ፣ ምግብ እና ነዳጅ እጥረት ኃላፊነት እንዲወስዱ ነበር ለተቃውሞ የወጡት።


በቅኝ ግዛት ዘመን የተገነባውን፣ የፕሬዚደንቱን ቤተመንግስት ሰብረው የገቡት ተቃዋሚዎች፣ በቅንጡ ክፍሎች ውስጥ ተሰይመዋል፣ በመዋኛ ገንዳው ውስጥ ተምነሽንሸዋል፣ የፕሬዚደንቱን አልባሳት ፈትሸዋል ።


ይሄ ከመሆኑ አስቀድሞ፣ ራጃፓክሳ እንዲያመልጡ ለመርዳት ወታደሮች ወደ ሰማይ የተኮሱ ሲሆን፣ ፕሬዚደንቱ የባህር ኃይል ጀልባ እንዲሳፈሩ ተደርገው ለደህንነታቸው ወደ ሀገሪቱ ደቡባዊ ውሃማ ቀጠና ተወስደዋል ።


በዛሬው ዕለት ለሁሉም ዜጋ ክፍት በነበረው የፕሬዚደንቱ መኖሪያ ውስጥ ህጻናት እና ወላጆቻቸው በስፍራው የሚገኘውን ፒያኑ ሲቆረቁሩ፣ ቅንጡ የጥበብ ስራዎችን ሲያደንቁ፣ በፕሬዚደንቱ ወንበር ላይ በየተራ ሲቀመጡ ውለዋል። ዘገባው የኤ ኤፍፒ ነው።
67 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:49:20 ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በመጠጥ ቤት ታዳሚዎች ላይ በተከፈተ የእሩምታ ተኩስ  19 ሰዎች ተገደሉ
https://amharic.voanews.com/a/6652777.html

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ቀጠና እና በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ ሁለት መጠጥ ቤቶች ላይ በደረሱ የእሩምታ ተኩስ ጥቃቶች 19 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ ።


በጆሃንስበርግ ሶዌቶ መንደር ፣ በሚኒባስ ተጭነው የመጡ ጥቃት አድራሾች በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ በመዝናናት ላይ በሚገኙ ሰዎች ላይ የእሩምታ ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ 15 ሰዎች ተገድለዋል ።


በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ላይ በምትገኘው ፣ ፒተርማሪትዝበርግ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሌላ መጠጥ ቤት ውስጥ ደግሞ ሁለት ሰዎች ካለ ልዩነት በዚህ በነበሩ ሰዎች ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኃላ በነበረ የተኩስ ልውውጥ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ 8 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ።


ፖሊስ ጥቃቶቹ ተያያዥ ስለመሆናቸው ለመናገር ጊዜው ገና መሆኑን ጠቁሞ፣ ተመሳሳይነታቸውን ግን ማጤኑን አስታውቋል-። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ እንደሌለ ተገልጿል። ሁለቱ ጥቃቶች የደረሱት ፣ ሀገሪቱ ከአፓርታይድ ዘመን ተላቃ ዴሞክራሲን መከተል ከጀመረችባቸው ሶስት አስርት ዓመታት ወዲህ ፣ በእጅጉ የከፋ ነው በተባለ የኃይል ጥቃቶችን እና አለመረጋጋት ሰደድ መመታት በቀጠለችበት ሰዓት ነው።


ባለፈው ሀምሌ ወር ላይ በእጅጉ የተንሰራፋ አመጽ፣ ዘረፋ ፣ በእሳት ማጋየት እና የመሰረተ-ልማት እና ኢንደስትሪ ተቋማትን ባወደመ ጥቃት ወቅት 350 ሰዎች ሞታዋል።በኮቪድ 19 ዳፋ በተፈተነችው ሀገር በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ። ዘገባው የኤ ኤፍ ፒ ነው።


 


 
63 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:12:09 መንግሥት ጭፍጨፋውን ማስቆም ለምን ተሳነው?
https://www.dw.com/am/%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B5-%E1%8C%AD%E1%8D%8D%E1%8C%A8%E1%8D%8B%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%89%86%E1%88%9D-%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%95-%E1%89%B0%E1%88%B3%E1%8A%90%E1%8B%8D/a-62414318?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

በኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት እዚህም እዚያም ኼድ መለስ ይል የነበረው ብሔርን መሰረት ያደረገ ግድያ እና ጭፍጨፋ ከሰሞኑ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ ብርቱ ቁጣ ቀስቅሷል። ባለፉት ቀናት ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች በተከታታይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል። ሙሉ ውይይቱ በድምፅ ከታች ይገኛል።
64 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:11:10 የኢትዮጵያ የቢዝነስ መድረክ በፓሪስ
https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%89%A2%E1%8B%9D%E1%8A%90%E1%88%B5-%E1%88%98%E1%8B%B5%E1%88%A8%E1%8A%AD-%E1%89%A0%E1%8D%93%E1%88%AA%E1%88%B5/a-62425499?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss

መድረኩ የፈረንሳይ ኩባንያዎችና ባለሃብቶች በተለያዩ የሥራ መስኮች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መሠማራት እንዲችሉ ለመሳብ እንዲሁም አማራጭ የቢዝነስ ዕድሎችን ለማመላከት የተመቻቸ ነው ተብሏል።
68 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 14:58:33 በደቡብ አፍሪካ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 15 ወጣቶች ተገደሉ
https://www.bbc.co.uk/amharic/articles/c51x3rp17pzo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

በደቡብ አፍሪካዋ ሶዌቶ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ዛሬ በተፈጸመ የጦር መሣሪያ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
91 views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:18:27 ፅንስ የማቋረጥ መብት እንዲከበር የሚጠይቁ በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን አደባባይ ወጡ
https://www.bbc.co.uk/amharic/articles/c4n2v2n4x7xo?at_medium=RSS&at_campaign=KARANGA

ከሁለት ሳምንት በፊት የፅንስ ማቋረጥን የሚፈቅደው ሕግ የቀለበሰውን የፍርድ ውሳኔ በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በዋይት ሐውስ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።
91 views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ